African Leadership Excellence Academy
2.17K subscribers
2.39K photos
90 videos
6 files
107 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#“ሱሉልታን_እንደ_ዳቮስ” #የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ከቀረጻቸው 13 ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን #የአመራር_ልማት_ማዕከሉን የዓለምአቀፍ ጉባኤ ማዕከል ለማድረግ የሚያስችል ነው።
አውሮፓውያን ችግር ሲገጥማቸው፤ ችግሮቻቸውን በጋራ ለመመከት፤ #የአውሮፓ_ማኔጅመንት_ኢንስቲትዩትን መስርተው ተሻግረዋል። ይህ ተቋም በጊዜ ሒደት አድጎና በልጽጎ ዳቮስ ላይ አድርሷቸዋል።
#በዳቮስ የማይፈቱ ችግሮች እንደሌሉ ይነገራል።
#አፍሪካዊ_ዳቮስን #በሱሉልታ ላይ ለማቋቋም ያስፈለገበትን ምክንያት #የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ፕሬዚደንት #ዛዲግ_አብርሃ እንዲህ ይገልጻሉ፦
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል #የአመራር_ልማት_ስርዓተ_ስልጠና ዝግጅትን በጋራ ገምግመዋል።
ግምገማው የተካሄደው የአካዳሚው የፕሮግራም ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ተወካይ #እሸቴ_አበበ /ዶ/ር/ እና የሪፎርም ኮሚቴ ሰብሳቢ #ሞገስ_ሎጋው /ዶ/ር/ እና የካሪኩለም ዝግጅት ቡድን ባሉበት ሲሆን፣ በግምገማውም በአፍሌክስና በኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል በትብብር የተዘጋጀው የአመራር ልማት ስርዓተ ስልጠና ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የተከናወነ መሆኑ ተጠቅሷል።
#ወንድወሰን_ካሳ ዶ/ር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል #የሰው_ኃይል_ልማት_ዳይሬክተር እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት የስርዓተ ስልጠና ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ለቫሊዴሽን ግምገማ /Validation Workshop/ የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይ ከቫሊዴሽን/ የሚገኘውን ግብዓት በማካተት ስርዓተ ስልጠናውን በበላይ ሃላፊዎች በማስጸደቅና ሞጁል በማዘጋጀት የአመራር ልማት ፕሮግራም ለማስጀመር የሚያስችል ስራዎች ማጠናቀቅ እንዲሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
ስለ አመራር ልማት ፕሮግራሙ እና ስለ አካዳሚው አገልግሎት አስተያየታቸውን ሰጥተውናል፡-
ወደ #አፍሌክስ ለአመራር ልማት ስመጣ ይህ ሶስተኛ ጊዜዬ ነው። ከአጠቃላይ የአመራር ልማት ተግባሩ ውጭ ከስራ ባልደረቦቼ ጋር እየተማማርን እና እየተወያየን የመጣንበትን ዓላማ ለማሳካት ትክክለኛ ቦታ ነው። ጥሩ ጊዜ እያሳለፍን ነው። ምግቡ፣ መኝታው፣ በአጠቃላይ መስተንግዶው ጥራቱን የጠበቀ ነው። እዚህ ፣ በአፍሌክስ ቆይታዬ ቤቴ ያለሁ ያህል ነው የሚሰማኝ።
ኤልያስ ኃይለ መስቀል
በገንዘብ ሚኒስቴር የብድር አስተዳደር ሲኒየር ኤክስፐርት
እዚህ በምንወስደው #የአመራር_ልማት ተጨማሪ ልምድ አዳብረን ወደ ስራችን ስለምንመለስ ገንቢ ነው። በአፍሌክስ ከመኝታው ጀምሮ ጊቢው በሙሉ ንጹህ እና ጽዱ ነው። አስተባባሪዎቹ የምንሰጣቸውን አስተያየት ተቀብለው በፍጥነት ተግባራዊ እያደረጉ ስለሆነ በጣም ጥሩ ነው።
ገነት ሸዋፈራው
በገንዘብ ሚኒስቴር የፐብሊክ ፋይናንስ ሪፎርም ባለሞያ
ይህ #የአመራር_ልማት በስራችን ብቁ እንድንሆን ያደርገናል። በቆይታችን ንጽህናው በተጠበቀ ስፍራ የተሟላ አገልግሎት እያገኘን ነው። #የአፍሌክስ ሰራተኞች ስለመኝታው፣ ስለምግቡ በአጠቃላይ ስለመስተንግዶው በቃልም በጽሁፍም በየጊዜው አስተያየታችንን እየጠየቁ ምቾታችንን ለመጠበቅ ጥረት እያደረጉ በመሆኑ ደስ ብሎኛል።
እሸቱ እስራኤል
በገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የልማት ድርጅቶች ክትትል ኤክስፐርት
#የአመራር_ልማት_ፕሮግራሙ ንድፈ ሃሳብን ከተግባራዊ ልምምድ ጋር አጣምሮ የያዘ ስለሆነ በስራችን ያለብንን ክፍተት እየሞላን እንድንሄድ ያስችለናል። የአመራር ልማቱ የመማሪያ ቁሳቁሶች የተሟሉበት በቴክኖሎጂ የታገዘ ነው። አካባቢው ብርዳማ ቢሆንም የመማሪያ፣ የመኝታ እና ሌሎች ክፍሎች በቂ ማሞቂያ ያላቸው የተስተናጋጅን ምቾት የሚሰጡ ናቸው። የተቋሙ መሰረተ ልማት እና አገልግሎት የሆቴል ደረጃ ያለው በመሆኑ እጅግ በጣም ጥሩ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
መቅደስ በላይ
በገንዘብ ሚኒስቴር የበጀት ዝግጅት እና አስተዳደር ባለሞያ