የኑዛዜ ሰነዶችን የማረጋገጥና የመመዝገብ አገልግሎት ለማግኘት ወደተቋማችን ሲመጡ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
መረጃውን ለሌሎች እንዲደርስ በማድረግ ተቋሙ አላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት እንዲሁም ብልሹ አሰራር ለማስቀረት እያደረገ ያለውን ጥረት ያግዙ ፡፡
በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ (በፍ/ህግ ቁጥር/ 881 መሠረት፣) ለማድረግ
• የኑዛዜ ተጠቃሚውን ወይም ጉዳዩን በግልጽ የሚያመላክት በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የኑዛዜ ሰነድ፤
• ሁለት ምስክሮች፤ (ችሎታ ያላቸውና ተነቦላቸው/አንብበው የተስማሙ)
•የተናዛዥ እና የምስክሮች መታወቂያ፤
የኑዛዜ መሻሪያ (በፍ/ብ/ህግ/ቁጥር 898 መሰረት፣)
• በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የኑዛዜ መሻሪያ ሰነድ፤
• ሁለት ምስክሮች፤
• የኑዛዜ ሻሪው እና የምስክሮች መታወቂያ ፤
• ቀደም ሲል ተረጋግጦ የተመዘገበው የኑዛዜ ሰነድ፤
ኑዛዜን ለማድረግም ሆነ ለመሻር ሚወስደው ጊዜ 20 ደቂቃ ሲሆን የሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት ይደረግባቸዋል፡፡
• በኑዛዜ ሰነድ ውስጥ ተናዛዡ ኑዛዜውን ያደረገው በሙሉ ፈቃደኝነት እና አንብቦ ወይም ተነቦለት የተስማማ መሆኑ መገለጽ አለበት፡
• አንድ የኑዛዜ ጽሁፍ ላይ ኑዛዜ ማድረግ የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡
• አንድ ሰው ለተወካይ እንደ እኔ በመሆነ ኑዛዜ እንዲያደርግልኝ (እንዲናዘዝልኝ)፤ ኑዛዜውን አንዲለውጥልኝ ወይም እንዲሽርልኝ ብሎ ሌላን ሰው ለመወከል አይችልም፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለአካለ መጠን ላልደረሰ ልጅ ሞግዚት የሆነ ሰው አካለ መጠን ባልደረሰው ልጅ ስም ኑዛዜ ሊደርግ አይችልም፡፡
• በህግ የተከለከለ ሰው ኑዛዜ ለማድረግ ሙሉ ችሎታ አለው፡፡ ሆኖም በፍርድ የተከለከለ ሰው በፍርድ በተከለከለበት ጊዜ ኑዛዜ ለማድረግ አይችልም፡፡
#አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties

በአዋጅ 1156/2011 የመብት ጥያቄ ስለሚቀርብበት የጊዜ ገደብ በተመለከተ በአንቀፅ 163 ስር የይርጋ ጊዜ ተቀምጧል፡፡
አንቀፅ 163(1) ስር የሚመለከተው በቅጥር ላይ ከተመሰረተ ግንኙነት የሚመነጭን ማንኛውንም አይነት ክስ ሲሆን በተለይም በአንቀፅ 163(3) አንቀፅ 163(4) ስር ከተመለከቱት ውጭ ያሉትን የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነቶችን ይመለከታል ፤ የጊዜ ገደቡም የመብቱን ጥያቄ ለማቅረብ ከሚቻልበት ቀን ጀምሮ እስከ 1 (አንድ) ዓመት ድረስ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡
በሌላ በኩል አንቀፅ 163(3) የሚመለከተው ሠራተኛን ብቻ ሲሆን ይኸውም ሠራተኛው የሚያቀርበው የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓት እና ሌሎች ከአሰሪና ሰራተኛ ጋር የተገናኙ ክፍያዎችን ነው፡፡ ይህ አንቀፅ በተለይም በስራ ላይ ያሉ እና የስራ ውላቸው ያልተቋረጠባቸው ነገር ግን የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓት እና ሌሎች ክፍያዎች ጋር በተያያዘ ከአሰሪ ጋር አለመግባባት ያላቸውን ሰራተኞችን በዋናነት የሚመለከት ነው፡፡ የጊዜ ገደቡም ጥያቄ መጠየቅ ከሚገባው ጊዜ ጀምሮ እስከ 6 (ስድስት) ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡
በመጨረሻም አንቀፅ 163(4) በዋናነት የሚመለከተው የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በሠራተኛውም ሆነ በአሠሪው የሚቀርብን ማንኛውም አይነት የክፍያ ጥያቄ ነው፡፡ የጊዜ ገደቡም የሥራ ውሉ በተቋረጠ በ 6 (ስድስት) ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡(ሕግ አገልግሎት)

በጊዜያዊነት የገቡ ዕቃዎች አገር ውስጥ የሚቆዩበት ጊዜ
*****
በጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀፅ 73 (በ1160/2006 እንደተሻሻለው) መሰረት በጊዜያዊነት የገቡ ዕቃዎች አገር ውስጥ የሚቆዩበት ጊዜ ከዚህ እንደሚከተለው ነው።
1) ከቱሪዝምና ከባህል ልውውጥ ወይም ከቴክኖሎጅ ሽግግር ጋር የተያያዙ ዕቃዎች ወደ አገር ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ተመልሰው መውጣት አለባቸው፤
2) ንግድ ለማስተዋወቅ የገቡ ዕቃዎች የማስተዋወቅ ተግባር በተጠናቀቀ በ2 ወር የጊዜ ገደብ ውስጥ መውጣት አለባቸው፤
3) ለግንባታ ሥራ፣ ለምክር አገልግሎት፣ ከእርዳታ ሥራ ጋር በተያያዘ ወይም በፕሮጀክት ስምምነት መሠረት ወደ አገር የገቡ ዕቃዎች በፕሮጀክቱ ስምምነት የተገለፀው የጊዜ ገደብ ሲጠናቀቅ ወይም ፕሮጀክቱ ወይም የእርዳታ ሥራው እንደተጠናቀቀ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ተመልሰው መውጣት አለባቸው፤
4) በጊዜያዊነት ወደ አገር ውስጥ የገባ ዕቃ በዚህ አዋጅ በተደነገገው የጊዜ ገደብ ተመልሶ ሊወጣ የማይችል መሆኑን አስመጪው ከጠየቀና በቂ ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠ ኮሚሽኑ የጊዜ ገደቡን ሊያራዝምለት ይችላል፤
5) በአዋጁ አንቀጽ 73 (4) መሠረት ዕቃው አገር ውስጥ የሚቆይበት ጊዜ ካልተራዘመ በስተቀር በሕግ የተወሰነው የመቆያ ጊዜ እንደተጠናቀቀ በ2 ወር ጊዜ ውስጥ ዕቃው ተመልሶ ከአገር መውጣት አለበት፡፡ ሆኖም ዕቃው ተመልሶ ከአገር ያልወጣ እንደሆነ በእርጅና ቅናሹ ላይ የሚከፈለው ቀረጥና ታክስ እንዲሁም አስተዳደራዊ መቀጫ ሲከፈል የተያዘው ዋስትና ተመላሽ ተደርጎ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ዕቃው ተመልሶ ከአገር እንዲወጣ ይደረጋል፤
6) ማንኛውም ቱሪስት ተሽከርካሪን ጨምሮ የያዘውን የግል መገልገያ ዕቃ፣ በዋስትና በማስመዝገብ በጊዜያዊነት ወደ አገር ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ ለዚህ ንዑስ አንቀፅ አፈፃፀም በሚኒስቴሩ (የገንዘብ ሚኒስቴር) ዝርዝር መመሪያ ሊያወጣ ይችላል፤
7) ወደ አገር ውስጥ የገባ ቱሪስት ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካልገጠመው ወይም የመቆያ ጊዜው ካልተራዘመለት በስተቀር በአዋጁ አንቀጽ 73 (1) በተለመከተው ጊዜ ውስጥ ተመልሶ ማውጣት ያለበት ሲሆን ዕቃውን ከአገር ያላስወጣ እንደሆነ ዕቃው ውርስ ተደርጎ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፤
8) ለዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (7) አፈፃፀም “ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት“ ማለት አግባብነት ባለው ማስረጃ የሚረጋገጥ ከባድ ህመም ወይም በህግ ቁጥጥር ሥር መዋል ወይም ከአገር እንዳይወጣ መታገድ ወይም የዕቃው መጥፋት ወይም መጎዳት እና ከነዚህ ጋር ተመሳሳይነት የሆነ ቱሪስቱ እንዳይመለስ የሚያደርግ ማንኛውም አስገዳጅ ሁኔታ ማለት ነው፤
9) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (1) የተመለከተው ቢኖርም ቱሪስቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር ፈቃድ ያገኘ እንደሆነ ወደ አገር ውስጥ ያስገባው ዕቃ የመኖሪያ ፈቃድ በተገኘበት ቀን ወደ አገር ውስጥ እንደገባ ተቆጥሮ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት በመፈፀም ቀረጥና ታክስ ከፍሎ ዕቃው አገር ውስጥ እንዲቀር ሊፈቀድለት ይችላል፤
10) በጊዜያዊነት ዕቃ ወደ አገር ውስጥ ያስገባ ሰው ዕቃውን ከአገር ለማስወጣት የማይችልበት በቂ ምክንያት ካቀረበ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት በመፈፀም በዕቃው ላይ ቀረጥና ታክሱን ከፍሎ ዕቃው አገር ውስጥ እንዲቀር ሊፈቀድለት ይችላል፤
11) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (10) የተመለከተው ቢኖርም ዕቃው አገር ውስጥ እንዲቀር የቀረበው ጥያቄ ዕቃው አገር ውስጥ እንዲቆይ የተፈቀደለት ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ከሆነ በዕቃው ላይ ሊከፈል የሚገባው ቀረጥና ታክስ መከፈሉ እንደተጠበቀ ሆኖ አስመጪው ያስያዘው ዋስትና ተመላሽ ተደርጎ የቀረጥና ታክሱን 25% በመቶ መቀጫ ከፍሎ ዕቃው አገር ውስጥ እንዲቀር ይደረጋል፤
12) በጊዜያዊነት ወደ አገር ውስጥ የገባ ዕቃ በዚህ አንቀፅ መሠረት ተመልሶ ከአገር ያልወጣ ወይም የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ተፈፅሞበት አገር ውስጥ እንዲቀር ያልተፈቀደለት እንደሆነ ዕቃው ይወረሳል፤
13) ለዚህ አንቀፅ አፈፃፀም “ቱሪስት” ማለት ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ኢትዮጲያ ውስጥ ለመቆየት ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ የውጭ አገር ዜጋ ሲሆን ለሥራ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባን ሰው አይጨምርም፤
/
በደንበኞች ትምህርት ቡድን
መጋቢት 13 ቀን 2014
ኮምቦልቻ፤

ኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር EWLA
የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በፌደራል ደረጃ በ1987 ዓ.ም በሴት የህግ ባለሙያዎች የተቋቋመ ፤ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተመዘገበ ሃገር በቀል የሲቪክ ማህበር ሲሆን ላለፉት ከ25 ዓመታት በላይ የሴቶችን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ሕጋዊ መብቶች እንዲታወቁ በማድረግ ሴቶች በሕገ-መንግስቱ እና በሌሎች ሕጎች በተመላከቱ መብቶቻቸዉ እንዲጠቀሙ የሚያግዙ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ፡፡
የማህበሩ ግብ ሴቶች በሁለንተናዊ ዘርፍ እኩል ተጠቃሚና ተሳታፊ እንዲሆኑ አስተዋፅኦ ማድረግ ሲሆን በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን መከላከልና ለሴቶች ከጥቃት የፀዳ አከባቢን መፍጠር አላማዉ አድርጎ በሶስት ፕሮግራሞቹ ማለትም የህግ ምርምር እና ጥናት፣ የህዝብ ማስተማርና አቅም ግንባታ እንዲሁም ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት በመስጠት ይሰራል፡፡ 👍👍👍👇👇👇👇👇👇👇
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ልዩልዩ #አለ_ችሎት #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

የዳግም ዳኝነት ጥያቄና የሰበር የህግ ትርጉም!
በፍ/ስ/ስ ህግ ቁጥር 6 መሰረት የዳግም ዳኝነት ጥያቄ ጉዳይ በይግባኝ ታይቶ ውሳኔ ከተገኘ በኋላም ቢሆን በድንጋጌው የተመለከቱት መመዘኛዎች ተሟልተው እስከተገኙ ድረስ መቅረብ እንደሚችሉ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል! ከዚህ በተጨማሪም አንድ ክስ በይርጋ መዘጋቱ ፍ/ስ/ስ ህግ ቁጥር 6 የተመለከቱት መስፈርቶች በተሟሉበት ሁኔታ የዳግም ዳኝነት ጥያቄን ላለማስተናገድ እንደበቂ ምክንያት የማይወሰድና በድንጋጌውም በመመዘኛነት ያልተቀመጠ ነው! (ቅፅ 19 ሰበር መዝገብ ቁ. 104028 እና ቅፅ 9 ሰበር መዝገብ ቁ. 43821)

ያለማስታወቂያ የስራ ዉል የተቋረጠበት የግል ድርጅት ሰራተኛ ካሳና የስንብት ክፍያ አያገኝም ::
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 1156/11 አንቀፅ 27/ሐ/ መሰረት የተሰናበተ ሰራተኛ ማግኘት የሚችለው ያልወሰደው ደሞዝ : የትርፍ ጊዜ ስራ ክፍያ ካለ : የልወሰደው የዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ : እና የስራ ልምድ ማስረጃ ሰርተፍኬት ብቻ ሊያገኝ ይችላል!

#ተራዝሟል
የመኖርያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪን እና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ አሳውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን ጥያቄና አገራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት የመኖርያ ቤት ተከራዮችን ለማስለቀቅና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ለመገደብ ደንብ ማውጣቱን አስታውሷል።
ደንቡ ላለፉት ሶስት ወራት እንዲራዘምም ተደርጎ እንደነበር ገልጿል።
አሁንም ዜጎችን ከተለያዩ ጫናዎች ለመከላከል ሲባል ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት እንዲራዘም የከተማው አስተዳደር መወሰኑን አሳውቋል።
ስለሆነም በዚሁ መሰረት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ተከራዮችን ማስለቀቅና እና የቤት ኪራይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።
" ኢትዮጵያዊ የመተሳሰብና የመተጋገዝ ባህላችንን በማሳደግ ፈታኝ ሁኔታዎች በጋራ ሆነን እንሻገር " ሲል የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አስተላልፏል።
@tikvahethiopia

Legal Trainee
Commercial Bank of Ethiopia
Addis Ababa
Full–time
JOB JOB DETAILS: Requirement • Qualification and word Experience: LLB Degree in Law with zero year of work experience
• Year of Graduation: Only 2020/21
Graduate • CGPA: 3.0 and above • Age : 35 and Below
Work Hours: 8
Experience in Months: Level of Education: Associate Degree

Attorney I
Awash Insurance Company S.C
Addis Ababa
Full–time
JOB DETAILS: Category: Banking & Insurance - Legal Salary Offer: As per Company Scale Experience Level: Junior Total Years Experience: 2 Job Requirement Educational Qualification: LLB degree in law
Work Experience: 2 years of relevant experience as an Attorney Qty: 2 (two)
Age: Below 40 years
Salary: Per Company’s scale with package of other benefits Place of work: Addis Ababa Work Hours: 8 Experience in Months: 24 Level of Education: Bachelor Degree
https://www.greatethiopiajobs.com/jobs/job-detail/job-Attorney-I-job-at-Awash-Insurance-Company-S.C-52849/nav-15?Itemid=231&utm_campaign=google_jobs_apply&utm_source=google_jobs_apply&utm_medium=organic

Greatethiopiajobs
Awash Insurance company S.C
Vacancy title: Attorney I
[ Type: FULL TIME , Industry: Insurance , Category: Legal ]
Jobs at:
Awash Insurance Company S.C
Deadline of this Job: 26 March 2022
Duty Station: Within Ethiopia , Addis Ababa , Horn of Africa …

Jimma District Operation Legal Officer at Bank of Abyssinia
Bank of Abyssinia
Addis Ababa
ETB 1,592–ETB 26,539 a month
Full–time
Job Requirement Education : LLB Degree in Law Experience: Minimum of 6 years banking experience, of which 3 years in the area of Law. Job Grade : VIII
Place of work : Jimma District Office, Salary: As per the Bank’s scale
Bank of Abyssinia
https://jobwebethiopia.com/jobs/jimma-district-operation-legal-officer-bank-abyssinia/?utm_campaign=google_jobs_apply&utm_source=google_jobs_apply&utm_medium=organic

Jobweb Ethiopia
Jimma District Operation Legal Officer at Bank of Abyssinia - Jobweb Ethiopia
Job Requirement Education : LLB Degree in Law Experience: Minimum of 6 years banking experience, of which 3 years in the area of Law. Job Grade : VIII Place of work : Jimma District Office, Salary: As per the Bank’s scale
ኦንላይን ዶክ.rar
35.1 MB
ሁሉም የሥልጠና ሰነድ
በወንጀል ምርመራ ሂደት የዐቃቤ ሕግ ሚና
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን ተከታታዮች፤ እንዴት ናችሁ ለዛሬ በወንጀል ምርመራ ሂደት የዐቃቤ ሕግ ሚና ምን ይመስላል በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ በፍትህ ሚኒስቴር በህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ውስጥ ዐቃቤ ሕግ ከሆኑት ከአይናለም ኃይለማሪያም ጋር ቆይታ አድርገን ተከታዩን ማብራሪያ ሰጠውናል እንደሚከተለው ይቀርባል፡-
በመጀመሪያ ዐቃቤ ህጓ ከኛ ጋር ለሚያደርጉት ቆይታ ምስጋናችን አቅርበን በወንጀል ምርመራ ሂደት የዐቃቤ ሕግ ሚና ምን ይመስላል? የሚለውን ጥያቂያችን አስከተልንላቸው
እሳቸውም የቃለ-መጠይቅ ክፍሉ ለዚህ ቃለ-መጠይቅ ስለጋበዛቸው ምስጋናቸውን አቅርበው ዐቃቤ ህግ በወንጀል ምርመራ ሂደት ውስጥ ብዙ ሚና ያለው ሲሆን በመጀመሪያ የምናየው ብለው ተከታዩን ርዕሰ-ጉዳይ በማስቀደም ማብራሪያቸውን ይጀምራሉ
አቤቱታ እና ጥቆማ በመቀበል ሂደት ውስጥ የዐቃቤ ህግ ሚና
በወንጀል ጉዳይ የዐቃቤ ህግ ሚና የሚጀምረው የወንጀል ጥቆማ ለፖሊስ ወይም ለዐቃቤ ህግ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን አንስተው በሌሎች ህጎች ለፖሊስ የተሰጠው ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ዐቃቤ ህግ በፌዴራል ፍርድ ቤት ስልጣን ስር የሚወድቅ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር ከማድረግ በተጨማሪ ክትትልና ድጋፍም ያደርጋል ብለዋል፣ በፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ዘርፍ የሚከናወኑ የምርመራ ሥራዎችንም ይመራል፣ ይከታተላል፣ ያስተባብራል፣ ሪፖርት እንዲቀርብለት ያደርጋል፤ ብለው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 40 ዋቢ አድርገው ያነሳሉ፡ ከተል አድርገውም ዐቃቤ ሕግ በሁሉም የፌዴራል ፖሊስ ጣቢያዎች እንዲሁም የፌዴራል ጉዳዮች በሚታዩባቸው የክልል ፖሊስ ጣቢያዎች ተገኝቶ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ጥቆማዎችን በህግ አግባብ በማስተናገድ ከፖሊስ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የደረሰውን የወንጀል አቤቱታ ወይም ጥቆማ በመቀበል የመጣውን ባለጉዳይ በሚገባ በማስተናገድ፤ የቀረበው አቤቱታ ወይንም ጥቆማ፤
በወንጀል ሊያስጠይቅ የሚችል መሆን አለመሆኑን በመለየት
ወንጀል ስለመፈጸሙ የሚጠቁም መረጃ ስለመኖሩ፣
ከለየ በኋላ ከፖሊስ ጋር በመሆን የምርመራ ዘዴዎችን በመወሰን ምርመራን ያስጀምራል ሲሉ የመጀመሪያውን የዐቃቤ ህግ ሚና ይናገራሉ፡፡
ምርመራን መምራት የዐቃቤ ህግ ድርብ ሚና መሆኑን ያነሱት ዐቃቤ ሕጓ
ምርመራው ከተጀመረ በኋላ፤
ቀድሞ ተጠርጣሪ ሊከሰስበት የሚችልበትን ወንጀል በመለየት፤ ከክስ ባሻገር ሌሎች አማራጭ መንገዶችን ይለያል፡፡
ውጤታማ በሆነ መንገድ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤት ለማቅረብ ይቻል ዘንድ ማስረጃዎች እንዴት መሰብሰብ እንዳለባቸዉ በመለየት መመሪያ ይሰጣል፡፡
ምርመራዉ የሞያ ምስክርነትን የሚፈልግ መሆኑን በመለየት ባለሞያዉ የምስክርነት ቃሉን እንዲሰጥ መመሪያ ይሰጣል፡፡
በተለያዩ የመንግስትና የግል ድርጅቶች የሚገኝ ማስረጃ እንዴት መሰብሰብ እንዳለበት በማሳየት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስለማስፈለጉ በመለየት ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡
ስለ ተጠርጣሪው መያዝ ውሳኔ በመስጠት በተያዘ ጊዜ ሊኖር ስለሚገባ የመብት ጥበቃ ወይም በማንኛውም ግለሰብ ላይ ከወንጀል ምርመራ ጋር በተያያዘ የተፈጸመ የመብት ወይም የህግ ጥሰት በሚኖርበት ወቅት ተገቢውን ማጣሪያ አድርጎ ውሳኔ ያሰጣል ሲሉ ዐቃቤ ህግ ምርመራን በመምራት ወቅት ያለውን ሚና ዘርዘር አድርገው ይናጋራሉ፤ ቀጥለውም በዚህም ወቅት
በቃል አቀባበል ጊዜ ተጠርጣሪው ያለው መብት ተነግሮት ሳይገደድ በፈቃደኝነት ቃል መስጠት እንዳለበት
ከማንኛውም አካላዊም ሆነ ስነ-ልቦናዊ ጫና የመጠበቅ መብት እንዳለው እንዲነገረው በማድረግ
በተመሳሳይ ጉዳይ በድጋሚ ያለመከሰስ መብት ያለው መሆኑ እንዲነገረው በማድረግ
እንደነገሩ ክብደት እና ሁኔታ በፍርድ ቤት በመቅረብ ስለተጠረጠረው ሰው የመያዣ ትዕዛዝን፣ ብርበራን፣ የዋስ መብትን እና ሌሎች የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሚያስፈልግባቸው ጉዳዮች ላይ ቀርቦ ጥያቄ ያቀርባል ክርክር ያደርጋል ብለዋል ፡፡
ብርበራ እና መያዝን በተመለከተ የዐቃቤህግ ሚናስ? ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ
ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ ጋር በመሆን በወንጀል ምርመራ የሚደረግን ማንኛውንም ብርበራ ለጉዳዩ አስፈላጊ መሆኑንና ተገቢዉን ማስረጃ ለማግኘት ብቻ የሚደረግ ወይም የተደረገ ስለመሆኑ በማረጋገጥ ለዚህም፡ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 32 መሰረት ወንጀል የተፈጸመበት ወይም በማስረጃነት የሚፈለግ ወይም የሚወረስ ዕቃ ብርበራዉ ሊደረግ በታሰበበት ቦታ ዉስጥ የተቀመጠ መሆኑን የሚያሳይ በቂ መረጃ ወይም ጥርጣሬ መኖሩን፤ ከሚመለከተዉ ፍርድ ቤት ብርበራዉ እንዲደረግ ትዕዛዝ ስለመሰጠቱ የሚያረጋግጥ የብርበራ ፍቃድ መኖሩን፤ እንዲሁም ያለብርበራ ትዕዛዝ የሚደረግ ከሆነም የብርበራ ትዕዛዝ ከፍርድ ቤት እስኪወጣ ዕቃዉ ይጠፋል ወይም አደጋ ይከሰታል ተብሎ በበቂ ሁኔታ ግምት የሚያስወስዱ ምክንያቶች ስለመኖራቸዉ፤ ብርበራዉ ከታሰበለት ዓላማ ዉጭ የተጠርጣሪዉን ወይም የሌላ ሰውን መብት ያልጣሰ መሆኑን ያረጋግጣል ሲሉ ብርበራ እና መያዝን በተመለከተ የዐቃቤ ህግ ምን እንደሚመስል ያብራራሉ፡፡
የኤግዚቢት አያያዝንና አቆያየትን በተመለከተ የዐቃቤ ህግ ሚና
ከፖሊስ ጋር በመሆን አንድ ንብረት በማስረጃነት ከመያዙ በፊት ንብረቱ ለወንጀል ምርመራው ወይም ለክሱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አስተዋፆ ያለዉ መሆኑን በማረጋገጥ፤ የማንኛውንም ኤግዚቢት ይዘት ወይም ባህሪ ለማወቅ በጣም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከተያዘዉ ንብረት ናሙና በመውሰድ በሚመለከተው አካል እንዲመረመር መመሪያ ዐቃቤ ሕጉ እንደሚሰጥ የገለጹት ዐቃቤ ሕጓ፤ የተያዘዉ ኤግዚቢት ከወንጀል ተግባሩ ጋር ተያያዥነት የሌለዉ ሆኖ ከተገኘ ንብረቱ ለባለንብረቱ እንዲመለስ መመሪያ በመስጠት የህጉን ተፈጻሚነት ያረጋግጣልም ብለዋል፡፡
ከዋስትና ጋር በተያያዘ የዐቃቤ ህግ ሚና
ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ ጋር በመሆን ተጠርጣሪ የተጠረጠረበት ወንጀል በወንጀል ሥነ-ሥርዐት ህጉ መሰረት ዋስትና የማያስከለክለው ከሆነ በዋስ እንዲለቀቅ በማድረግ፤ ዋስትና የሚያስከለክለው ከሆነ መርማሪ ፖሊስ በፍርድ ቤት ተገቢዉን ክርክር እንዲያደርግ ሊያሳዉቀዉ ወይም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፍርድ ቤት በመሄድ ተገቢውን ክርክር ሊያደርግ ይችላል ይላሉ፡፡ ዋስትና ማቅረብ ባልቻሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ህግ ምርመራው ተጠናቆ የምርመራ መዝገቡ በአስቸኳይ ውሳኔ እንዲያገኝ ጥረት ያደርጋል ያሉ ሲሆን ፖሊስ ከህግ ዉጭ በሆነ መንገድ ለተጠርጣሪ ዋስትና ከፈቀደ ወይም የዋስትና መብትን ከከለከለ ዐቃቤ ሕግ ድርጊቱ ስልጣንን አላግባብ መጠቀም በመሆኑ ለሚመለከተዉ አካል ምርመራ እንዲያጣራ በማሳወቅ አስፈላጊው እርምጃ እነዲወሰድ ያደርጋል ይላሉ፡፡
የምስክሮችን ቃል በመመርመርና በመመዘን ሂደት ውስጥ የዐቃቤ ህግ ሚና አጠራጣሪ፣
አሻሚና የሚጋጩ ማስረጃዎች ሲኖሩ ማስረጃዎቹን በድጋሚ አስቀርቦ የማጣራትና እንደ አስፈላጊነቱም ምስክሮች ተጨማሪ ቃል እንዲሰጡ በማድረግ ተጠርጣሪው እጅ ከፍንጅ ሳይሆን ከረጅም ጊዜ በኋላ በክትትል የተያዘ ከሆነ ተበዳይና ምስክሮች ተጠርጣሪውን ከሌሎች ሰዎች መሃል በአግባቡ የመረጡት ስለመሆኑና ተጨማሪ ቃላቸውን ስለመስጠታቸው ያረጋግጣል ሲሉ ዐቃቤ ህግ የምስክሮችን ቃል በመመርመርና በመመዘን ሂደት ያለውን ሚና ያብራራሉ ፡፡

ሰርጎ መግባትና ክትትል ማድረግ ሂደት ውስጥ የዐቃቤ ህግ ሚና ምን ይመስላል
ሰርጎ የመግባትና የክትትል ስራውን ሂደት መከታተል፣ ህጋዊነቱን በማረጋገጥና የሚሰበሰቡትም ማስረጃዎች ህጋዊና ተቀባይነት ያላቸዉ ስለመሆናቸው ያረጋግጣል ብለው ስለ ሰርጎ መግባትና ስለ ክትትል ማድረግ ሂደት አጠር ያለች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
መረጃ በሚስጥር ስለሚያቀብሉ ሰዎችና ወኪሎችን በተመለከተ የዐቃቤ ህግ ሚና
ዐቃቤ ሕግ መረጃን በሚስጥር የሚያቀብሉ ሰዎች ከዐቃቤ ህግ ወይም ከፖሊስ ጋር አብረው በመስራታቸው ምክንያት ራሳቸውም ሆነ የቅርብ ዘመዶቻቸው ለአደጋ እንደይጋለጡና ጥበቃ እንዲያገኙ ለሚኒስትሩ እንዲያመለክቱ በመጠቆም እንዲሁም ህጋዊ ችሎታ ለሌላቸው ጠቋሚዎች በራሱ እንደሚያመለክትና እና በሚኒስትሩ በተጠየቀ ጊዜም አስተያየት እንደሚሰጥ ይናገራሉ፡፡
ከቀዳሚ ምርመራ ጋር ተያያዘ የዐቃቤ ሕግ ሚና
ቀዳሚ ምርመራ የሚከናወነው በከባድ የወንጀል ጉዳዮች ምርመራ ተጠናቆ በዐቃቤ ህግ ክስ እስኪመሰረት ድረስ ምስክሮች አድራሻ በመቀየር፣ ቋሚ አድራሻ የሌላቸው በመሆኑ ማግኘት የማይቻል ከሆነ መሆኑን የተናገሩት ዐቃቤ ሕጓ ከሀገር በመውጣት ወይም ሞት በመሳሰለ ምክንያትም ላይገኙ እና ላይመሰክሩ የሚችሉበት ሁኔታ ካለ ወይም በእድሜ መጃጀት ምክንያት የምስክርነት ቃሉን የሚረሳበት ሁኔታ ይኖራል ተብሎ ከታመነ እንዲሁም ምስክርነቱን ለመስጠት በማያስችለው በሽታ የተያዘ እንደሆነ የማስረጃውን መጥፋት ለመከላከልና ማስረጃውን ጠብቆ ለማቆየት የሚደረግ የጥንቃቄ ስርዓት ነው ይላሉ፡፡ እነዚህ ስጋቶች በሚኖሩበት ጊዜ ዐቃቤህጉ ቀዳሚ ምርመራ የሚካሔድበትን ፍርድ ቤት በማስፈቀድ ቀዳሚ ምርመራ ያደርጋል ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ክቡራን ተከታዮቻችን ከዛሬው ጥንቅራችን ቁም ነገር እንዳገኛችሁበት ተስፋ በማድረግ ለነበረን ቆይታ ዐቃቤ ህጓን እያመሰገንን በቀጣይ ፕሮግራም እስክንገናኝ ቸር ተመኝን፡፡

ስለ ወክልና መሰረታዊ ጉዳዮች በኢትዮጵያ ህግ
መግቢያ
ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳዮቻቸውን በራሳቸው መፈጸም ወይም ማከናወን የማይችሉባቸው አጋጣሚዎች ጥቂት አይደሉም፡፡ይህም ሲሆን ሌሎች ሰዎች ጉዳያቸውን እንደነሱ በመሆን እንዲፈፅሙላቸው ሲያደርጉ ይስተዋለል፡፡ ጉዳዮቹ በተለይ ለምሳሌ ማህበራዊ(ለቅሶ መድረስ፣የተመመ ሰው መጠየቅ ወዘተ) ሳይሆን ህጋዊ ጉዳዮች ማድረግ( ሽያጭ ወይም ግዢ መፈፀም) ሲሆን በህግ የሚያስከተሉት እራሱን የቻለ ህጋዊ ውጤት ስለሚኖረው ስራዎችን የማከናወኑ ሀላፊነት ህግን መሰረት ባደረገ ስምምነት ላይ የተመሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡ስለሆነም ይህንን ስለሌላ ሰው ስራን የመስራት ሀላፊነት እና ግንኙነት የሚያስተዳድር ህግ እስፈላጊ ሆኖ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ይህንን ግንኙነት የሚገዛ ህግ በኢትዮጵያ ውክልናን የተመለከቱ ድንጋጌዎች በፍትህ ብሄር ህጉ 4ኛ መፅሀፍ አንቀፅ 14 ስር ስለ እንደራሴነት በጠቅላላ ክፍል እና ስለወኪልነት በሁለት አካቶ ይገኛል፡፡ ይሁንና የፍትሀ ብሄር ህጉ በእንደራሴነት እና በወኪልነት መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ ያብራራ ሆኖ አይታይም፡፡ በመሆንም እንደራሴነት እና ወኪልነት በህግ ባለሞያዎች ዘንድ በተለዋዋጭነት( interchangeably) በጥቅም ላይ ሲውሉ ይስተዋላል፡፡
በፍትሀ ብሄር ህጉ ቁጥር 2179 ስር እንደተደነገገው የሌላ ሰው እንደራሴ በመሆን ስራዎችን የመፈፀም ስልጣን የሚመነጨው ከህግ ወይም ከውል ነው፡፡ ለአካለ መጠን ላልደረሰ ልጅ ሞግዚት መሆን ወይም ንብረት ለማስተዳደር በሕግ የተፈቀደላቸው ጠባቂ ወይም አሳደሪ የመሆን የእንደራሴነት ስልጣን ለምሳሌ ከህግ የሚገኝ የውክልና ስልጣን ነው ፡፡ በሌላ በኩል አንድን የህግ ጉዳይ ጠበቃ ፍርድ ቤት ይዞ እንዲከራከርለት ባለጉዳይ ለጠበቃ የሚሰጠው የእንደራሴነት ስልጣን ደግሞ ከውል የሚገኝ የውክልና ስልጣን መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
የእንደራሴነት ስልጣን ወሰንን በተመለከተ የእንደራሴነት ሥልጣን የተገኘው በውል መሰረት የሆነ እንደሆነ ስልጣኑ የሚወሰነው በተዋዋዮቹ ስምምነት ነው፡፡ ይህም እንደራሴው ስራ እንዲሰራለት ሀላፊነት የሰጠው ሰው እንዲያከናውንለት ከጠየቀው ጉዳይ ወይም እንዲሰራ ከተስማሙት ስራ ውጪ መስራት አይችልም ማለት ነው፡፡ እንዲሁም እንደራሴው የተሰጠውን ሥልጣን ሦስተኛ ወገን ለሆነ ሰው አስታውቆ እንደሆነ በሦስተኛው ሰው ላይ ሥልጣኑ የሚፀናው ባስታወቀው ማስታወቂያ መሰረት ይሆናል፡፡ይህ ሲሆን የእንደራሴነት ስልጣን የሚተረጎመው ሳይስፋፋ በጠባቡ መሆን እንዳለበት የፍትሀ ብሄር ህጉ ይደነግጋል፡፡ በመቀጠል በፍትሀ ብሄር ህጉ ስለወኪልነት የተካተቱ መሰረታዊ ጉዳዮችን እንመለከታለን፡፡
የውክልና ትርጉም
ውክልና ማለት ተወካይ የተባለ አንድ ሰው ወካይ ለተባለው ሰው እንደራሴ ሆኖ አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ሥራዎች በወካዩ ሥም ለማከናወን ግዴታ የሚገባበት ውል ማለት ነው”(የፍትሀ ብሄር ህግ ቁጥር 2199)፡፡ ከትርጉሙ ለመረዳት እንደሚቻለው ውክልና ከውል የሚመነጭ የእንደራሴነት ስልጣን ሲሆን ውክልና የሚደረገው በወካይና በተወካይ መካከል በሚደረግ ስምምነት ነው፡፡ በተጨማሪም በውክልናው የሚከናወኑት ስራዎች ህጋዊ መሆን እንዳለባቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ህጋዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ለምሳሌ ወንጀል ለመፈፀም የሚደረግ የውክልና ስምምነት ተቀባይነት የለውም ማለት ነው፡፡
የውክልና አስፈላጊነት
አንድ ሰው አንዳንድ ተግባሮችን በራሱ ከማድረግ ይልቅ ሌላን ሰው በመወከል ተግባሮቹ እንዲከናወኑለት ሊፈልግ ይችላል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የጊዜ ጥበት፣ የቦታ ርቀት ወይም የሁኔታዎች አለመመቻቸት፣ የእውቀት ወይም የክህሎት አለመኖርና የችሎታ ማነስ ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ ሌሎችም በምክንያትነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
የውክልና ውል አመሰራረት
ውክልና በግልፅ (ማለትም ወካይ የውክልና ስልጣኑን ለተወካይ እንደሰጠው በግልፅ በማሳወቅ) ወይም በዝምታ ሊሰጥ ይችላል (expressly or impliedly) ፡፡ ተወካዩም ሊፈፅመው የሚገባው የሥራ ተግባር ስለአፈፃፀሙ በአንዳንድ ህጋዊ ፎርም ውስጥ እንዲገባ የሚያስፈልገው ሲሆን ውክልናው ለተወካዩ ሊሰጠው የሚገባው ይኸው ሕግ በሚያዘው ፎርም መሠረት ነው፡፡ ለምሳሌ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በፅሁፍ መሆን ካለበት ወኪሉ ሽያጩን እንዲያከናውንለት ወካይ የሚሰጠው የውክልና ሥልጣን ውል ከወዲሁ በፅሁፍ መሆን ይኖርበታል፡፡
በሌላ በኩል ውክልናውን የሚቀበለው ተወካይ መቀበሉን በግልፅ ወይም በዝምታ ሊፈጽም ይችላል፡፡ ውክልናውን መቀበል የማይፈልግ ከሆነ ደግሞ በግልፅ እንደማይቀበል በመግለፅ ከኃላፊነት እራሱን ማግለል ይችላል፡፡ ስለሆነም ተወካይ ውክልናውን የማይቀበል መሆኑን ከወዲሁ በግልፅ ካላስታወቀ በስተቀር የተወከለበት ነገር ከሚያካሂደው ሥራ ጋር ግንኙነት ያለው ጉዳይ መሆኑ በግለፅ የታወቀ ከሆነ፣ ወይም ከሙያ ሥራው አመራር ጋር የሚመሣሠል ጉዳይ ከሆነ፣ ወይም ይህንን የመሠለውን ጉዳይ ለመሥራት ፍቃደኛ ለመሆኑ በአደባባይ ገልጾ ሀሳብ በማቅረብ አስታውቆ እንደሆነ ውክልናውን እንደተቀበለ ይቆጠራል።
በመርህ ደረጃ አንድ ሰው ለቀረበለት ውል ምላሸ ሳይሰጥ ዝም ቢል የቀረበለትን የውል ሀሳብ እንደተቀበለ እንደማያስቆጥርበት (silence doesn’t amount to acceptance) የፍትሀ ብሄር ሕግ ይደነግጋል(ፍ/ብ/ህ/ቁ.1682)፡፡ ነገር ግን የውክልና ጉዳይ በልዩ ሁኔታ የሚወሠድ በመሆኑ አንድ ሰው በቀረበለት የውክልና ውል ላይ ግልፅ የሆነ ያለመቀበል ሃሣብ እስካላቀረበ ድረስ ዝምታው የውክልናውን ውል እንደተቀበለ የሚያስቆጥርበት መሆኑን የፍ/ብ/ህ//ቁ 2201(2) ደንግጓል፡፡ በዚህ ሁኔታ የውክልናው ውል ውክልናውን ባቀረበውና በተቀበለው ሰው መካከል ይመሠረታል ማለት ነው፡፡ ውክልናው የሚሰጠው ለብዙ ሰዎች ከሆነ ግን የውክልና ስልጣኑን ሁሉም ባንድነት መቀበላቸው ካልተረጋገጠ በቀር ውክልናው እንደጸና አይቆጠርም። በመሆኑም ውክልና ከላይ በተጠቀሱት ሁኔታዎች ይቋቋማል ማለት ነው፡፡
የውክልና ወሰን
ውክልናው ሲቋቋም የውክልናው ወሰን እስከምን ድረስ ነው የሚለው ደግሞ በፍትሃ ብሄር ህጉ ቁጥር 2202 ላይ ተቀምጧል። በዚህም መሠረት የውክልናው ወሰን በውሉ ላይ በግልፅ ተጠቅሶ ካልተቀመጠ በስተቀር ለውክልናው የሚሰጠው ወሰን እንደ ጉዳዩ አይነት ይሆናል። ወካዩ የውክልናውን ወሰን በውክልናው ውል ላይ በግልፅ ካስቀመጠ ደግሞ ወሰኑ በግልጽ በተቀመጠው መሠረት ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ውክልናው ለአንድ ልዩ ጉዳይ ወይም ለእያንዳንዱ ጉዳዮች ወይም ለወካዩ ጉዳዮች ሁሉ ጠቅላላ ውክልና ሊሆን ይችላል (ፍ/ብ/ህ/ቁ 2202 (2))። ይህ ማለት አንድ ሰው ለአንድ ለተወሠነ ጉዳይ ብቻ ወይንም ለተለያዩ ከአንድ በላይ ለሆኑ ጉዳዮች ወይንም ለሁሉም ጉዳዮቹ ውክልና ሊሰጥ ይችላል ማለት ነው፡፡ ስለሆነም ከላይ በተጠቀሰው የውክልና ወሰን መሠረት ውክልናን ጠቅላላ ውክልናና ልዩ ውክልና ተብሎ ይከፈላል ሊከፈል ይችላል፡፡
ጠቅላላ ውክልና

ጠቅላላ ውክልና ማለት በጠቅላላ አነጋገር የተደረገ ውክልና ሲሆን የአስተዳደር ሥራዎች ለመፈፀም ብቻ ለተወካዩ የሚሰጥ ውክልና ነው፡፡ ይህ ማለት ወካይ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በዝርዝር ሳይገለፅ እንዲሁ በጠቅላላ አነጋገር ወክየዋለሁ የሚል ከሆነ ተወካዩ ከአስተዳደር ሥራዎች ውጭ የመሥራት ሥልጣን አይኖረውም ማለት ነው። ይህም የሚሆነው ተወካዩ የተወከለበት ነገር ከሚያካሂደው ሥራ ጋር ግንኙነት ይኑረው አይኑረው መረዳት ባልተቻለበት ጊዜ ነው፡፡ ተወካዩ የተወከለበት ነገር ከሚያካሂደው ነገር ግንኙነት ካለው ግን ተወካዩ ከአስተዳደር ሥራዎች ይልቅ ከራሱ የዕለት ስራዎች ጋር የሚገናኘውን ሥራ ነው መስራት ያለበት። ስለዚህ ተወካዩ የሚተገብረው ሥራ ወካዩ ከወከለው ጉዳይ ጋር ያለውን ግንኙነት መረዳት ካልተቻለ ተወካዩ በተሠጠው ሥልጣን መሥራት የሚችለው የአስተዳደር ስራዎችን ብቻ ይሆናል፡፡
የአስተዳደር ሥራ ተብለው በፍትሀ ብሄር ህጉ የተቀመጡት ሥራዎች የሚከተሉት ናቸው( ፍ/ብ/ህ/ቁ. 2204)፡፡
የወካዩን ሀብት የማሰቀመጥ፣ የመጠበቅ ሥራ
ከሶስት አመት ለማያልፍ ዘመን የማከራየት
በብድር የተሰጠውን ሀብት የመሰብሰብ
ከሀብቱ የሚመጣውን ገቢ ተቀብሎ የማስቀመጥና
ለተከፈሉ ዕዳዎች ደረሰኝ የመሥጠት ሥራዎች ናቸው።
በመሆኑም በጠቅላላ ውክልና የውክልና ሥልጣን የተሰጠው ተወካይ ከላይ ከተዘረዘሩት ሥራዎች ውጭ የመሥራት ወይንም የመከወን ሥልጣን የለውም። በዚህ ጉዳይ ብዙ ጊዜ በህብረተሰቡ ዘንድ የተሳሳተ ግንዛቤ ይታያል ፡፡ይህም ስሙ ጠቅላላ ውክልና ስለሚል ብቻ ለተወካይ አጠቃላይ የወካዩን ተግባሮች የመከወን ሥልጣን የሰጠው አድርጐ የመረዳት ሁኔታ አለ፡፡ በዚህም ምክንያት ወካዮች ሁሉንም ሥራዎችን መወከል ሲፈልጉ ጠቅላላ ውክልና ወይም ሙሉ ውክልና ብለው የውክልና ስልጣን የመስጠት ሁኔታዎች ያጋጥማሉ። ይሁንና ጠቅላላ ውክልና ግን ሰዎች በሚያስቡት ወይም በሚገነዘቡት መልኩ ሳይሆን ህጉ ባስቀመጠው መሠረት የአስተዳደር ስራዎችን ብቻ የሚያካትት ነው።
ልዩ ውክልና
ልዩ ውክልና ማለት አንድ ሰው ከአስተዳደር ሥራ ውጭ ያሉ ሥራዎችን በወኪሉ ለማሠራት የሚያስችለው የውክልና አይነት ነው፡፡ ስለሆነም በልዩ ውክልና የውክልና ስልጣን የተሰጠው ተወካይ ተለይተው በዝርዝር የተመለከቱ ጉዳዮችንና እንደ ጉዳዩ አይነትና እንደ ልማድ አሰራር ከጉዳዩ ጋር ተከታታይነትና ተመሣሣይነት ያላቸው ነገሮችን ማከናወን ይችላል ማለት ነው( ፍ/ብ/ህ/ቁ 2206/1/)፡፡ ከዚህ ባሻገር አንድ ተወካይ ልዩ የውክልና ሥልጣን ከሌለው በስተቀር ሊፈጽማቸው የማይችላቸው ተግባራቶች አሉ፡፡ እነሱም፡-
• የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መሸጥ ወይም አሲዞ መበደር
• ካፒታሎችን በአንድ ማህበር ውስጥ ማስገባት
• የሀዋላ ሰነዶችን መፈረም (sign bill of exchange)
• መታረቅ
• ለመታረቅ ውል መግባት
• ስጦታ ማድረግ ወይም
• በአንድ ጉዳይ በፍርድ ቤት ቀርቦ መከራከር ናቸው።
በሌላ በኩል በፍትሀ ብሄር ህጉ ከተካተቱ መሰረታዊ ጉዳዮች ውስጥ የተወካይ እና የወካይ ግዴታዎች ይገኙበታል፡፡እነሱም፡-
የተወካይ ግዴታዎች
ጥብቅ የሆነ ቅንልቦና መኖር /ቅን የመሆን ግዴታ/
ታማኝነት
ሚስጥር ጠባቂነት /በውክልና ምክንያት ያገኘውን ሚስጥር የመጠበቅ ግዴታ/
የሂሳብ አያያዝና ሂሣብ የማቅረብ ግዴታ
ታታሪነት /ትጉህ የመሆን ግዴታ/
ስራን በራስ የመፈፀም ግዴታ/obligation to act personally/
የወካይ ግዴታዎች
ለተወካዩ ደሞዝ /የድካም ዋጋ/የመክፈል ግዴታ/ስምምነት ወይም ልማዳዊ አሠራር ካለ
ወጭ የመሥጠትና የማወራረድ ግዴታ
ተወካይን ከግዴታ ነፃ ማውጣት(ተወካይ ስለወካይ የውል ግዴታ ገብቶ ከሆነ ውሉን በመፈፀም ተወካይን በግዴታ ማውጣት)
ለተወካይ ኪሣራ መክፈል (የወካይን ስራ ሲሰራ ከተወካይ ጥፋት ውጪ ጉዳት ከደረሰበት ወካይ የካሣ ክፍያ የመክፈል ግዴታ አለበት)
የውክልና ስልጣንን አላግባብ መጠቀም
አንድ ተወካይ በተሰጠው የውክልና ስልጣን ሊሰራው ከሚገባው ተግባር ባሻጋር ሌላ ወካዩ እንዲሰራ የማይፈልገውን ተግባር ቢያከናውን ተወካዩ የተሰጠውን የውክልና ሥልጣን ያለአግባብ ተጠቅሟል ሊባል ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ተወካዩ የተጣለበትን አደራ በአግባቡ አለመወጣቱን ያሣያል፡፡ የተሰራውን ስራ በተመለከተ ደግሞ ወካዩ ተወካዩ የፈፀመውን ተግባር ማፅደቅ ወይም ውድቅ ማድረግ ይችላል ፡፡ እንዲሁም ተወካይ ጊዜው ባለፈበት የውክልና ሥልጣን የተገለገለ ወይም በተሻረ ውክልናው የሰራ እንደሆነ የተሰራውን ስራ ወካይ ሊያፀድቀው ወይንም ሊሽረው ይችላል( ፍትሃብሄር ሕግ ቀ. 2190/2/ ) ፡፡
ስለውክልና ሥልጣን መቅረት ወይም መቋረጥ
የውክልና ሥልጣን ከዚህ በታች በተቀመጡት ሶስት ምክንያቶች መሠረት ሊቀር ወይንም ሊቋረጥ ይችላል፡፡ እነሱም ፡-
1. የውክልናው ሥልጣን በወካዩ መሻር
2. የተወካዩ የውክልና ስልጣኑን መተው
3. የወካዩ ወይም የተወካዩ መሞት ፣ከአካባቢ መጥፋት ፣ለሥራት ችሎታ ማጣት ወይም በንግድ ኪሣራ ላይ መውደቅ ናቸው፡፡
በአጠቃላይ ውክልና በሰዎች የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ውስጥ የሚስተዋል ክንውን በመሆኑና የውክልና ህግ በኢትዮጵያ በብዛት የሚሰራበት ህግ በመሆኑ ሰዎች ስለውክልና ጠቅላላ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ጉዳዮች በተወካይ እንዲፈጸሙላቸው ሲያደርጉ ወክልና ከመስጠታቸው በፊት የውክልናን ውጤት ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡
ምንጭ፦ በፍትህ ሚኒስቴር የንቃተ ህግ፣ ትምህርተና ስልጠና ዳይሬክቶሬት