አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ጥልቅ የሕግ ትንታኔ እና አመክንዮ የተሰጠበትን የፌዴራሉ ጠቅላይፍርድ ቤት 1ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 258350 የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ

ሰበር ሰሚ ችሎቱ ዉሳኔ የሰጠበት ጉዳይ በአንድ ሀላፊነቱ የተወሰነ የንግድ ማህበር አባላት መካከል ብርቱ አለመግባባት ተከስቷል በሚል ማህበሩ እንዲፈርስ የቀረበን ክስ የሚመለከት ነው፡፡ 16 ገጾች ካሉት የሰበር ሰሚው ችሎት ውሳኔ ውስጥ 1ዐ ሩ ገጽ የሕግ ትንታኔ እና አመክንዮ የያዘ ነው፡፡ ውሳኔው የአገሪቱን ሕጎች: የአገር ውስጥ እና የውጪ ሐገር የሕግ ትንታኔ ጽሑፎችን: የሕግ መዝገበ ቃላቶችን እና የሐገራችን ምሁራን እና የሕግ ባለሞያዎች ጽሑፍችን በማጣቀሻነት ተጠቅሟል፡፡
በመጨረሻም ሰበር ሰሚ ችሎቱ ተፈጠረ የተባለው አለመግባባት ብርቱ ካለመሆኑ በተጨማሪ የማሕበሩ ዓላማ ከግብ እንዳይደርስ ሊያስተጓጉል የሚችል አለመሆኑ የተረጋገጠ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 181/6 አነጋገር መሠረት በአባላቱ መካከል የማሕበሩን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የማያስችል ብርቱ አለመግባባት ቢፈጠር እንኳን በቀሪ አባላት ማሕበሩ ዓላማውን ማሳካት የሚችልበት ሁኔታ ያለ እንደሆነ የተወሰኑት የማህበሩ አባላት ድርሻቸውን ይዘው ከማህበሩ እንዲወጡ ይደረጋል እንጂ ማህበሩ እንዲፈርስ መወሰን አይቻልም ከሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል፡፡ ሙሉውን የውሳኔውን ይዘት ከፍርድ ቤቱ ድሕረገጽ ማግኘት ይቻላል፡፡
በእትመት አሰፋ
#ፌዴራልጠቅላይፍርድቤት
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM