ባልና ሚስት በጋብቻቸው ውስጥ ያፈሩትን ንብረት የመካፈል መብታቸው '#ዘላለማዊ' ነው::
[በእርግጥ በቤተሰብ ሕጉ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ማቅረቢያ የጊዜ ገደብ በግልጽ አልተደነገገም:: እንደሚታወቀው እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ባጋጠመ ጊዜ ማለትም አንድ ሕግ ስለ አንድ መብት/ግዴታ መጠየቂያ (ክስ ማቅረቢያ) የጊዜ ገደብ በግልጽ ባልደነገገ ጊዜ ክፍተቱን ለመሙላት በፍ/ሕ 1676(1) እና 1845 የተመለከተው የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ተግባራዊ ይደረጋል::]
ይሁንና የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍልን አስመልክቶ በቤተሰብ ሕጉ የተፈጠረውን የይርጋ ጊዜ ክፍተት ከፍ/ሕ/ቁ. 1676(1) እና 1845 አኳያ ተርጉሞ በመሙላት "በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት የክፍፍል ጥያቄ ጋብቻው ከፈረሰበት ቀን ጀምሮ በ10 ዓመት ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል" የሚል ትርጉም መስጠት 'የተፋቾችን' ሕገ መንግሥታዊ የንብረት መብት የሚጥስ ስለሆነ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40(1፣ 7)፣ 50(5)፣ 55፣ 79(1)፣ እና 9(1) መሠረት ተፈጻሚነት የለውም::"👴🏽
↪️ፌደሬሽን ም/ቤት መ/ቁ. 77/12
↪️ሰኔ 3/2012 ዓ.ም.)