አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ባልና ሚስት በጋብቻቸው ውስጥ ያፈሩትን ንብረት የመካፈል መብታቸው '#ዘላለማዊ' ነው::
[በእርግጥ በቤተሰብ ሕጉ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ  ማቅረቢያ የጊዜ ገደብ በግልጽ አልተደነገገም:: እንደሚታወቀው እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ባጋጠመ ጊዜ ማለትም አንድ ሕግ ስለ አንድ መብት/ግዴታ መጠየቂያ (ክስ ማቅረቢያ) የጊዜ ገደብ በግልጽ ባልደነገገ ጊዜ ክፍተቱን ለመሙላት በፍ/ሕ 1676(1) እና 1845 የተመለከተው የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ተግባራዊ ይደረጋል::]

ይሁንና የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍልን አስመልክቶ በቤተሰብ ሕጉ የተፈጠረውን የይርጋ ጊዜ ክፍተት ከፍ/ሕ/ቁ. 1676(1) እና 1845 አኳያ ተርጉሞ በመሙላት "በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት የክፍፍል ጥያቄ ጋብቻው ከፈረሰበት ቀን ጀምሮ በ10 ዓመት ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል" የሚል ትርጉም መስጠት 'የተፋቾችን' ሕገ መንግሥታዊ የንብረት መብት የሚጥስ ስለሆነ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40(1፣ 7)፣ 50(5)፣ 55፣ 79(1)፣ እና 9(1) መሠረት ተፈጻሚነት የለውም::"👴🏽

↪️ፌደሬሽን ም/ቤት መ/ቁ. 77/12
↪️ሰኔ 3/2012 ዓ.ም.)
በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የመድኃኒቶች ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ ያግዛል የተባለዉ አዲስ መመሪያ ወጣ

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የመድኃኒቶች ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያግዝ አዲስ መመሪያ አውጥቷል።

"የባዮኤክቫለንስ ጥናት ማዕከል እና የባዮአናሊቲካል ላብራቶሪ ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 1043/2017" ተብሎ የሚጠራው ይህ መመሪያ፣ በገበያ ላይ የሚውሉ የመድኃኒት ምርቶች ተመሳሳይ የፈዋሽነት እና የደህንነት ደረጃዎችን ማሟላታቸውን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

በተለይም በጽንስ ስም የሚመረቱ መድኃኒቶች ከታወቁ የመድኃኒት ምርቶች ጋር ተመሳሳይ የሆነ የፈዋሽነት እና የደህንነት ደረጃ እንዲኖራቸው ለማድረግ ያለመ ነው።

ይህ መመሪያ "ባዮኢኩዊቫለንስ" የተሰኘ ልዩ ጥናት በማድረግ በጽንስ ስም የሚመረቱ መድኃኒቶች ከታወቁ የመድኃኒት ምርቶች ጋር ያላቸውን ተመሳሳይነት ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው ይደነግጋል።

በተጨማሪም፣ መመሪያው የመድኃኒት
ማምረቻ ተቋማትና ላቦራቶሪዎች ፈቃድና ቁጥጥር ላይ እንደሚያተኩር ካፒታል ለመረዳት ችሏል።

መመሪያው በኢትዮጵያ የመድኃኒት ቁጥጥር ላይ ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ለመድኃኒት ኢንዱስትሪው ዕድገት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። በተጨማሪም፣ ለሕዝብ ተደራሽና ጥራት ያላቸውን መድኃኒቶች ለማቅረብ ያለመ ነው ተብሏል።

Source: capitalethiopia
#Ethiopianbusinessdaily
ጋብቻ ከፈረሰ በኃላ (የንብረት ክፍፍል ከመደረጉ በፊት) የጋራ ንብረት የሆነን የማይንቀሳቀስ ንብረት (ቤት) አንደኛው ወገን ያለሌላኛው ፈቃድ በሽያጭ ያስተላለፉት ከሆነ የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69 (1) “ም” ሆነ (2) ድንጋጌዎች ለክርክሩ ተፈጻሚነት ሊኖራቸው የሚችልበት አግባብ አይኖርም፡፡ አግባብነት ያለው የጋራ ንብረትን ለማስተላለፍ የጋራ ባለሀብትን ፈቃድ የሚያስፈልግ ስለመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ.1266 የተመለከተው ድንጋጌ ነው።

የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69 የሚገኘው በቤተሰብ ሕጉ የጋብቻ ውጤትን በሚመለከተው ምዕራፍ ሦስት ክፍል ሦስት ስር ሲሆን ይህ ክፍልም ጋብቻው ጸንቶ በሚገኝበት ጊዜ በንብረት በኩል የሚያስከትለውን ሕጋዊ ውጤት የሚገዛ ነው፡፡

ዳሩ ግን፣ አንደኛው ወገን ቤቱን በሽያጭ ያስተላለፉት ጋብቻው ከፈረሰ በኃላ (የንብረት ክፍፍል ክፍፍል ከመደረጉ በፊት) ከሆነ ለጉዳዩ ተፈጻሚነት የሚኖረው የጋራ ባለሀብትነትን የሚመለከተው የፍ/ብ/ሕጉ ድንጋጌ ነው።

ይህ ከሆነ ደግሞ፣ አንደኛው ወገን በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ነው የሚለው ንብረት ላይ የተፈጸመው የሽያጭ ውል እንዲፈርስ ክስ ለማቅረብ የሚችለው በምን ያህል ጊዜ ውስጥ እንደሆነ በቤተሰብ ሕጉ ውስጥ በተለይ የተመለከተ ድንጋጌ ባለመኖሩ በዚህ ዓይነት ጉዳዮች ላይ ተፈጸሚነት ሊኖረው የሚገባው በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1677(1) ድንጋጌ መሰረት በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1845 ድንጋጌ የተመለከተው አጠቃላይ የአስር ዓመት የይርጋ ጊዜ ነው፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሚያዝያ 12 ቀን 2007 ዓ.ም በሰ/መ/ቁጥር 95338 የሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#We are hiring!
Nisir Law Firm wants to hire Advocate's Assistant.

Sex: Female
Qualification:
- obtained LL.B from a recognized university.
- good communication, writing and computer  skill.
- Apart from the Amharic language, having the skill of other languages is a plus.
Salary: by negotiation
Place of work: Around Kirkos Division FFIC, Addis Ababa.
Those of you who fulfill the requirements please send your cover letter and CV via telegram
@SileshiMequanint
የፈተና ውጤት ስለማሳወቅ
የማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፍቃድ ለማውጣት ታህሳስ 12 ቀን 2017ዓ.ም ፈተና ለወሰዳችሁ በሙሉ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ውጤታችሁ የተገለጸ ሲሆን ማለፊያ ውጤቱ ከመቶ ሀምሳ መሆኑን እንድታውቁ እና የፈተናው ውጤት ላይ ቅሬታ የሚኖራችሁ ከሆነ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ብቻ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
ጥልቅ የሕግ ትንታኔ እና አመክንዮ የተሰጠበትን የፌዴራሉ ጠቅላይፍርድ ቤት 1ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 258350 የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ

ሰበር ሰሚ ችሎቱ ዉሳኔ የሰጠበት ጉዳይ በአንድ ሀላፊነቱ የተወሰነ የንግድ ማህበር አባላት መካከል ብርቱ አለመግባባት ተከስቷል በሚል ማህበሩ እንዲፈርስ የቀረበን ክስ የሚመለከት ነው፡፡ 16 ገጾች ካሉት የሰበር ሰሚው ችሎት ውሳኔ ውስጥ 1ዐ ሩ ገጽ የሕግ ትንታኔ እና አመክንዮ የያዘ ነው፡፡ ውሳኔው የአገሪቱን ሕጎች: የአገር ውስጥ እና የውጪ ሐገር የሕግ ትንታኔ ጽሑፎችን: የሕግ መዝገበ ቃላቶችን እና የሐገራችን ምሁራን እና የሕግ ባለሞያዎች ጽሑፍችን በማጣቀሻነት ተጠቅሟል፡፡
በመጨረሻም ሰበር ሰሚ ችሎቱ ተፈጠረ የተባለው አለመግባባት ብርቱ ካለመሆኑ በተጨማሪ የማሕበሩ ዓላማ ከግብ እንዳይደርስ ሊያስተጓጉል የሚችል አለመሆኑ የተረጋገጠ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 181/6 አነጋገር መሠረት በአባላቱ መካከል የማሕበሩን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የማያስችል ብርቱ አለመግባባት ቢፈጠር እንኳን በቀሪ አባላት ማሕበሩ ዓላማውን ማሳካት የሚችልበት ሁኔታ ያለ እንደሆነ የተወሰኑት የማህበሩ አባላት ድርሻቸውን ይዘው ከማህበሩ እንዲወጡ ይደረጋል እንጂ ማህበሩ እንዲፈርስ መወሰን አይቻልም ከሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል፡፡ ሙሉውን የውሳኔውን ይዘት ከፍርድ ቤቱ ድሕረገጽ ማግኘት ይቻላል፡፡
በእትመት አሰፋ
#ፌዴራልጠቅላይፍርድቤት
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ድምጽ ብክለት።

ከፍተኛ ድምጽ እየለቀቁ ነው የተባሉ 50 የምሽት እና የቀን መዝናኛ ክበቦች መታሸጋቸው ተነግሯል፡፡

ድምፅ እየለቀቁ ተገኝተዋል የተባሉት ላይ 915 ሺ ብር ቅጣት ተላልፏል፡፡ 50 ቤቶች ታሽገዋል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በከተማ አስተዳደር ባለፉት 6 ወራት በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ባደረገዉ ድንገተኛ ኦፕሬሽን አብዛኞቹ ከተቀመጠዉ ስታንዳርድ በላይ ድምፅ እየለቀቁ ተገኝተዋል ሲል 9መቶ 15ሺ ብር ቅጣት መቅጣቱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጿል፡፤

ቅጣቱ ከተላለፈባቸው ተቋማት መካከል ባርና ሬስቶራንቶች፣ ግሮሰሪዎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ይገኙበታል ተብሏል።

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዲዳ ድሪባ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቁይታ እንደገለጹት፤ የድምፅ ልኬት ኦፕሬሽኑ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች መከናወኑን ገልጸው በተለይ ከነዚህ ተቋማት ከምሽት 3:00 ሰዓት በኋላ የሚለቁት ከፍተኛ የሆነ ድምፅ በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ችግር በፈጠሩ 50 ቤቶች ላይም የእሽግ እርምጃ ወስደናል ብለዋል።

የድምጽ ብክለት በርካታ የምሽት እና የቀን መዝናኛ ክበቦች እንደሚገኙባቸው ሲገለፅ ፤ የከተማዋ አካባቢዎች የተለያየ መልክ ቢኖረውም በመኖሪያ አካባቢዎች የሚገኙ ልዩ ልዩ የንግድና ኢንዱስትሪ ቤቶች በምሽቱ ክፍለ ጊዜ ከ 45 ዴቤ(DB) በላይ ድምጽ ማውጣት እንደ ድምጽ ብክለት የሚታይ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ምንጭ። ETHIO FM 107.8
#ethiopianarchitectureandurbanism
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Proclamation No- 1363-2017.pdf
8.7 MB
አዲሱ የነዳጅ ውጤቶቾ ግብይት አዋጅ 1363/2017

Petroleum Product Marketing Proclamation Number 1363/2024
Banking Business Proclamation No.1360_2025.pdf
12 MB
Punlished🅱anking Business Proclamation No.1360_2025.pdf