አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ድምጽ ብክለት።

ከፍተኛ ድምጽ እየለቀቁ ነው የተባሉ 50 የምሽት እና የቀን መዝናኛ ክበቦች መታሸጋቸው ተነግሯል፡፡

ድምፅ እየለቀቁ ተገኝተዋል የተባሉት ላይ 915 ሺ ብር ቅጣት ተላልፏል፡፡ 50 ቤቶች ታሽገዋል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በከተማ አስተዳደር ባለፉት 6 ወራት በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ባደረገዉ ድንገተኛ ኦፕሬሽን አብዛኞቹ ከተቀመጠዉ ስታንዳርድ በላይ ድምፅ እየለቀቁ ተገኝተዋል ሲል 9መቶ 15ሺ ብር ቅጣት መቅጣቱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጿል፡፤

ቅጣቱ ከተላለፈባቸው ተቋማት መካከል ባርና ሬስቶራንቶች፣ ግሮሰሪዎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ይገኙበታል ተብሏል።

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዲዳ ድሪባ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቁይታ እንደገለጹት፤ የድምፅ ልኬት ኦፕሬሽኑ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች መከናወኑን ገልጸው በተለይ ከነዚህ ተቋማት ከምሽት 3:00 ሰዓት በኋላ የሚለቁት ከፍተኛ የሆነ ድምፅ በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ችግር በፈጠሩ 50 ቤቶች ላይም የእሽግ እርምጃ ወስደናል ብለዋል።

የድምጽ ብክለት በርካታ የምሽት እና የቀን መዝናኛ ክበቦች እንደሚገኙባቸው ሲገለፅ ፤ የከተማዋ አካባቢዎች የተለያየ መልክ ቢኖረውም በመኖሪያ አካባቢዎች የሚገኙ ልዩ ልዩ የንግድና ኢንዱስትሪ ቤቶች በምሽቱ ክፍለ ጊዜ ከ 45 ዴቤ(DB) በላይ ድምጽ ማውጣት እንደ ድምጽ ብክለት የሚታይ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ምንጭ። ETHIO FM 107.8
#ethiopianarchitectureandurbanism