"የፈተናዎች ኤጀንሲ እና የትምህርት ሚኒስቴር ድርጊት አስተዳደራዊ በደል ነው" - የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም
የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የፈተናዎች ኤጀንሲ እና ትምህርት ሚኒስቴር በአዋጅ የተጣለባቸውን ኃላፊነት አለመወጣታቸው አስተዳደራዊ በደል ነው አለ፡፡ ተቋሙ በዛሬው እለት የፈተና ውጤታችን ተሳስቷል የሚል ጥያቄ ባነሱ ተማሪዎች ዙሪያ በሰጠው መግለጫ ተቋማቱ ቅሬታዎችን ተቀብለው ለመፍታት ከመጣር ይልቅ ‹አጣርተን ጨርሰናል›፣ ‹ጉዳዩ እኛንአይመለከተንም የሚሉ ምላሾች መስጠታቸው በአዋጅ ቁጥር 1183/2012 በተቀመጠው መሰረት አስተዳደራዊ በደል ነው ብሏል፡፡
የተፈታኝ ተማሪዎቹ ቤተሰቦች የጸጥታ አካባቢያቸውን የመከላከል ስራዎች ላይ መሳተፋቸው በተፈታኝ ተማሪዎች ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር መግለጫው አንስቷል፡፡ በትምህርት ሚንስትር በኩል ጉዳዩን በአግባቡ እና በጥሞና ሳይታይና ሳይፈተሽ በጥቅሉ ‹ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አወሳሰን ላይ የሚታይ ነገር የለም› በሚል መወሰኑ ተገቢ አለመሆኑንም ተቋሙ ገልጿል።
የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የቀረቡለትን አቤቱታዎችን መሰረት አድርጎ ባካሄደው ጥናት የደረሰበትን ግኝት በዛሬው ዕለት ይፋ በመግለጫው ይፋ አድርጓል፡፡ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ከተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ያለምንም ገደብ በአካልም ሆነ በኦንላይን መቀበልና በተገቢዉ የሰው ኃይል አማካይነት መፍታት አለበት ብሏል።
በተጨማሪም በጦርነት ወይም የፀጥታ ችግር የነበረባቸው አካባቢዎች ላይ የተፈተኑ ተማሪዎችን ተፅእኖ በመረዳት እና “ተቋማት የሚሰጡት ምላሽ በተማሪዎች ህመም ውስጥ ሆነው መሆን ስላለበት” የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤትን የትምህርት ሚኒስቴር ዳግም ዕንዲታይ ተቋሙ ጠይቋል።
ethio mereja
የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የፈተናዎች ኤጀንሲ እና ትምህርት ሚኒስቴር በአዋጅ የተጣለባቸውን ኃላፊነት አለመወጣታቸው አስተዳደራዊ በደል ነው አለ፡፡ ተቋሙ በዛሬው እለት የፈተና ውጤታችን ተሳስቷል የሚል ጥያቄ ባነሱ ተማሪዎች ዙሪያ በሰጠው መግለጫ ተቋማቱ ቅሬታዎችን ተቀብለው ለመፍታት ከመጣር ይልቅ ‹አጣርተን ጨርሰናል›፣ ‹ጉዳዩ እኛን
የተፈታኝ ተማሪዎቹ ቤተሰቦች የጸጥታ አካባቢያቸውን የመከላከል ስራዎች ላይ መሳተፋቸው በተፈታኝ ተማሪዎች ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር መግለጫው አንስቷል፡፡ በትምህርት ሚንስትር በኩል ጉዳዩን በአግባቡ እና በጥሞና ሳይታይና ሳይፈተሽ በጥቅሉ ‹ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አወሳሰን ላይ የሚታይ ነገር የለም› በሚል መወሰኑ ተገቢ አለመሆኑንም ተቋሙ ገልጿል።
የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የቀረቡለትን አቤቱታዎችን መሰረት አድርጎ ባካሄደው ጥናት የደረሰበትን ግኝት በዛሬው ዕለት ይፋ በመግለጫው ይፋ አድርጓል፡፡ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ከተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ያለምንም ገደብ በአካልም ሆነ በኦንላይን መቀበልና በተገቢዉ የሰው ኃይል አማካይነት መፍታት አለበት ብሏል።
በተጨማሪም በጦርነት ወይም የፀጥታ ችግር የነበረባቸው አካባቢዎች ላይ የተፈተኑ ተማሪዎችን ተፅእኖ በመረዳት እና “ተቋማት የሚሰጡት ምላሽ በተማሪዎች ህመም ውስጥ ሆነው መሆን ስላለበት” የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤትን የትምህርት ሚኒስቴር ዳግም ዕንዲታይ ተቋሙ ጠይቋል።
ethio mereja
የቀጠለ..........
የመግለጫው ሙሉ ቃል፡-
በሀገራችን መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበራቸውን ለመከታተል ይቻል ዘንድ የተለያዩ የዴሞክራሲ ተቋማት ተመስርተዋል፡፡ ከእነዚህ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ተልዕኮው ህገ- መንግስታዊ መርሆች በትክክል እንዲተገበሩ፣ ግልጽ የሆነ መንግስታዊ አስራር እንዲኖር ፣ዜጎች የመብታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑና መልካም የመንግስት አስተዳደር እንዲሰፍን ማስቻል ነው፡፡
ተቋሙም ይህንኑ ህገ- መንግስታዊ ተልዕኮ ለማሳካት ይችል ዘንድ በተሻሻለው የተቋሙ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1142/2011 ከተሰጠው ስልጣንና ተግባር መካከል አንዱ ዜጎች አስተዳደራዊ በደሎችን አስመልክተው የሚያቀርቧቸውን ቅሬታዎች ተቀብሎ በመመርመር የአስተዳደር ጥፋት የተፈጸመ መሆኑን ሲያረጋግጥ ተገቢውን የመፍትሄ ሀሳብ መስጠት ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ደግሞ በራስ ተነሳሽነት ምርመራ የማካሄድ ስልጣን እንዳለው አንቀጽ 7(2) ላይ በግልጽ ተደንግጓል፡፡
በዚህም መሰረት በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን አስመልክቶ ለተቋሙ የቀረቡ ጥቆማዎች እና በተለያዩ ሚዲያዎች ጉዳዩን አስመልክቶ የቀረቡ ዘገባዎችን መነሻ በማድረግ ችግሮችን በምርመራ በመለየት ተገቢውን የመፍትሄ ሃሳብ ለመስጠት በተደረገ የራስ ተነሳሽነት ምርመራ ሪፖርት መሰረት ተቋሙ ተከታዩን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ሀ. የቀረቡ አቤቱታዎችን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ምርመራና ግኝቶች
1 በፈተና ወቅት የተፈጠሩ የእርማት ስህተቶች በድጋሚ እንዲታይልን ቅሬታችንን ለፈተናዎች ኤጀንሲ ብናቀርብም ቅሬታችንን ተቀብሎ ሊያስተናግደን አልቻለም በማለት የቀረበውን ጥቆማ በተመለከተ ተቋሙ ባደረገው ምርመራ የፈተናዎች ኤጀንሲ የፈተና እርማትን አስመልክቶ ተማሪዎች ያቀረቡትን ቅሬታ በመቀበል ምላሽ መስጠቱን የገለጸ ቢሆንም የተቋሙ መርመሪዎች ለምርመራ ስራ በኤጀንሲው በተገኙበት ወቅት በርካታ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለማቅረብ በኤጀንሲው ቢገኙም ወደ ውስጥ ገብቶ ቅሬታን ለማቅረብም ሆነ ቅሬታቸውን ተቀብሎ ሊያስተናግዳቸው እንዳልቻለ ይልቁንም ቅሬታቸውን ለትምህርት ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ ተነግሯቸዋል፡፡
ቅሬታቸውን ይዘው ወደ በትምህርት ሚኒስቴር በመሄድ ለማቅረብ ጥረት ቢያደርጉም በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ጉዳዩ የሚመለከተው የፈተናዎች ኤጀንሲ ነው በሚል ቅሬታቸውን ሳይቀበል የቀረ መሆኑን እና በዚህ ምክንያትም ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅሬታቸውን ለማቅረብ መጥተው ለእንግልት እየተዳረጉ እንደሚገኙ የተቋሙ መርማሪዎች በቦታው በመገኘት አረጋግጠዋል፡፡
ማንኛውም ዜጋ በመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን ቅሬታ ለሚመለከተው አገልግሎት ሰጪ ተቋም የማቅረብ መብት እንዳለውና ቅሬታ የቀረበለት አካልም ቅሬታውን ተቀብሎ ያለምንም ገደብ ምላሽ የመስጠት ግዴታ እንዳለበት በፌደራል የአስተዳደር ስነ ስርዓትን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 20፣21፣22፣23 እና ተከታዮቹ መሰረት ግዴታ ያለበት መሆኑን በአዋጁ በግልጽ ተደንግጓል፡፡
ይሁን እንጂ የፈተናዎች ኤጀንሲ እና ትምህርት ሚኒስቴር በአዋጅ የተጣለባቸውን ሀላፊነት ከመወጣት ይልቅ ቅሬታዎችን አጣርተን ጨርሰናል እና ጉዳዩ እኛን አይመለከትም በሚሉ ተገቢ ባልሆኑ ምክንያቶች የተማሪዎችን ቅሬታ ለመቀበል ፍቃደኛ አለመሆናቸው ከአዋጅ ቁጥር 1183/2012 አኳያ አስተዳደራዊ በደል መሆኑን ተቋሙ አረጋግጧል፡፡
2 የሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ ለቀረቡለት ከ20,000 በላይ ቅሬታዎች ምላሽ የሰጠ መሆኑን ገልጿል፡፡ አብዛኛዎቹ ቅሬታዎች ደግሞ የቀረቡት በኦንላይ(online) ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለእነዚህ አቤቱታዎች የተሰጠው ምላሽ እንደቀረበው ቅሬታ አይነት በመለየት ሳይሆን ለሁሉም ቅሬታዎች ተመሳሳይ ምላሽ ማለትም ቅሬታው የታየ መሆኑን ብቻ የሚገልጽ ምላሽ ነው የሚሰጠው፡፡ ይህ አሰራር ደግሞ በአቤታታ አቅራቢዎች ላይ ቅሬታን የፈጠረ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
3. የ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በሁለት ዙር የተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይ የሁለተኛ ዙር ፈተና እርማት ላይ ስህተቶች የተፈጠሩ መሆኑን የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ በምርመራ ሂደት ወቅት ለተቋሙ መርማሪዎች አረጋግጧል፡፡ በተጨባጭም የእርማት ስህተት አለ በሚል ቅሬታ ካቀረቡ ተፈታኝ ተማሪዎች መካካል ድጋሚ እርማት በተደረገ ወቅት ስህተት የተፈጠረ መሆኑን ማሳያ ወይም ማረጋገጫ መሆን የሚችሉ የማስተካካያ እርማቶች እና ውጤቶች መከሰታቸው በእርማት ሂደቱ ላይ ችግሮች መፈጠራቸውን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች መሆናቸውን ተቋሙ አረጋግጧል፡፡
4. ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት የጦርነት እና የጸጥታ ችግሮች በነበረባቸው አካባቢዎች ፈተናውን የወሰድን ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ሊወሰንልን ይገባል በሚል የቀረበውን ጥቆማ በሚመለከት የትምህርት ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ለሚዲያ አካላት በሰጠው ምላሽ እንደገለጸው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ላይ በልዩ ሁኔታ ሊታይ የሚችል ጉዳይ እንደሌለ እና የመግቢያ ነጥቡ ላይ ማሻሻያ እንደማይደረግ አሳውቋል፡፡
ተቋሙ ጉዳዩን አስመልክቶ ባደረገው ምርመራ መገንዘብ እንደቻለው ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በተሰጠበት ወቅት በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በተለይም በአፋር፣አማራ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጦርነት እና የጸጥታ ችግሮች የነበሩ መሆኑ በመንግስት በይፋ የሚታወቅ ነው፡፡ ጦርነቱ እና የጸጥታ መደፍረሱን ለመከላከል ሕዝብ እና መንግስት በጋራ በርካታ ስራዎችን ያከናወኑ መሆኑ የቅርብ ጊዜ እውነታ ነው፡፡ በዚህ እንቅስቃሴ ወቅትም የተፈታኝ ተማሪ ቤተሰቦች በተለያዩ አግባቦች በእነዚህ የመከላከል ስራዎች ላይ ሲሳተፉ የነበሩ መሆኑና እነዚህ ጦርነትን እና የጸጥታ ችግሮችን የመከላከል ስራዎች በተፈታኝ ተማሪዎች ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ይህንን ጉዳይ በአግባቡ እና በጥሞና ሳይታይና ሳይፈተሸ በጥቅሉ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አወሳሰን ላይ የሚታይ ነገር የለም በሚል በይፋ በሚዲያ ውሳኔውን ማሳወቁ ከመልካም አስተዳደር መርሆች አኳያ ተገቢ የሆነ ውሳኔ አለመሆኑን ተቋሙ አረጋግጧል፡፡
ለ. በተቋሙ የተሰጠ የመፍትሄ ሀሳብ
1.ሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ የፈተና እርማትን አስመልክቶ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ከተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ተገቢውን ጊዜ ሰጥቶ ያለምንም ገደብ በአካል ፣ኦንላይን(online) የአቤቱታ ማቅረቢያ ጨምሮ ሁሉንም አማራጮች ተጠቅሞ አቤቱታዎች በመቀበል ተገቢውን የሰው ሀይል በመመደብ ለቅሬታዎቹ ግልጽ እና ምክንያታዊ ምላሽ እንዲሰጥ፡፡ በተለይ በኦን ላይን(online) ለቀረቡ አቤቱታዎች እየተሰጡ ያሉ ምላሾች በአግባቡ የታዩ እና ማጣራት የተደረገባቸው ስለመሆናቸው ተገቢው ቁጥጥር እንዲደረግባቸው፤
2.በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በሁለተኛ ዙር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች የፈተና እርማት ሂደት ላይ ስህተቶች የተፈጠሩ መሆኑ ይታወቃል ስለዚህ በሁለተኛው ዙር እርማት ተጨማሪ ስህተት አለመኖሩን ድርጅቱ በሚያረጋግጥበት ስርአት (verification) አረጋግጦ ለአቤት ባዮች አጥጋቢ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል፤ #አለ_ዜና

3.የትምህርት ሚንስቴር በጦርነት ወይም የጸጥታ ችግር በነበረባቸው አከባቢዎች የተመዘገበውን የተማሪዎች ዉጤት በአንጻራዊነት ሰላም በነበረባቸው አካባቢዎች ከተፈኑ ተማሪዎች ዉጤት ጋር ያለውን ልዩነት (Variation) ወይም ተቀራራቢነት በማየት እና በሚያገኘው ግኝት መሰረት የተማሪዎች ወደ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚያስገባው መቁረጫ ዉጤት ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ ዳግም ማየት የሚችልበት ሁኔታ ቢኖር ምክንያቱም ተቋማት የሚሰጡት ምላሽ በተማሪዎች ህመም ውስጥ ሆነው መሆን ስላለበት፡፡
"ዛሬ በዴሞክራሲያዊ ባህሪ ያላስተናገድነውን ትውልድ ነገ መብትህን በሰላማዊ ወይም በዴሞክራሲያዊ መንገድ ጠይቅ የማለት የሞራል ልዕልና አይኖረንም"
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም
#አለ_ህግ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
.......... #አለ_Share .........
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

የስራ መሪ ማለት በሕግ ወይም እንደድርጅቱ የሥራ ጠባይ በአሠሪው በተሰጠውየውክልና ሥልጣን መሠረት የሥራ አመራር ፖሊሲዎችን የማውጣትና የማስፈፀም ሥልጣን ያለው ወይም ሠራተኛን የመቅጠር፣ የማዘዋወር፣ የማገድ፣ የማሰናበት ወይም የመመደብ ተግባሮችን የመወሰን ሥልጣን ያለው ግለሰብ ሲሆን፣ እነዚህን የሥራ አመራር ጉዳዮች አስመልክቶ የአሠሪውን ጥቅም
ለመጠበቅ አሠሪው ሊወስደው ስለሚገባው እርምጃ በማንም ሳይመራ የራሱን የውሳኔ ሃሣብ የሚያቀርብ የሕግ አገልግሎት ኃላፊን እንደሚጨምር አዋጅ 1156/2011 አንቀፅ 2(10) ይደነግጋል፡፡
በተጨማሪም በአዋጅ 1156/2011 አንቀፅ 3(2)(ሐ) ድንጋጌ መሰረት የሥራ መሪ የሆነ ሰራተኛ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 1156/2011 ሳይሆን የሚዳኘው በፍትሐብሔር ሕጉ ነው፡፡ ከአንቀፅ 2550 ጀምሮ ይመልከቱ ::(ህግ አገልግሎት!

Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
የኑዛዜ ሰነዶችን የማረጋገጥና የመመዝገብ አገልግሎት ለማግኘት ወደተቋማችን ሲመጡ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
መረጃውን ለሌሎች እንዲደርስ በማድረግ ተቋሙ አላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት እንዲሁም ብልሹ አሰራር ለማስቀረት እያደረገ ያለውን ጥረት ያግዙ ፡፡
በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ (በፍ/ህግ ቁጥር/ 881 መሠረት፣) ለማድረግ
• የኑዛዜ ተጠቃሚውን ወይም ጉዳዩን በግልጽ የሚያመላክት በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የኑዛዜ ሰነድ፤
• ሁለት ምስክሮች፤ (ችሎታ ያላቸውና ተነቦላቸው/አንብበው የተስማሙ)
•የተናዛዥ እና የምስክሮች መታወቂያ፤
የኑዛዜ መሻሪያ (በፍ/ብ/ህግ/ቁጥር 898 መሰረት፣)
• በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የኑዛዜ መሻሪያ ሰነድ፤
• ሁለት ምስክሮች፤
• የኑዛዜ ሻሪው እና የምስክሮች መታወቂያ ፤
• ቀደም ሲል ተረጋግጦ የተመዘገበው የኑዛዜ ሰነድ፤
ኑዛዜን ለማድረግም ሆነ ለመሻር ሚወስደው ጊዜ 20 ደቂቃ ሲሆን የሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት ይደረግባቸዋል፡፡
• በኑዛዜ ሰነድ ውስጥ ተናዛዡ ኑዛዜውን ያደረገው በሙሉ ፈቃደኝነት እና አንብቦ ወይም ተነቦለት የተስማማ መሆኑ መገለጽ አለበት፡
• አንድ የኑዛዜ ጽሁፍ ላይ ኑዛዜ ማድረግ የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡
• አንድ ሰው ለተወካይ እንደ እኔ በመሆነ ኑዛዜ እንዲያደርግልኝ (እንዲናዘዝልኝ)፤ ኑዛዜውን አንዲለውጥልኝ ወይም እንዲሽርልኝ ብሎ ሌላን ሰው ለመወከል አይችልም፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለአካለ መጠን ላልደረሰ ልጅ ሞግዚት የሆነ ሰው አካለ መጠን ባልደረሰው ልጅ ስም ኑዛዜ ሊደርግ አይችልም፡፡
• በህግ የተከለከለ ሰው ኑዛዜ ለማድረግ ሙሉ ችሎታ አለው፡፡ ሆኖም በፍርድ የተከለከለ ሰው በፍርድ በተከለከለበት ጊዜ ኑዛዜ ለማድረግ አይችልም፡፡
#አለ_ህግ

በአዋጅ 1156/2011 የመብት ጥያቄ ስለሚቀርብበት የጊዜ ገደብ በተመለከተ በአንቀፅ 163 ስር የይርጋ ጊዜ ተቀምጧል፡፡
አንቀፅ 163(1) ስር የሚመለከተው በቅጥር ላይ ከተመሰረተ ግንኙነት የሚመነጭን ማንኛውንም አይነት ክስ ሲሆን በተለይም በአንቀፅ 163(3) አንቀፅ 163(4) ስር ከተመለከቱት ውጭ ያሉትን የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነቶችን ይመለከታል ፤ የጊዜ ገደቡም የመብቱን ጥያቄ ለማቅረብ ከሚቻልበት ቀን ጀምሮ እስከ 1 (አንድ) ዓመት ድረስ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡
በሌላ በኩል አንቀፅ 163(3) የሚመለከተው ሠራተኛን ብቻ ሲሆን ይኸውም ሠራተኛው የሚያቀርበው የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓት እና ሌሎች ከአሰሪና ሰራተኛ ጋር የተገናኙ ክፍያዎችን ነው፡፡ ይህ አንቀፅ በተለይም በስራ ላይ ያሉ እና የስራ ውላቸው ያልተቋረጠባቸው ነገር ግን የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓት እና ሌሎች ክፍያዎች ጋር በተያያዘ ከአሰሪ ጋር አለመግባባት ያላቸውን ሰራተኞችን በዋናነት የሚመለከት ነው፡፡ የጊዜ ገደቡም ጥያቄ መጠየቅ ከሚገባው ጊዜ ጀምሮ እስከ 6 (ስድስት) ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡
በመጨረሻም አንቀፅ 163(4) በዋናነት የሚመለከተው የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በሠራተኛውም ሆነ በአሠሪው የሚቀርብን ማንኛውም አይነት የክፍያ ጥያቄ ነው፡፡ የጊዜ ገደቡም የሥራ ውሉ በተቋረጠ በ 6 (ስድስት) ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡(ሕግ አገልግሎት)

በጊዜያዊነት የገቡ ዕቃዎች አገር ውስጥ የሚቆዩበት ጊዜ
*****
በጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀፅ 73 (በ1160/2006 እንደተሻሻለው) መሰረት በጊዜያዊነት የገቡ ዕቃዎች አገር ውስጥ የሚቆዩበት ጊዜ ከዚህ እንደሚከተለው ነው።
1) ከቱሪዝምና ከባህል ልውውጥ ወይም ከቴክኖሎጅ ሽግግር ጋር የተያያዙ ዕቃዎች ወደ አገር ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ተመልሰው መውጣት አለባቸው፤
2) ንግድ ለማስተዋወቅ የገቡ ዕቃዎች የማስተዋወቅ ተግባር በተጠናቀቀ በ2 ወር የጊዜ ገደብ ውስጥ መውጣት አለባቸው፤
3) ለግንባታ ሥራ፣ ለምክር አገልግሎት፣ ከእርዳታ ሥራ ጋር በተያያዘ ወይም በፕሮጀክት ስምምነት መሠረት ወደ አገር የገቡ ዕቃዎች በፕሮጀክቱ ስምምነት የተገለፀው የጊዜ ገደብ ሲጠናቀቅ ወይም ፕሮጀክቱ ወይም የእርዳታ ሥራው እንደተጠናቀቀ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ተመልሰው መውጣት አለባቸው፤
4) በጊዜያዊነት ወደ አገር ውስጥ የገባ ዕቃ በዚህ አዋጅ በተደነገገው የጊዜ ገደብ ተመልሶ ሊወጣ የማይችል መሆኑን አስመጪው ከጠየቀና በቂ ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠ ኮሚሽኑ የጊዜ ገደቡን ሊያራዝምለት ይችላል፤
5) በአዋጁ አንቀጽ 73 (4) መሠረት ዕቃው አገር ውስጥ የሚቆይበት ጊዜ ካልተራዘመ በስተቀር በሕግ የተወሰነው የመቆያ ጊዜ እንደተጠናቀቀ በ2 ወር ጊዜ ውስጥ ዕቃው ተመልሶ ከአገር መውጣት አለበት፡፡ ሆኖም ዕቃው ተመልሶ ከአገር ያልወጣ እንደሆነ በእርጅና ቅናሹ ላይ የሚከፈለው ቀረጥና ታክስ እንዲሁም አስተዳደራዊ መቀጫ ሲከፈል የተያዘው ዋስትና ተመላሽ ተደርጎ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ዕቃው ተመልሶ ከአገር እንዲወጣ ይደረጋል፤
6) ማንኛውም ቱሪስት ተሽከርካሪን ጨምሮ የያዘውን የግል መገልገያ ዕቃ፣ በዋስትና በማስመዝገብ በጊዜያዊነት ወደ አገር ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ ለዚህ ንዑስ አንቀፅ አፈፃፀም በሚኒስቴሩ (የገንዘብ ሚኒስቴር) ዝርዝር መመሪያ ሊያወጣ ይችላል፤
7) ወደ አገር ውስጥ የገባ ቱሪስት ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካልገጠመው ወይም የመቆያ ጊዜው ካልተራዘመለት በስተቀር በአዋጁ አንቀጽ 73 (1) በተለመከተው ጊዜ ውስጥ ተመልሶ ማውጣት ያለበት ሲሆን ዕቃውን ከአገር ያላስወጣ እንደሆነ ዕቃው ውርስ ተደርጎ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፤
8) ለዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (7) አፈፃፀም “ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት“ ማለት አግባብነት ባለው ማስረጃ የሚረጋገጥ ከባድ ህመም ወይም በህግ ቁጥጥር ሥር መዋል ወይም ከአገር እንዳይወጣ መታገድ ወይም የዕቃው መጥፋት ወይም መጎዳት እና ከነዚህ ጋር ተመሳሳይነት የሆነ ቱሪስቱ እንዳይመለስ የሚያደርግ ማንኛውም አስገዳጅ ሁኔታ ማለት ነው፤
9) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (1) የተመለከተው ቢኖርም ቱሪስቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር ፈቃድ ያገኘ እንደሆነ ወደ አገር ውስጥ ያስገባው ዕቃ የመኖሪያ ፈቃድ በተገኘበት ቀን ወደ አገር ውስጥ እንደገባ ተቆጥሮ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት በመፈፀም ቀረጥና ታክስ ከፍሎ ዕቃው አገር ውስጥ እንዲቀር ሊፈቀድለት ይችላል፤
10) በጊዜያዊነት ዕቃ ወደ አገር ውስጥ ያስገባ ሰው ዕቃውን ከአገር ለማስወጣት የማይችልበት በቂ ምክንያት ካቀረበ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት በመፈፀም በዕቃው ላይ ቀረጥና ታክሱን ከፍሎ ዕቃው አገር ውስጥ እንዲቀር ሊፈቀድለት ይችላል፤
11) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (10) የተመለከተው ቢኖርም ዕቃው አገር ውስጥ እንዲቀር የቀረበው ጥያቄ ዕቃው አገር ውስጥ እንዲቆይ የተፈቀደለት ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ከሆነ በዕቃው ላይ ሊከፈል የሚገባው ቀረጥና ታክስ መከፈሉ እንደተጠበቀ ሆኖ አስመጪው ያስያዘው ዋስትና ተመላሽ ተደርጎ የቀረጥና ታክሱን 25% በመቶ መቀጫ ከፍሎ ዕቃው አገር ውስጥ እንዲቀር ይደረጋል፤
12) በጊዜያዊነት ወደ አገር ውስጥ የገባ ዕቃ በዚህ አንቀፅ መሠረት ተመልሶ ከአገር ያልወጣ ወይም የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ተፈፅሞበት አገር ውስጥ እንዲቀር ያልተፈቀደለት እንደሆነ ዕቃው ይወረሳል፤
13) ለዚህ አንቀፅ አፈፃፀም “ቱሪስት” ማለት ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ኢትዮጲያ ውስጥ ለመቆየት ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ የውጭ አገር ዜጋ ሲሆን ለሥራ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባን ሰው አይጨምርም፤
/
በደንበኞች ትምህርት ቡድን
መጋቢት 13 ቀን 2014
ኮምቦልቻ፤

ኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር EWLA
የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በፌደራል ደረጃ በ1987 ዓ.ም በሴት የህግ ባለሙያዎች የተቋቋመ ፤ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተመዘገበ ሃገር በቀል የሲቪክ ማህበር ሲሆን ላለፉት ከ25 ዓመታት በላይ የሴቶችን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ሕጋዊ መብቶች እንዲታወቁ በማድረግ ሴቶች በሕገ-መንግስቱ እና በሌሎች ሕጎች በተመላከቱ መብቶቻቸዉ እንዲጠቀሙ የሚያግዙ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ፡፡
የማህበሩ ግብ ሴቶች በሁለንተናዊ ዘርፍ እኩል ተጠቃሚና ተሳታፊ እንዲሆኑ አስተዋፅኦ ማድረግ ሲሆን በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን መከላከልና ለሴቶች ከጥቃት የፀዳ አከባቢን መፍጠር አላማዉ አድርጎ በሶስት ፕሮግራሞቹ ማለትም የህግ ምርምር እና ጥናት፣ የህዝብ ማስተማርና አቅም ግንባታ እንዲሁም ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት በመስጠት ይሰራል፡፡ 👍👍👍👇👇👇👇👇👇👇
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ልዩልዩ #አለ_ችሎት #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በፌደራል ደረጃ በ1987 ዓ.ም በሴት የህግ ባለሙያዎች የተቋቋመ ፤ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተመዘገበ ሃገር በቀል የሲቪክ ማህበር ሲሆን ላለፉት ከ25 ዓመታት በላይ የሴቶችን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ሕጋዊ መብቶች እንዲታወቁ በማድረግ ሴቶች በሕገ-መንግስቱ እና በሌሎች ሕጎች በተመላከቱ መብቶቻቸዉ እንዲጠቀሙ የሚያግዙ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ፡፡
የማህበሩ ግብ ሴቶች በሁለንተናዊ ዘርፍ እኩል ተጠቃሚና ተሳታፊ እንዲሆኑ አስተዋፅኦ ማድረግ ሲሆን በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን መከላከልና ለሴቶች ከጥቃት የፀዳ አከባቢን መፍጠር አላማዉ አድርጎ በሶስት ፕሮግራሞቹ ማለትም የህግ ምርምር እና ጥናት፣ የህዝብ ማስተማርና አቅም ግንባታ እንዲሁም ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት በመስጠት ይሰራል፡፡ 👍👍👍👇👇👇👇👇👇👇
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ልዩልዩ #አለ_ችሎት #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
የዳግም ዳኝነት ጥያቄና የሰበር የህግ ትርጉም!
በፍ/ስ/ስ ህግ ቁጥር 6 መሰረት የዳግም ዳኝነት ጥያቄ ጉዳይ በይግባኝ ታይቶ ውሳኔ ከተገኘ በኋላም ቢሆን በድንጋጌው የተመለከቱት መመዘኛዎች ተሟልተው እስከተገኙ ድረስ መቅረብ እንደሚችሉ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል! ከዚህ በተጨማሪም አንድ ክስ በይርጋ መዘጋቱ ፍ/ስ/ስ ህግ ቁጥር 6 የተመለከቱት መስፈርቶች በተሟሉበት ሁኔታ የዳግም ዳኝነት ጥያቄን ላለማስተናገድ እንደበቂ ምክንያት የማይወሰድና በድንጋጌውም በመመዘኛነት ያልተቀመጠ ነው! (ቅፅ 19 ሰበር መዝገብ ቁ. 104028 እና ቅፅ 9 ሰበር መዝገብ ቁ. 43821)