African Leadership Excellence Academy
2.17K subscribers
2.39K photos
90 videos
6 files
107 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ እድገት !!
ክቡር የኢፌዴሪ #ጠቅላይ_ሚኒስትር_ዐቢይ_አሕመድ (ዶ/ር) ስለ #አፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ምን አሉ?
የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ እድገት !! በሚል በቀረበው የከፍተኛ አመራር ስልጠና ላይ የስራ ቦታ፤ ኤርጎኖሚክስ፤ የተቋማት ግንባታና የመፈጸም ባህል በሚለው ገለጻ ስር ስለ ተሻጋሪ ተቋማት ይህን ብለዋል።
እንደ #አፍሌክስ ያሉ ተቋማት ለትውልድ የሚሻገሩ ናቸው። ጥርት ብለው፤ ትልቅ ሆነው፤ ኢትዮጵያን በሚመጥን መልኩ የተሰሩ ናቸው።
ስለ አመራር ልማት ፕሮግራሙ እና ስለ አካዳሚው አገልግሎት አስተያየታቸውን ሰጥተውናል፡-
ወደ #አፍሌክስ ለአመራር ልማት ስመጣ ይህ ሶስተኛ ጊዜዬ ነው። ከአጠቃላይ የአመራር ልማት ተግባሩ ውጭ ከስራ ባልደረቦቼ ጋር እየተማማርን እና እየተወያየን የመጣንበትን ዓላማ ለማሳካት ትክክለኛ ቦታ ነው። ጥሩ ጊዜ እያሳለፍን ነው። ምግቡ፣ መኝታው፣ በአጠቃላይ መስተንግዶው ጥራቱን የጠበቀ ነው። እዚህ ፣ በአፍሌክስ ቆይታዬ ቤቴ ያለሁ ያህል ነው የሚሰማኝ።
ኤልያስ ኃይለ መስቀል
በገንዘብ ሚኒስቴር የብድር አስተዳደር ሲኒየር ኤክስፐርት
እዚህ በምንወስደው #የአመራር_ልማት ተጨማሪ ልምድ አዳብረን ወደ ስራችን ስለምንመለስ ገንቢ ነው። በአፍሌክስ ከመኝታው ጀምሮ ጊቢው በሙሉ ንጹህ እና ጽዱ ነው። አስተባባሪዎቹ የምንሰጣቸውን አስተያየት ተቀብለው በፍጥነት ተግባራዊ እያደረጉ ስለሆነ በጣም ጥሩ ነው።
ገነት ሸዋፈራው
በገንዘብ ሚኒስቴር የፐብሊክ ፋይናንስ ሪፎርም ባለሞያ
ይህ #የአመራር_ልማት በስራችን ብቁ እንድንሆን ያደርገናል። በቆይታችን ንጽህናው በተጠበቀ ስፍራ የተሟላ አገልግሎት እያገኘን ነው። #የአፍሌክስ ሰራተኞች ስለመኝታው፣ ስለምግቡ በአጠቃላይ ስለመስተንግዶው በቃልም በጽሁፍም በየጊዜው አስተያየታችንን እየጠየቁ ምቾታችንን ለመጠበቅ ጥረት እያደረጉ በመሆኑ ደስ ብሎኛል።
እሸቱ እስራኤል
በገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የልማት ድርጅቶች ክትትል ኤክስፐርት
#የአመራር_ልማት_ፕሮግራሙ ንድፈ ሃሳብን ከተግባራዊ ልምምድ ጋር አጣምሮ የያዘ ስለሆነ በስራችን ያለብንን ክፍተት እየሞላን እንድንሄድ ያስችለናል። የአመራር ልማቱ የመማሪያ ቁሳቁሶች የተሟሉበት በቴክኖሎጂ የታገዘ ነው። አካባቢው ብርዳማ ቢሆንም የመማሪያ፣ የመኝታ እና ሌሎች ክፍሎች በቂ ማሞቂያ ያላቸው የተስተናጋጅን ምቾት የሚሰጡ ናቸው። የተቋሙ መሰረተ ልማት እና አገልግሎት የሆቴል ደረጃ ያለው በመሆኑ እጅግ በጣም ጥሩ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
መቅደስ በላይ
በገንዘብ ሚኒስቴር የበጀት ዝግጅት እና አስተዳደር ባለሞያ
"ባደጉ እና ባላደጉ ሃገራት መካከል ያለው ዋና ልዩነት የተቋም ግንባታ ነው!" ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
#አፍሌክስ አመራር ማለት ሃገር የሚመሩ ግለሰቦች ስብስብ ብቻ ሳይሆን በትውልድ ቅብብሎሽ ሃገርን በእድገት ጎዳና የሚያራምዱ ጠንካራ ተቋማት ግንባታም ጭምር ነው ብሎ ያምናል። 🌍
አብዛኞቹ የአፍሪካ ሃገራት ተቋማቶቻቸው እድገታቸውን በዘላቂነት ለማስቀጠልና ፈጠራን ለማበረታታት ብቁ ሳይሆኑላቸው ቀርተው ሲቸገሩ ይታያሉ።
የተቋም ግንባታ ላይ ትኩረት ባደረጉ ባለራዕይ መሪዎች የምትመራ፣ ዘላቂ ልማትን የሚያረጋግጡ ጠንካራ ተቋማት ያሏት አፍሪካን አስቡ! 🤔
#አፍሌክስ ይህንን ሃሳብ ወደተግባር ለመቀየር ጉዞ ጀምሯል!🚶‍♂️‍➡️🚶‍♂️‍➡️🚶‍♂️‍➡️
💪የአመራር ልማት መርሀ-ግብሮቻችን መሪዎች ጠንካራ ተቋማትን ለመገንባት ብሎም ለመምራት የሚያስችላቸውን ክህሎት ለማስታጠቅ የተቀረፁ ናቸው።
#አፍሌክስ የአፍሪካን ተቋማዊ ገጽታ ለመቀየር ይሰራል!🚀
🌍በጋራ ለበለጸገች አህጉር መሰረት እናኑር!