አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የኢትዮጵያና የውጭ ሀገር ገንዘቦች መያዝ ላይ ያለው ገደብ እና የወንጀል ተጠያቂነት🔴
ገንዘብ እንደ ሀብት መለኪያ ሆኖ ከማገልገሉ ባለፈ የመገበያያ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ለዚህ እዲረዳ ሀገራት የየራሳቸው የሆነ ሕጋዊ ገንዘብ አላቸው፡፡ ይህን የራሳቸውንም ሆነ የሌላ ሀገር ገንዘብ ስለአያያዝና አጠቃቀሙ ምንዛሬን ጨምሮ የሚያስተዳድሩበት ሥርዓት ይዘረጋሉ፡፡ በዚህ አጭር ፅሑፍ የኢትዮጵያና የውጭ ሀገር ገንዘቦችን አያያዝ በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣው መመሪያን ማዕከል አድርገን ያሉት ገደቦች ምን እንደሚመስሉ ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

1. የገንዝብና የውጭ ሀገር ገንዘብ ምንነት

ቀደም ባሉት ጊዜያት ግብይቶች ሁሉ ቁስን በመለዋወጥ ወይም ዕቃን በዕቃ በቀጥታ መለዋወጥን (Barter System) መሰረት ያደረጉ ነበሩ፡፡ በዚህ ስርዓት ውስጥ ግብይት እጅግ ከባድ ስለሆነ ቀስ በቀስ ሌላ የግብይት ስርዓቱን የሚያቀላጥፍ በማስፈለጉ ምክንያት በራሳቸው ዋጋ ያላቸው ቁሶች ጉልህ ሚናቸውን መጫወት ጀመሩ፡፡ ለአብነት ወርቅ፣ ብር እና የመሳሰሉት ቁሶች በተፈጥሯቸው ከገንዘብነት ባለፈ ለሌላ ጉዳይ አገልግሎት ላይ መዋል የሚችሉ ናቸው፡፡ በሂደት ግን ይህም አሰራር ተቀይሮ ለብቻው በራሱ ገንዘብ ሆኖ ከማገልገል ውጭ ዋጋው ኢምንት የሆነ፤ መንግስታት አትመው ወይም አሳትመው ስርጭቱን እንዲሁም ተመኑን የሚያስቀምጡለት ስርዓት የተፈጠረ ሲሆን እነዚህም አሁን የምንገለገልባቸው የወረቀት ገንዘብና ሳንቲሞች ናቸው፡፡

የውጭ ሀገር ገንዘብ ምንነትን አስመልክቶ በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 በአንቀፅ 2(5) ሥር እንደሚከተለው ተተርጉሟል፡- “የውጭ ሀገር ገንዘብ ማለት ከኢትዮጵያ ገንዘብ በስተቀር ከኢትዮጵያ ውጭ በማናቸውም ሀገር ሕጋዊ ገንዘብ የሆነና በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረግ ክፍያ ተቀባይነት እንዳለው ብሔራዊ ባንክ ያሳወቀው ማናቸውም ገንዘብ ነው” ይላል፡፡ በዚህ ትርጉም መሰረት አንድ የውጭ አገር ገንዘብ በኢትዮጵያ ተቀባይነት እንዲያገኝ ሁለት መሰረታዊ ነገሮች ሟሟላት እንደሚጠበቅበት ይገልፃል፡፡ 1ኛ በሌላ ሃገር ህጋዊ የሆነ ገንዘብ መሆን አለበት፣ 2ኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ ለክፍያ ያሳወቀው መሆን አለበት የሚሉ መስፈርቶች ተቀምጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተቀባይነት እንዳላቸው ያሳወቃቸው ማለትም በቋሚነት በሕግ ተለይተው የታወቁ የውጭ ሀገር ገንዘቦች ባይኖሩም በየጊዜው ዋጋ እየተመነ የሚያወጣቸውና የተለመዱ የውጭ ሀገር ገንዘቦች አሉ፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ ከብሔራዊ ባንክ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው የሚከተሉት ገንዘቦች በወቅቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ለክፍያ እውቅና የተሰጣቸው ገንዘቦች ናቸው፡፡ እነዚህም የጃፓን የን፣ የኖርዌይ ክሮን፣ የስዊድን ክሮነር፣ የቻይና ይዋን፣ የዴንማርክ ክሮነር፣ የሳውዲ ሪያል፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ድርሀም፣ የአውስትራሊያ ዶላር፣ የካናዳ ዶላር፣ የአሜሪካ ዶላር፣ የሲውዘርላንድ ፍራንክ፣ የእንግሊዝ ፓውንድ እና የአውሮፓ ዩሮ ናቸው፡፡ ከነዚህ የገንዘብ ዓይነቶች ውጪ የሌላ ሀገር ገንዘብ ይዞ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ ተጠያቂነት የለበትም ማለት ነው፡፡

2. የውጭ ሀገር ገንዘብ የመያዝ ገደብ

ገደብና ክልከላው የተቀመጠው በመመሪያ ቀጥር FXD/49/2017 ሲሆን በውጭ ሀገር ገንዘቦች ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ብርም ላይ ጭምር ነው፡፡ በዚህ መመሪያ መሰረት ክልክላና ገደቡ በሁለት ተከፍሎ ተቀምጧል፡፡ ይኸውም ዜግነትን መሰረት ሳያደርግ የኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነና የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ በሚል የተከፈለ ነው፡፡ በዜግነት እና በነዋሪነት መካከል ያለው ልዩነት ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሚፈልግ ቢሆንም ባጭሩ ለመግለፅ ዜግነት በትውልድ ወይም በሕግ የሚገኝና በአንድ ሀገር እራሱን የቻለ ዜጋ ያልሆነ ሰው የማያገኘው መበትና ግዴታን የሚያሰጥ ግለሰብን ከሀገር ጋር የሚያስተሳስር (የሚያዛምድ) ሥርዓት ሲሆን ነዋሪነት ማለት ደግሞ ዜግነት ያለውም የሌለውም ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በአዋጅ ቁጥር 354/95 አንቀፅ 13-15 እና በደንብ ቁጥር 144/95 አንቀፅ 26-31 ባሉት ድንጋጌዎች መሰረት ነዋሪ ማለት ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ፈቃድ አግኝቶ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ሰው ማለት ነው፡፡

ክልከላውን በተመለከተ በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው በውጪ ሀገር በነበረው ጉዞ ምክንያት መጠኑ ከ1,000 (አንድ ሺ) የአሜሪካን ዶላር በላይ ወይም ለዚሁ ተመጣጣኝ የሆነ የውጭ ሀገር ገንዘብ በእጁ የያዘ ሰው ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ቅፅ አማካኝነት በአቅራቢያ ለሚገኝ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ማሳወቅ ወይም ዲክሌር ማድረግ እንዳለበት እና በ30 ቀናት ውስጥ ባንክ በመሄድ ወደ ኢትዮጵያ ብር መመንዘር እንዳለበት በመመሪያው አንቀፅ 4.1(a) እና 4.2 ሥር ተደንግጓል፡፡ መጠኑ ከ1,000 (አንድ ሺ) የአሜሪካን ዶላር ያነሰ ወይም ለዚሁ ተመጣጣኝ የሆነ የውጭ ሀገር ገንዘብ ይዞ ወደ ሀገር የገባ ሰው ምንም እንኳን በሕጉ የማሳወቅ ግዴታ ባይጣልበትም በ30 ቀናት ውስጥ ወደ ሕጋዊ ባንኮች ሄዶ ወደ ኢትዮጵያ ብር የመመንዘር ግዴታ አለበት፡፡

ከውጪ ሀገር የገባም ባይሆን በሆነ አጋጣሚ ማንኛውንም ያክል መጠን ያለው የውጪ ሀገር ገንዘብ ያለው ሰው ገንዘቡ በእጁ ከገባበት ወይም ለጉምሩክ ኮሚሽን ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ብር መመንዘር እንዳለበት በመመሪያው አንቀፅ 3 እና 4.2 (a) ላይ ተደንግጓል፡፡ የውጭ ሀገር ገንዘብ ያለው ሰው በባንክ ወደ ኢትዮጵያ ብር መመንዘር አለበት ብቻም ሳይሆን ከቀነ ገደቡ በላይ መያዝ እንደማይችል ወይም ክልክል እንደሆነ በመመሪያው ላይ ተደንግጓል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ ያልሆነ ሰውም ቢሆን ወደ ሀገር በሚገባበት ጊዜ ከ3,000 የአመሪካን ዶላር በላይ ወይም ለዚሁ ተመጣጣኝ የሆነ የሌላ ሀገር ገንዘብ የያዘ እንደሆነ በአየር ማረፊያዎች ወይም በሌሎች የመግቢያ በሮች ላይ ለሚገኝ የጉምሩክ ኮሚሽን ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው ቅፅ ላይ ሞልቶ የማሳወቅ ወይም Diclare የማድረግ ግዴታ እንዳለበት በመመሪያው አንቀፅ 4.1 (b) ሥር ተደንግጓል፡፡

በመመሪያው አንቀፅ 4.2 (c) መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ ያልሆነ ሰው ዲክሌር ያደረገውን የውጭ ሀገር ገንዘብ ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ባንክ ሄዶ ወደ ኢትዮጵያ ብር የመመንዘር ግዴታ አለበት፡፡ ቢሆንም እስከ የቪዛው (ቪዛ ማለት በኢትዮጵያ ነዋሪ ላልሆነ ሰው ለተወሰነ ጊዜ የሚሰጥ የመኖሪያ ፈቃድ ነው) ማለቂያ ጊዜ ድረስ ማቆየት እንደሚችል በአንቀፅ 4.2 (c) ተደንግጓል፡፡

3. የኢትዮጵያ ብር ላይ የተጣለ ገደብ

ከላይ በተጠቀሰው መመሪያ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው ከውጪ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ እና ከኢትዮጵያ ውጪ የሚሄድ ሰው ላይ እንጂ ማንኛውም ሰው ላይ የተጣለ ገደብ እንዳሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ወይም ከኢትዮጵያ የሚወጣ ማንኛውም ሰው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተወሰነው ወይም ከተፈቀደው መጠን በላይ የኢትዮጵያን ገንዘብ ይዞ ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት ወይም ለመውጣት እንደማይችል በአዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀፅ 18(6) ሥር ተደንግጓል፡፡ የተፈቀደው የገንዘብ መጠንን አስመልክቶ የመመሪያ ቁጥር FXD/49/2017 አንቀፅ 2.1 መሰረት ከውጪ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ሰውም ሆነ ከኢትዮጵያ ወደ ውጪ ሀገር የሚሄድ ሰው 1,000 (አንድ ሺ) በላይ ብር መያዝ እንደማይችል ተደንግጓል
በልዩ ሁኔታ ግን ወደ ጅቡቲ የሚጓዝ ሰው እስከ 4,000 ብር ድረስ ይዞ መጓዝ እንደሚፈቀድለት በመመሪያው አንቀፅ
2.2 ላይ ተደንግጓል፡፡

4. የገደቡ አስፈላጊነት

የመመሪያው መግቢያ “ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡና ከኢትዮጵያ የሚወጡ ሰዎች ላይ ብር የመያዝ መጠናቸው ላይ ገደብ ማድረግ በማስፈለጉ” እንዲሁም “የውጪ ሀገር ገንዘቦች አያያዝና አጠቃቃም ላይ ገደብና ቁጥጥር ማድረግ በማስፈለጉ…” መመሪያው እንደተዘጋጀ ከመገልፅ አልፎ የገደቡን አስፈላጊነት በግልፅ አላስቀመጠም፡፡ ሆኖም ካለው ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት የገደቡን አስፈላጊነት መገመት ይቻላል፡፡

አንደኛውና የመጀመሪያው ምክንያት ሀገሪቱ እየገጠማት ያለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ ገደቡ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለሚኖረው ነው፡፡ ምክንያቱም ተመዝግቦ የገባ የውጭ ሀገር ገንዘብ (ያልተመዘገበም ቢሆን) በገደቡ ምንክንያት ከ30 ቀናት በላይ በግለሰቡ እጅ ሊቆይ ስለማይችል ወደ ፋይናንስ ሥርዓቱ ገብቶ የውጭ ምንዛሬ ዕጥረቱን የማቃለል ሚናው ቀላል አይደለም፡፡

ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ገደቡ ሕገ-ወጥነትን ለመከላከል ሁነኛ መሳሪያ ሆኖ ማገልገል መቻሉ ነው፡፡ ሰዎች በህገ-ወጥ መንገድ ለምሳሌ በሙስና፣ ግብር በመደበቅ፣ በማታለል፣ በሥርቆት፣ በአራጣ ወዘተ ያገኙትን ገንዘብ ማስረጃ ለማጥፋትና ሕጋዊ ለማስመሰል የኢትዮጵያን ሕጋዊ መተላለፊያ ኬላዎችን ተገን አድርገው ሊገቡ ወይም ሊወጡ ይችላሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ማን፣ መቼ፣ የትና ምን ይዞ እንደተጓዘ ሥርዓት ያለው ገደብና ቁጥጥር የማይደረግ ከሆነ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ሕጋዊነት እንዲላበስና ሕገ-ወጥነት እንዲስፋፋ ያደርጋል፡፡

5. የወንጀል ተጠያቂነት

ለአንድ ሕግ ተፈፃሚ መሆን ክልከላና ገደብ ማድረግ ብቻውን በቂ የማይሆንበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ በመሆኑም በሕጉ የተቀመጡትን ክልከላና ገደቦች ተላልፎ የሚገኝን ሰው ተመጣጣኝና ፍትሐዊ ቅጣት ሊኖር የግድ ይላል፡፡ የመመሪያውን ድንጋጌዎች የሚጥሱ ሰዎች በአዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀፅ 26 መሰረት መቀጣት እንዳለባቸው በመመሪያው አንቀፅ 6 ላይ ተደንግጓል፡፡ ይህ ድንጋጌ ደግሞ በወንጀል ሕግ መሰረት ያስቀጣል ስለሚል በኢፌድሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 346 እና 354 መሰረት ወንጀሉ የተፈፀመበት ሀብት (ገንዘቡ) መወረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ ከ10 እስከ 15 ዓመት ፅኑ እስራት እና ከ50 እስከ 200 ሺ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ያስቀጣል፡፡

ምንጭ የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር
#አለ_ህግ #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_ስራ
#አለ_ልዩልዩ
#አለ_ችሎት
#አለ_ዜና
#አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና
#አለ_መረጃ
#አለ_ትምህርት
#አለ_ሁሉም
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩🟨🟥
COMMERCIAL CODE IMPLEMENTATION TRAINING.pdf
2.2 MB
for South Region
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩🟨🟥
contract 15.docx
27.7 KB
አስተያየቶችን እንቀበላለን
We welcome comments.
#አለ_ህግ #ALE_lawsocities
Dear @Berhanuworkie Congratulations.
You are rewarded 50 birr card for your great job sharing our channel for more than 200 peoples.
Pleas, send us your phone.
Dear @Berhanuworkie Congratulations.
You are rewarded 50 birr card for your great job sharing our channel for more than 200 peoples.
ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 2035(2)
እንወያይ...... 🙏
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ልዩልዩ #አለ_ችሎት #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Forwarded from BERHANU. W
አለ(ALE)law societies ለተሸለምኩት የሞባይል ካርድ ከልብ አመሠግናለሁ ።
ከ3 አመት በፊትም በውስጥ መስመር ለተሠጠኝ የህግ ትምህርት ምክር ማመስገኔ እንዳይረሳብኝ ። እግዚአብሔር ያክብርልኝ ።

Dear Customer, your prepaid account has been recharged succesfully.your Recharged balance is 50.00 Birr.your balance is 53.59 Birr.With this balance your account will expire on 19/09/2022.ethio telecom
የቤት ኪራይ ውል - አንኳር ነጥቦች
_

የውሉ ሥርዓት፡-
የቤት ኪራይ ውል ተዋዋይ ወገኖች፣ ማለትም አከራይ እና ተከራይ፣ በመረጡት ሥርዓት (በጽሑፍ ወይም በቃል) ሊደረግ ይችላል፡፡ ሕግ በጽሑፍም ሆነ በቃል ለሚደረጉ የቤት ኪራይ ውሎች እኩል ጥበቃ ይሰጣል፡፡

የኪራዩ መጠን እና የሚከፈልበት ጊዜ፡-
አከራይና ተከራይ በቤት ኪራይ ውል በስምምነት ከሚወስኗቸው ጉዳዮች መካከል የኪራዩ የዋጋ ልክ እና ኪራዩ የሚከፈልበት ጊዜ ይጠቀሳሉ፡፡ አከራይና ተከራይ በኪራይ ውሉ የኪራዩን የዋጋ መጠን እና ኪራዩ የሚከፈልበትን ጊዜ ካልወሰኑ፤ በፍትሐብሔር ሕጋችን የተቀመጡ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ የፍትሐብሔር ሕጋችን አንቀጽ 2950(2) አከራይና ተከራይ በውላቸው ውስጥ የኪራዩን የዋጋ መጠን ካላስቀመጡ ወይም በሚያጠራጠር ጊዜ የማዘጋጃ ቤት ባለሥልጣናት በወሰኑት ታሪፍ መሠረት ወይም የተወሰነ ታሪፍ የሌለ እንደሆነ የቦታዎቹን ልማድ በመከተል የኪራዩ የዋጋ መጠን እንደሚወሰን ይደነግጋል፡፡ በተመሳሳይ፣ አከራይና ተከራይ ኪራዩ የሚከፈልበትን ጊዜ በውላቸው ካልተወሰኑ ወይም ካልተስማሙ ተፈጻሚ የሚሆነው ደንብ በፍትሐብሔር ሕጋችን አንቀጽ 2951 ሠፍሯል፡፡ በዚሁ መሠረትም የቤት ኪራይ ውሉ ለአንድ ዓመት ወይም ለተወሰኑ ብዙ ዓመታት ተደርጎ እንደሆነ ኪራዩ በየሦስት ወር መጨረሻ የሚከፈል ይሆናል፡፡ ሆኖም የቤት ኪራይ ውሉ በጣም አጭር ለሆነ ጊዜ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ተደርጎ እንደሆነ በየወሩ መጨረሻ የሚከፈል ይሆናል፡፡

የተከራዩትን ቤት ስለማደስ፡-
በቤት ኪራይ ውል ሊወሰን ወይም ስምምነት ሊደረግበት የሚችለው ሌላኛው ጉዳይ የቤቱ እድሳት ነው፡፡ በፍትሐብሔር ሕጉ አንቀጽ 1954 መሠረት ማደስ የቤቱን መዝጊያዎችን ወይም መስኮቶችን፣ የቤቱን ወለሎችን ወይም ንጣፎችን፣ የውሃ መስመሮችንና የፍሳሽ ማስወገጃዎችን ማደስ እና ቤቱን የማፅዳት እና በደንብ የመያዝ ተግባሮችን ያጠቃልላል፡፡ ተከራይ ለማደስ የተዋዋለውን የተከራየውን ቤት በራሱ ኪሳራ (ወጭ) ለማደስ እንደሚገደድ በፍትሐብሔር ሕጋችን አንቀፅ 1953 ተደንግጓል፡፡ ሆኖም ግን ቤቱ በማርጀት ወይም ካቅም በላይ በሆነ ነገር የተበላሸ ሲሆን ተከራዩ ቤቱን የማደስ ስራ መፈፀም አይጠበቅበትም፡፡ ይሁን እንጂ በቤት ኪራይ ውሉ ውስጥ በማርጀት ወይም ካቅም በላይ በሆነ ነገር የተበላሹትንም ጭምር አድሳለው በማለት ተከራዩ የተስማማ ከሆነ እንዲያድስ ይገደዳል፡፡

የተከራዩትን ስለ ማከራየት (የኪራይ ኪራይ)፡-
ተከራይ የተከራየውን ቤት መልሶ ለማከራየት ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ተከራዩ የተከራየውን ቤት ሊያከራይ የሚችለው አከራዩ ለዚህ የኪራይ ኪራይ ተቃውሞ ከሌለው ብቻ ነው፡፡

የቤት ኪራይ ክፍያን በጊዜው አለመክፈል፡-
ተከራይ የቤት ኪራይ ክፍያውን በጊዜው ያልከፈለ እንደሆነ የሚያስከትለው ውጤት በፍትሐብሔር ሕጋችን አንቀፅ 2952 ሰፍሯል፡፡ የቤት ኪራይ ውሉ ለአንድ ዓመት ወይም ከአንድ ዓመት ለበለጠ ጊዜ ተደርጎ እንደሆነ አከራዩ የሠላሳ ቀን ማስጠንቀቅያ በመስጠት፤ የቤት ኪራይ ውሉ ለአጭር ጊዜ ተደርጎ እንደሆነ ደግሞ አከራዩ የአስራ አምስት ቀን ማስጠንቀቅያ በመስጠት፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ ተከራዩ ኪራዩን ያልከፈለ እንደሆነ አከራዩ ውሉን የሚያቆርጥ መሆኑን ለተከራዩ ያሳውቃል፡፡ በዚህ በተሰጠው የማስጠንቀቂያ ጊዜ ውስጥ ተከራዩ ያልከፈለ እንደ ሆነ አከራይ ውሉን ለማቋረጥ ይችላል፡፡

የቤት ኪራይ ውል የሚፈርስባቸው ምክንያቶች፡-
በአከራይና ተከራይ መካከል የተደረገ የቤት ኪራይ ውል በልዩ ልዩ ምክንያቶች ሊፈርስ ወይም ሊቋረጥ ይችላል፡፡ የቤት ኪራይ ውሉ ለተወሰነ ጊዜ ተደርጎ የውሉ ጊዜ ሲያበቃ፤ ተዋዋይ ወገኖች በስምምነት ውላቸውን ለማቋረጥ ሲስማሙ፤ ተከራይ ኪራዩን በጊዜው ባለመክፈሉ አከራዩ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሰጥቶት በዚህ ጊዜ ውስጥም ያልከፈለ እንደሆነ፤ አከራይ ቤቱን ፈልጎት ለተከራይ ማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት ወይም ተከራዩ ቤቱን መልቀቅ ፈልጎ ለአከራዩ ማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት የቤት ኪራይ ውል ሊቋረጥ ይችላል፡
👇#Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
"የፈተናዎች ኤጀንሲ እና የትምህርት ሚኒስቴር ድርጊት አስተዳደራዊ በደል ነው" - የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም

የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የፈተናዎች ኤጀንሲ እና ትምህርት ሚኒስቴር በአዋጅ የተጣለባቸውን ኃላፊነት አለመወጣታቸው አስተዳደራዊ በደል ነው አለ፡፡ ተቋሙ በዛሬው እለት የፈተና ውጤታችን ተሳስቷል የሚል ጥያቄ ባነሱ ተማሪዎች ዙሪያ በሰጠው መግለጫ ተቋማቱ ቅሬታዎችን ተቀብለው ለመፍታት ከመጣር ይልቅ ‹አጣርተን ጨርሰናል›፣ ‹ጉዳዩ እኛን አይመለከተንም የሚሉ ምላሾች መስጠታቸው በአዋጅ ቁጥር 1183/2012 በተቀመጠው መሰረት አስተዳደራዊ በደል ነው ብሏል፡፡

የተፈታኝ ተማሪዎቹ ቤተሰቦች የጸጥታ አካባቢያቸውን የመከላከል ስራዎች ላይ መሳተፋቸው በተፈታኝ ተማሪዎች ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር መግለጫው አንስቷል፡፡ በትምህርት ሚንስትር በኩል ጉዳዩን በአግባቡ እና በጥሞና ሳይታይና ሳይፈተሽ በጥቅሉ ‹ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አወሳሰን ላይ የሚታይ ነገር የለም› በሚል መወሰኑ ተገቢ አለመሆኑንም ተቋሙ ገልጿል።

የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የቀረቡለትን አቤቱታዎችን መሰረት አድርጎ ባካሄደው ጥናት የደረሰበትን ግኝት በዛሬው ዕለት ይፋ በመግለጫው ይፋ አድርጓል፡፡ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ከተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ያለምንም ገደብ በአካልም ሆነ በኦንላይን መቀበልና በተገቢዉ የሰው ኃይል አማካይነት መፍታት አለበት ብሏል።

በተጨማሪም በጦርነት ወይም የፀጥታ ችግር የነበረባቸው አካባቢዎች ላይ የተፈተኑ ተማሪዎችን ተፅእኖ በመረዳት እና “ተቋማት የሚሰጡት ምላሽ በተማሪዎች ህመም ውስጥ ሆነው መሆን ስላለበት” የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤትን የትምህርት ሚኒስቴር ዳግም ዕንዲታይ ተቋሙ ጠይቋል።
ethio mereja
በዩኒቨርሰቲ መግቢያ ፈተና እርማት ላይ ስህተት መፈጠሩን እንዳረጋገጠ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ፡፡

የ2013 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን አስመልከቶ በቀረበ ቅሬታና በተካሄደ ምርመራ መሰረት የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
#አለ_ህግ #አለ_ዜና #አለ_ትምህርት
የቀጠለ..........
የመግለጫው ሙሉ ቃል፡-

በሀገራችን መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበራቸውን ለመከታተል ይቻል ዘንድ የተለያዩ የዴሞክራሲ ተቋማት ተመስርተዋል፡፡ ከእነዚህ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ተልዕኮው ህገ- መንግስታዊ መርሆች በትክክል እንዲተገበሩ፣ ግልጽ የሆነ መንግስታዊ አስራር እንዲኖር ፣ዜጎች የመብታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑና መልካም የመንግስት አስተዳደር እንዲሰፍን ማስቻል ነው፡፡

ተቋሙም ይህንኑ ህገ- መንግስታዊ ተልዕኮ ለማሳካት ይችል ዘንድ በተሻሻለው የተቋሙ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1142/2011 ከተሰጠው ስልጣንና ተግባር መካከል አንዱ ዜጎች አስተዳደራዊ በደሎችን አስመልክተው የሚያቀርቧቸውን ቅሬታዎች ተቀብሎ በመመርመር የአስተዳደር ጥፋት የተፈጸመ መሆኑን ሲያረጋግጥ ተገቢውን የመፍትሄ ሀሳብ መስጠት ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ደግሞ በራስ ተነሳሽነት ምርመራ የማካሄድ ስልጣን እንዳለው አንቀጽ 7(2) ላይ በግልጽ ተደንግጓል፡፡

በዚህም መሰረት በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን አስመልክቶ ለተቋሙ የቀረቡ ጥቆማዎች እና በተለያዩ ሚዲያዎች ጉዳዩን አስመልክቶ የቀረቡ ዘገባዎችን መነሻ በማድረግ ችግሮችን በምርመራ በመለየት ተገቢውን የመፍትሄ ሃሳብ ለመስጠት በተደረገ የራስ ተነሳሽነት ምርመራ ሪፖርት መሰረት ተቋሙ ተከታዩን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ሀ. የቀረቡ አቤቱታዎችን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ምርመራና ግኝቶች

1 በፈተና ወቅት የተፈጠሩ የእርማት ስህተቶች በድጋሚ እንዲታይልን ቅሬታችንን ለፈተናዎች ኤጀንሲ ብናቀርብም ቅሬታችንን ተቀብሎ ሊያስተናግደን አልቻለም በማለት የቀረበውን ጥቆማ በተመለከተ ተቋሙ ባደረገው ምርመራ የፈተናዎች ኤጀንሲ የፈተና እርማትን አስመልክቶ ተማሪዎች ያቀረቡትን ቅሬታ በመቀበል ምላሽ መስጠቱን የገለጸ ቢሆንም የተቋሙ መርመሪዎች ለምርመራ ስራ በኤጀንሲው በተገኙበት ወቅት በርካታ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለማቅረብ በኤጀንሲው ቢገኙም ወደ ውስጥ ገብቶ ቅሬታን ለማቅረብም ሆነ ቅሬታቸውን ተቀብሎ ሊያስተናግዳቸው እንዳልቻለ ይልቁንም ቅሬታቸውን ለትምህርት ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ ተነግሯቸዋል፡፡

ቅሬታቸውን ይዘው ወደ በትምህርት ሚኒስቴር በመሄድ ለማቅረብ ጥረት ቢያደርጉም በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ጉዳዩ የሚመለከተው የፈተናዎች ኤጀንሲ ነው በሚል ቅሬታቸውን ሳይቀበል የቀረ መሆኑን እና በዚህ ምክንያትም ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅሬታቸውን ለማቅረብ መጥተው ለእንግልት እየተዳረጉ እንደሚገኙ የተቋሙ መርማሪዎች በቦታው በመገኘት አረጋግጠዋል፡፡

ማንኛውም ዜጋ በመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን ቅሬታ ለሚመለከተው አገልግሎት ሰጪ ተቋም የማቅረብ መብት እንዳለውና ቅሬታ የቀረበለት አካልም ቅሬታውን ተቀብሎ ያለምንም ገደብ ምላሽ የመስጠት ግዴታ እንዳለበት በፌደራል የአስተዳደር ስነ ስርዓትን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 20፣21፣22፣23 እና ተከታዮቹ መሰረት ግዴታ ያለበት መሆኑን በአዋጁ በግልጽ ተደንግጓል፡፡

ይሁን እንጂ የፈተናዎች ኤጀንሲ እና ትምህርት ሚኒስቴር በአዋጅ የተጣለባቸውን ሀላፊነት ከመወጣት ይልቅ ቅሬታዎችን አጣርተን ጨርሰናል እና ጉዳዩ እኛን አይመለከትም በሚሉ ተገቢ ባልሆኑ ምክንያቶች የተማሪዎችን ቅሬታ ለመቀበል ፍቃደኛ አለመሆናቸው ከአዋጅ ቁጥር 1183/2012 አኳያ አስተዳደራዊ በደል መሆኑን ተቋሙ አረጋግጧል፡፡

2 የሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ ለቀረቡለት ከ20,000 በላይ ቅሬታዎች ምላሽ የሰጠ መሆኑን ገልጿል፡፡ አብዛኛዎቹ ቅሬታዎች ደግሞ የቀረቡት በኦንላይ(online) ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለእነዚህ አቤቱታዎች የተሰጠው ምላሽ እንደቀረበው ቅሬታ አይነት በመለየት ሳይሆን ለሁሉም ቅሬታዎች ተመሳሳይ ምላሽ ማለትም ቅሬታው የታየ መሆኑን ብቻ የሚገልጽ ምላሽ ነው የሚሰጠው፡፡ ይህ አሰራር ደግሞ በአቤታታ አቅራቢዎች ላይ ቅሬታን የፈጠረ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

3. የ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በሁለት ዙር የተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይ የሁለተኛ ዙር ፈተና እርማት ላይ ስህተቶች የተፈጠሩ መሆኑን የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ በምርመራ ሂደት ወቅት ለተቋሙ መርማሪዎች አረጋግጧል፡፡ በተጨባጭም የእርማት ስህተት አለ በሚል ቅሬታ ካቀረቡ ተፈታኝ ተማሪዎች መካካል ድጋሚ እርማት በተደረገ ወቅት ስህተት የተፈጠረ መሆኑን ማሳያ ወይም ማረጋገጫ መሆን የሚችሉ የማስተካካያ እርማቶች እና ውጤቶች መከሰታቸው በእርማት ሂደቱ ላይ ችግሮች መፈጠራቸውን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች መሆናቸውን ተቋሙ አረጋግጧል፡፡

4. ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት የጦርነት እና የጸጥታ ችግሮች በነበረባቸው አካባቢዎች ፈተናውን የወሰድን ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ሊወሰንልን ይገባል በሚል የቀረበውን ጥቆማ በሚመለከት የትምህርት ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ለሚዲያ አካላት በሰጠው ምላሽ እንደገለጸው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ላይ በልዩ ሁኔታ ሊታይ የሚችል ጉዳይ እንደሌለ እና የመግቢያ ነጥቡ ላይ ማሻሻያ እንደማይደረግ አሳውቋል፡፡

ተቋሙ ጉዳዩን አስመልክቶ ባደረገው ምርመራ መገንዘብ እንደቻለው ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በተሰጠበት ወቅት በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በተለይም በአፋር፣አማራ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጦርነት እና የጸጥታ ችግሮች የነበሩ መሆኑ በመንግስት በይፋ የሚታወቅ ነው፡፡ ጦርነቱ እና የጸጥታ መደፍረሱን ለመከላከል ሕዝብ እና መንግስት በጋራ በርካታ ስራዎችን ያከናወኑ መሆኑ የቅርብ ጊዜ እውነታ ነው፡፡ በዚህ እንቅስቃሴ ወቅትም የተፈታኝ ተማሪ ቤተሰቦች በተለያዩ አግባቦች በእነዚህ የመከላከል ስራዎች ላይ ሲሳተፉ የነበሩ መሆኑና እነዚህ ጦርነትን እና የጸጥታ ችግሮችን የመከላከል ስራዎች በተፈታኝ ተማሪዎች ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ይህንን ጉዳይ በአግባቡ እና በጥሞና ሳይታይና ሳይፈተሸ በጥቅሉ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አወሳሰን ላይ የሚታይ ነገር የለም በሚል በይፋ በሚዲያ ውሳኔውን ማሳወቁ ከመልካም አስተዳደር መርሆች አኳያ ተገቢ የሆነ ውሳኔ አለመሆኑን ተቋሙ አረጋግጧል፡፡

ለ. በተቋሙ የተሰጠ የመፍትሄ ሀሳብ

1.ሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ የፈተና እርማትን አስመልክቶ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ከተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ተገቢውን ጊዜ ሰጥቶ ያለምንም ገደብ በአካል ፣ኦንላይን(online) የአቤቱታ ማቅረቢያ ጨምሮ ሁሉንም አማራጮች ተጠቅሞ አቤቱታዎች በመቀበል ተገቢውን የሰው ሀይል በመመደብ ለቅሬታዎቹ ግልጽ እና ምክንያታዊ ምላሽ እንዲሰጥ፡፡ በተለይ በኦን ላይን(online) ለቀረቡ አቤቱታዎች እየተሰጡ ያሉ ምላሾች በአግባቡ የታዩ እና ማጣራት የተደረገባቸው ስለመሆናቸው ተገቢው ቁጥጥር እንዲደረግባቸው፤

2.በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በሁለተኛ ዙር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች የፈተና እርማት ሂደት ላይ ስህተቶች የተፈጠሩ መሆኑ ይታወቃል ስለዚህ በሁለተኛው ዙር እርማት ተጨማሪ ስህተት አለመኖሩን ድርጅቱ በሚያረጋግጥበት ስርአት (verification) አረጋግጦ ለአቤት ባዮች አጥጋቢ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል፤ #አለ_ዜና