Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#Naharsí Malaak Dr. Abiy Acmad Awlaytit Maláh Buxal Reedah Xayyoyse Qusba Abnisa:
1. Demeke Mekonnen, Afâ Caagiidah Malaak,
2. Dr Abraham Bilay, Kalali Qandeh Malaak
3. Gifta Qumar Cuseen, Buqrê Malaak,
4. Gifta Malaaku Allebel - Sinaaqat Malaak,
5. Gifta Gebremeskel Chaala, Tellemmoo Kee Dariifâ Fantaaxawih Malaak,
6. Injineer Takkele Uma- Maqaadin Malaak
7. Ambasaader Naasise Chaali, Turiizim Malaak,
8. Gifti Muufarihaat Kaamil, - Taamaa Kee Duddí Malaak
9. Gifta Acmad Shide- Maaliyyah Malaak,
10. Gifta Laagew Ayyalew - Culentí Malaak,
11. Dr Fitsum Asfaw, - Ekraarô Dadfoosih Malaak,
12. Gifta Bellete Molla - Innovation Kee Teknoloojî Malaak,
13. Gifti Xagmaawit Moges - Merraytuu Kee Loojistiik Malaak,
14. Gifti Chaltu Saani, Magaalol Daddoosih Malaak,
15. Injineer Habtaamu Hitefa - Lee Kee Enerji Malaak,
16. Engineer Qeysha Macammad Muusa- Laqin Dariifaa Kee Efeq Daddoosih Malaak,
17. Dr. Birhaanu Negga, Barittô Malaak,
18. Dr. Liya Taxxase, Qaafiyat Dacayrih Malaak,
19. Dr. Ergoote Tesfaayo, Sayyoo Kee Ayyunyiinô Caagiidah Malask,
20. Gifta Gejeela Merxaasa, Qaadaa Kee Isportî Malaak,
21. Dr. Geexiyoon Timootiwoos, Qadli Malaak
22. Gifta Binnalf Anxu-alem, Salaam Malaak

#Walta
#ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና አዲስ ለተቋቋሙ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ዝርዝር ይፋ ሆነ፡፡

ሰመራ-መስከረም 26/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና አዲስ ለተቋቋሙ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ዝርዝር ይፋ ሆነ፡፡

በዚሁ መሠረትም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ለስራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ለፍትህ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ዝርዝር ይፋ ሆኗል፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ አስፈጻሚ አካላት
1. ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣
2. የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት፣
3. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣
4.የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣም፣
5. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣
6.የቤተ መንግስት አስተዳደር፣
7. የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣
8. የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣
9. የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣
10. የፋይናንስ ደህነነት አገልግሎት፣
11. አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣
12. የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን፣
13. የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ፣
14. የሪፐብሊክ ጥበቃ ሀይል፣
15. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት፣
16. የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣
17. የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣
18. የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን፣
19. የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን፣ (በቀጣይ የሚስተካከል)
20. የአስተዳደር ጉዳዮች፣የወሰንና ማንነት ኮሚሽን (በቀጣይ የሚስተካከል)።

የትራንስፖርት ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አካላት
1. የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን
2. የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን
3. የመድህን ፈንድ አገልግሎት
4. የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት

የከተማ መሰረተ ልት ሚኒስቴር ተጠሪ አካላት
1. የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት
2. የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን
3. የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን
4. የመንግስት የልማት ድርጅት ይዞታ

የገቢዎች ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አካላት

1. የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን

ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አካላት
1. የኢትዮጵያ ስታቲክስ አገልግሎት
2. የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት
3. የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
1. የኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
2. የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን
3. የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን
4. የኢትዮጵያ ምርት ገበያ

የማዕድን ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አካላት
1. የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት
2. የማዕድን ኢንዱስትሩ ልማት ኢንስቲትዩት

የቱሪዝም ሚኒስቴር ተጠሪ አካላት
1. የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን
2. የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ አካላት
1. የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት
2. የግብርና ቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ
3. የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
የገንዘብ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አካላት
1. የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ
2. የመንግስት ግዥ አገልግሎት

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አካላት
1. የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት
2. የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አካላት
1. የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት
2. የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት
3. የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት
4. የኢትዮጵያ አክሬዴሽን አገልግሎት
5. የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን
6. የኢትዮጵያ ምርት ገበያ

የግብርና ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አካላት
1. የኢትዮጵያ ግብርና ምርት ኢንስቲትዩት
2. የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት
3. የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን
4. የኢትዮጵያ ቡናና ሻ ይ ባለስልጣን
5. የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን
6. የእንስሳትና ጤና ኢንስቲትዩት
7. የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት
8. የኢትዮጵያ ደን ልማት
9. የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተጠሪ የሆኑ አካላት
1. የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ
2. የግል ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ


#Walta
#የአሸባሪ ቡድኑ ጥቃት ኢትዮጵያዊያን ቀፎው እንደተነካበት ንብ በጋራ እንዲቆሙ አድርጓል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናገሩ።

ሰመራ-መስከረም 28/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የአሸባሪ ቡድኑ ጥቃት ኢትዮጵያዊያን ቀፎው እንደተነካበት ንብ በጋራ እንዲቆሙ አድርጓል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳደሩ ይህን ያሉት አቶ ምህረተአብ ሙሉጌታ የተባሉ ባለሀብት በአፋር ክልል ችግር ለደረሰባቸው ዜጎች እንዲውል ያደረጉትን የግማሽ ሚሊየን ብር ድጋፍ በተረከቡበት መርኃግብር ላይ ነው።

አቶ ምህረተአብ ድጋፉን ያደረጉት ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የውስጥና የውጭ ፈተናዎች ለመቋቋም ለሚታገሉ የአፋር ልዩ ኀይልና ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ያላቸውን ክብር ለማሳየት መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው የአፋር ሕዝብ አሸባሪው የህወሓት ቡድን የጅቡቲን መስመር ለመዝጋት ያደረገውን እንቅስቃሴ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ባደረገው ተጋድሎ ቡድኑን ከስፍራው ማስወጣቱን አድንቀዋል።

"ለተፈናቀሉ ወገኖቼ ድጋፉን የማደርገው በኢትዮጵያዊነት መተባበር የገጠመንን ፈተና ለመወጣት ነው" ብለዋል። ይህን የፈተና ጊዜ ተጋግዘን ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ መውሰድ ይገባናልም ነው ያሉት።

በቀጣይም በሌሎች ክልሎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች አቅማቸው በፈቀደ መጠን ድጋፉን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

ባለሃብቱ ቀደም ሲልም በጥሬ ገንዘብና በቁሳቁስ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ለመከላከያ ሠራዊት ማድረጋቸው ተወስቷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው፣ ወጣቱ ባለሃብት በአዲስ መንግስት ምስረታ ማግስት ለክልሉ ሕዝብ በማሰብ የዜግነት ግዴታውን በመወጣቱ አድንቀዋል።

ግለሰቦችና ተቋማት ለችግር የተጋለጡ የአፋር ወገኖችን ለመርዳት እያደረጉት ላለው ድጋፍም አመስግነዋል።

"የኢትዮጵያ ትልቁ ወዳጇ ውስጣዊ አቅሟ ነው" ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ "ትልቁ ጠላቷ ደግሞ ድክመቷ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

አሸባሪው ቡድን አገር የመምራት ዕድል አግኝቶ እንኳን ራሱን ነፃ አውጪ አድርጎ እንደሚጠራ ያስታወሱት አቶ አወል፣ ቡድኑ የኢትዮጵያ ጠላት መሆኑን ሁሉም ዜጋ መረዳት አለበት ብለዋል።

ለትግራይ ክልል ሕዝብ ያልሆነ ኃይል ለሌላውም እንደማይበጅ ገልፀው፣ ሕዝቡን ለረሃብ መዳረጉን፣ ትግራይን ማፍረሱን፣ ታዳጊዎችንም ለጦርነት እየማገደ መሆኑን አንስተዋል።

ቡድኑ ወጣቶችን እየጨረሰ የ'አሸንፈናል' የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ቢሆንም ሲያልመው ከነበረው አፋር ምድር እንዲወጣ መደረጉን ገልፀዋል።

የአፋር ህዝብ በአገሩ አንድነትና ሕልውና እንደማይደራደር ገልፀው፤ ቡድኑ አፋርን ተጠቅሞ ኢትዮጵያን ለማፍረስ አልሞ እንደነበር፤ በሕዝቡና በመከላከያ ሠራዊቱ ሕልሙ በአጭር መቀጨቱን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የአሸባሪ ቡድኑ ጥቃት ኢትዮጵያዊያን ቀፎው እንደተነካበት ንብ በጋራ እንዲቆሙ አድርጓል ያሉት አቶ አወል የሽብር ኃይሉ እንዲደመሰስ ጥረታችን ይቀጥላል፤ አንዘናጋም ብለዋል።

#Walta
#ለትግራይ ክልልና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አዲስ ምደባ ልደረግ ነው፣፣

ሰመራ-ጥቅምት 9/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ለትግራይ ክልልና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አዲስ ምደባ ልደረግ ነው፣፣

በአሸባሪው ሕወሓት ቡድን በተፈጠረው ችግር ምክንያት በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በየኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲ በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገፅ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡

በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከዛሬ ጀምሮ መመዝገብ እንደሚችሉ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለመመዝገብ https://forms.gle/wYpZtTqpdQ417Bxx8 በመጠቀም የተቀመጠውን ፎርም እንዲሞሉ እና ምዝገባ እንዲያካሂዱ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡


#Walta
#የፌደራል መንግሥት መግለጫና ጥሪ፣፣

ሰመራ-ጥቅምት 12/2014 (አፍ.ብ.መ.ድ)

የፌደራል መንግሥት መግለጫና ጥሪ፣፣

ሕብረተሰቡ የሕወሓትን የሽብር ቡድን እኩይ ዓላማና እቅድ በመረዳት አገርን ለመበታተን የተነሳውን የጥፋት ኃይል ሴራ እንዲያከሽፍ መንግሥት ጥሪ አቀረበ፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል።

ሙሉ መግለጫው ቀጥሎ ቀርቧል:-

አሸባሪው የትሕነግ ቡድን ደሴ ከተማን ዒላማው አድርጎ የሚያቅዳቸው በርካታ የጥፋት ሥራዎች መኖራቸው የሚታወቅ ነው።

በሁሉም ግንባሮች በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን፣ በአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ እንዲሁም ለህልውናቸው በተሰለፉት የክልሉ ወጣቶች የሚደርስበት ከባድ ኪሳራ ሩቅ እንደማያስኬደው ግልጽ ሆኗል።

የደሴ ከተማ ላይ ያቀደው ጥፋትም ይህንኑ ሽንፈቱን በጥፋት ሥራ ለመሸፈን ማቀዱን ያሳያል። ኅብረተሰቡም የዚህን ሽብር ቡድን እኩይ ዓላማና እቅድ በመረዳት ሀገርን ለመበታተን አቅዶ የተነሳውን የጥፋት ኃይል ሴራ ማክሸፍ ይገባዋል።

የሽንፈት ገፈትን እየቀመሰ የሚገኘው የሽብርተኛው ቡድን በደሴ ብዙ ሠራዊት ሊኖር ይችላል በሚል በተጨማሪም ፋኖ የከተማ የውጊያ ስልትን ለማካሄድ ሊዘጋጅ ይችላል የሚል ግምትን በማሳደር ሰርጎ ገቦችን በመጠቀም በከተማዋ የመብራት መስመሮችን ለማቋረጥ እና በደሴ የሚገኘው የፀጥታ ኃይል ላይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናን ለማሳደር ማቀዱን የሚያሳዩ መረጃዎች ወጥተዋል።

በከተማዋ የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊትም ኾነ የክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ከመረጃ እንዲርቅ ማድረግንም በእቅዱ ይዟል። ሐሰተኛ መረጃዎችንና ምስሎችን በስፋት በማሰራጨትም የሠራዊቱንና አጠቃላይ የፀጥታ ኃይሉን ሞራል ለማዳከም ያስችሉኛል በሚል የያዛቸው እቅዶች መኖራቸው ተደርሶበታል።

ይህ የጥፋት ቡድን ሀገርን ማሸበር ዋና ዓላማው መሆኑን የሚያሳይ ነው። የአማራ ክልል ሕዝብና መላው ኢትዮጵያውያን የሽብር ቡድኑ ትህነግ ያቀዳቸውን የማወናበጃና የኅብረተሰቡን ኢኮኖሚና ማኅበራዊ ተግባራት የማወክ እንቅስቃሴን ቀድሞ በመረዳት ሰርጎ ገቦችን በማጋለጥና አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ እንደስካሁኑ ጠንካራ ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል መንግሥት መልእክት ያስተላልፋል።

#Walta
#የደሴ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት የሞተር እና ባለ3 እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መወሰኑ ተሰማ።

ሰመራ-ጥቅምት 14/2014 (አፍ.ብ.መ.ድ)

የደሴ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት የሞተር እና ባለ3 እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መወሰኑ ተሰማ።

ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበረው ውሳኔ እስኪነሳ ወይም እስኪሻሻል ሞተር ሳይክሎች እና ባለ3 እግር ተሽከርካሪዎች በየትኛውም ሰዓት ከተማዋ ላይ መንቀሳቀስ አይችሉም።

ውሳኔው የተላለፈው የደሴ ከተማን ፀጥታና ደኅንነት ለማስጠበቅና የአሸባሪውን ሕወሓት ሰርጎ ገቦች ለመቆጣጠር እንዲቻል በሚል መሆኑን የደሴ ከተማ አስተዳደር ለዋልታ ገልጿል።

ንግድ ቤቶች በተለይም መድኃኒት ቤቶች በአስቸኳይ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ የፀጥታ ምክር ቤቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ውሳኔውን በማያከብሩ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድም ምክር ቤቱ አስጠንቅቋል።

#Walta
#Xesê Magaalak Saay Malah Buxa Sidiica Iba-lee Kee Motooritte Angayye Waytay inta margaqa Tatrusse.

Samara-Kaxxa garabluk 14, 2014 (AFMMA)

Xesê Magaalak Saay Malah Buxa Sidiica Iba-lee Kee Motooritte Angayye Waytay inta margaqa Tatrusse.

Walta TV tatrusseh tan tama Xaagi elle yascassennal Dessê Magaalak Saay Malah Buxa tama margaqat kah temeetem Juntâ Qarkakisaa Kee ken farmoytit Bajaajittee Kee Motoorittet dooqaysimak abtam dudda umaaneena Kee Qarkakisso Lowsiisoonuu kee salcisoonu kinnim timixxigeh tan.

Asaakih ayrok Xabba haanam abbinowtaamih afkan kak yeceen tama margaqa duugumee Kee Isiisa edde takkem Kee taamal sugelem timixxigeh tan.

Tah tannal anuk, Inkih tan Tellemmô Buxaaxiiy baxsaluk Diwaatâ Buxaaxi Sissikuk taama Qimmissam faxxintam tescesseh tan tama margaqa yumcuwwee afkan abbinoose wannan dagaral maaqatta gexelem kassisse.

#Walta
#የአገር መከላከያ ሰራዊት መግለጫ

የሽብርተኛው ሕወሓት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሰራዊቱን የድል ግስጋሴ እንደማይገታው የአገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ፡፡

የአገር መከላከያ ሰራዊት ባወጣው መግለጫ ሽብርተኛው ከሚታወቅባቸው ስልቶቹ መሀል አንዱ ቅጥፈቱ ነው ብሏል፡፡

ሙሉ መግለጫው ቀጥሎ ቀርቧል፡-

የሽብርተኛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሠራዊታችንን የድል ግስጋሴ አይገታውም !

ሽብርተኛው ከሚታወቅባቸው ስልቶቹ መሀል አንዱ ቅጥፈቱ ነው፡፡ ጉልበት ሲያንሰው ምላሱ ይረዝማል፤ ያልሆነውን ሆንኩ፣ ያላደረገውንም አደረኩ…ይላል፡፡ ይህ ደግሞ ጥርሱን የነቀለበት እና ተወልዶ ያረጀበት ባህሪው ነው፡፡

አንድም ቀን ከአፉ እውነት ተገኝታ የማታውቀው ይህ ሽብርተኛ፣ ሽንፈቱን የሚሸፍነው የሠራዊታችንን ስም በማጠልሸት ነው፡፡ ደጋፊዎቹ ኪሳራውን እንዳያወቁ ፣ ሰላማዊው ህዝብ ልጆቹን እና ምግብ እንዳይጠይቅ እንዲሁም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ነውረኝነቱን እንዳይገነዘብ ሁል ጊዜ የተለመደች ስልት አለችው - የሠራዊታችንን ስም ማጠልሸት፡፡

ጀግናው ሠራዊታችን ባልዋለበት እና ባህሪው ባልሆነው ጉዳይ በጁንታው ፕሮፓጋንዲስቶች በስሙ ተደጋጋሚ ድራማ እየተሰራበት አይተናል፡ ሰምተናል፡፡ እዚህ ቦታ ሰላማዊ ህዝብ ገደል ከተተ፣ እዛ ደግሞ አቃጠለ… የሚሉ በውሸት ተቀነባብረው ለአለም የደረሱ ተውኔቶችን ታድመናል፡፡

እነዚህ በተደጋጋሚ በመከላከያ ሀይላችን ላይ ሲደረጉ የነበሩት የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ልክ ጸሀይ እንደመታው የጠዋት ጤዛ ወዲያው እውነታው ታውቆ ይጋለጣሉ፡፡ ለጊዜው ደጋፊዎቹን ቢያስጨፍርም የኋላ ኋላ እውነቱን ህዝባችን እና አለም አቀፉ ማህበረሰብ እየተገነዘቡት መጥተዋል፡፡

መዋሸት የማይሰለቸው ይህ ቡድን አሁንም የሠራዊታችንን ስም ለማጥቆር በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ ሠራዊቱ ሰላማውያንን ገደለ፣ አረደ…የሚሉ ከብት ባልዋለበት አይነት ድራማ ለማሳየት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ይህም እንደ ከዚህ ቀደሞቹ እርቃኑን መቅረቱ አይቀርም ፡፡ ምክንያቱም ቅጥፈትን የሚሸከም ህዝብ ስለሌለን፡፡

የመከላከያ ሠራዊታችን ሰብዓዊ ስሜት ያለው ህዝባዊነቱን ዛሬ ዛሬ አሸባሪው ህወሀት ቢክድም ዓለም የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ህዝብ ሲቸገር የሚያካፍል፣ ሲታመም የራሱን መድሀኒት የሚሰጥ ፣ ህዝብ ሲጠማ የሚያጠጣ፣ ሊገሉት የመጡት ሲማረኩ እንኳን የራሱን ሬሽን አካፍሎ ጦሙን የሚውል አዛኝ ፣ ሩህሩህ እና ደግ ሰራዊት ነው ያለን፡፡

የሠራዊታችን ባህሪ ይህ ሆኖ ሳለ የአሸባሪው ህወሀት ደጋፊዎች ሰሞኑን የተለመደ የፈጠራ ስራ እየፈበረኩ በማህበራዊ ሚዲያ ያሰራጩት የሠራዊቱን የደንብ ልብስ በመጠቀም በተደመሰሱት ታጣቂዎቹ ላይ የሚፈጽመው የተለመደ ድራማ መሆኑን ህዝባችን እንዲረዳ እየገለጽን ሠራዊታችን ወደፊትም የጀመረውን ሽብርተኞችን የማጽዳት ዘመቻ ከግብ ያደርሳል፡፡

ምንም እንኳን ጠላቶቹ ያልዋለበትን እና ባህሪው ያልሆነውን ጭቃ ሊለጥፉበት ቢሞክሩም፣ እሱ ግን እንደ እስካሁኑ ለእውነት እና ርትዕ በመቆም የድል ግስጋሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

#Walta
የሚያጋጥመንን ሕመም ችለን፤ የሚደቀንብንን ፈተና ተቋቁመን፣ የውስጥ ክፍተቶቻችንን ሞልተን፣ ጠንክረንና ነጥረን በመውጣት የጥፋት ቡድኑን ምኞት እናመክናለን። ሕዝብን በጅምላ ጠላት አድርጎ የሚፈርጅበት አካሄዱ፣ ሒሳብ የማወራረድ ጥማቱ፣ ሐገር የማፍረስ ከንቱ መሻቱ እና ሀገርና ሕዝብን ለውጭ ጠላቶቻችን አሳልፎ የመስጠት ክህደቱ እስከወዲያኛው ያከትማል።

ዛሬ ባህር ዳር ተገኝተን ይሄንን የኢትዮጵያ መከራ የሆነ ጠላት በሕዝባዊ ኃይል እንዴት መክተን፣ ቀልብሰንና ደምስሰን እንደምንቀብረው መክረናል። በወኔና በቆራጥነት፣ በእልህና በቁጭት የተነሡ የሀገር ልጆች በአነስተኛ መሥዋዕትነት የጥፋት ቡድኑን ተልዕኮ ለማምከን ዝግጁነታችንን ደግመን አረጋግጠናል። ድላችን የሚሳካው በተነሳሽነታችን ልክ ነውና፣ እንደ አንድ ልብ መካሪና እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ አንድ ክንድ ተግባሪ ሆነን የተነሣብንን ጠላት አሳፍረን እንሸኘዋለን።

የሽብር ቡድኑ ጀንበር ስታዘቀዝቅ፣ ያኔ ለሀገራችን የንጋት ጨረር ይፈነጥቃል። ለዚህም ታሪካዊ ሥራ ሠርተን ታሪክን እንደምንቀይር ምንም ጥርጥር የለውም።

መላው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትና የሁሉም ክልል የጸጥታ ኃይሎች በየአውደ ውጊያው እየተዋደቁና ክቡር መስዋዕትነት እየከፈሉ የሚገኙት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት የማይተካ ክብርና ፍቅር ነው፡፡ እኛም ሆንን መላው ኢትዮጵያውያን በማንኛውም ሁኔታ አብረናችሁ መሆናችንን እያረጋገጥን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ለዘላለም በጀግንነት የሚዘክሯችሁ መሆኑን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን፡፡

ስለሆነም የጀመራችሁት ታሪካዊና ፍትሀዊ ተጋድሎ በድል እንደሚጠናቀቅ ለአፍታም ቢሆን አንጠራጠርም፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለእናንተ ለብርቅዬ ጀግኖቻችን ያለንን ፍቅርና አክብሮት በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስም በይፋ ልንገልጽላችሁ እንወዳለን፡፡

በመጨረሻም አሸባሪው ሕወሓት የከፈተብን ጦርነት ህዝባዊ ጦርነት ስለሆነ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጦርነቱን ስፋትና ጥልቀት በመረዳት እንደወትሮው ሁሉ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከሁሉም ክልል የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሰለፍ አገርን ከጥቃት እንድንከላከል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የአገራችን ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ባለሀብቶችና ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶችና በአገር ውስጥና በውጭ አገር የምትኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የምንገኝበት ወቅታዊ ሁኔታ በአንድ ልብ የምንመክርበት፣ በጋራ የተሰነዘረብንን ጥቃት በጋራ የምንመክትበት፣ ብቸኛ አገራችንን በማፍረስ በአለም አደባባይ እርካሽና ክብር የለሽ ዜጎች ሊያደርጉን የተነሱ የውስጥ ባንዳዎችንና ኢትዮጵያ ጠል ኃይሎችን ያለአንዳች ልዩነት በመፋለም አኩሪ ገድል የምንፈጽምበትና ታሪክ የምንሰራበት መድረክ ላይ እንገኛለን፡፡ ስለሆነም በሚቀርብላችሁ ማንኛውም አገራዊ ግዴታ ላይ በመሳተፍ ኢትዮጵያን ለማዳን እንድትዘምቱ ጥሪያችንን በድጋሚ እናስተላልፋለን፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!
በሀገር-አቀፉ የፌዴራልና የክልል መንግስታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ
ጥቅምት፣ 2014 ዓ.ም
ባሕር ዳር

#Walta
#የብልፅግና ፓርቲ ጥሪ

ሰመራ-ጥቅምት 20/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)


የአሸባሪው ትሕነግ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ከንቱ ምኞትን በሚገባው ቋንቋ አስረድተን እስከወዲያኛው ላይመለስ በአጠረ ጊዜ ልንሸኘው ይገባል ሲል ብልፅግና ፓርቲ ጥሪ አቀረበ፡፡

ፓርቲው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው ሐተታ አሸባሪው ሕወሓት ኢትዮጵያን በቅጥፈት እጆቹ ጠፍጥፎ የጋገራት ህብስት አድርጎ በመቁጠር እሱ ባሻው ሰዓት የሚያቦካትና የሚፈረካክሳት ጡብ አድርጎ ይቆጥራታል ብሏል።

ነገር ግን ኢትዮጵያዊያንን በጎሳ እና በመንደር በመከፋፈል ኢትዮጵያ ኅልውናዋን መቼም ልታጣ አትችልም ሲል በአጽንኦት ገልጿል።

ኢትዮጵያዊነት የኅብር መገለጫ የዜግነት ክብር እና ኢትዮጵያዊ በመሆን ብቻ የሚገነዘቡት እውነት እንጂ አየር ላይ የተበተነ ጉም አይደለም ሲልም ነው ያብራራው፡፡

አያይዞም ሽብርተኛው የትሕነግ ቡድን በአገሪቱ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ መከራ ሲዘራና ሲያሳጭድ መቆየቱን የጠቀሰው ብልጽግና ፓርቲ ነፃ አወጣዋለሁ የሚለውንም የትግራይ ሕዝብ በነፃ አውጪ ስም በርካታ ግፍና መከራ ሲያሸክመው መኖሩን አስረድቷል።

አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ከወራሪ ጠላት ጠብቀው ያስረከቡንን ውድ አገራችንን የወቅቱ የጋራ ጠላታችን የሆነው ትሕነግ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ከንቱ ምኞቱን በሚገባው ቋንቋ አስረድተን እስከወዲያኛው ላይመለስ በአጠረ ጊዜ ልንሸኘው ይገባል ብሏል ፓርቲው፡፡

ኢትዮጵያዊነትን በማንኳሰስ የሚለወጥ አንዳች ነገር እንደሌለ የገለጸው ብልጽግና ፓርቲ አገር የሁላችንም ምሰሶ ናት አገር ከግለሰቦችና ከቡድኖች በላይ ናት፤ እንደ አፈ ቀላጤዎቹ ቢሆንማ ኖሮ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ልትኖር አትችልም ነበር ብሏል።

#Walta
ኤርትራ በአሜሪካ የተጣለባትን ማዕቀብ ተቃወመች፣፣

ሰመራ-ኅዳር 4/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ኤርትራ በአሜሪካ መንግሥት ያተጣለባትን ማዕቀብ ግብረገብነት የጎደለው ስትል ተቃወመችው፡፡

ኤርትራ በአሜሪካ መንግሥት ያተጣለባትን ማዕቀብ ግብረገብነት የጎደለው ስትል ተቃወመችው፡፡

የኤርትራ መንግሥት ዛሬ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤ የአሜሪካን አካሄድ ኮንኗል፡፡

የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር እየጣለ የሚገኘው ማዕቀብ በተሳሳተ አረዳዱና ግጭት ፈጣሪ ፖሊሲው የተመራ ስሁት ውሳኔ መሆኑንም አፅንኦት ሰጥቶበታል፡፡

የተናጠል ማዕቀቡ ሊጣልበት የሚገባው አካል ወደ ሉኣላዊቷ አገር ኤርትራ ሮኬትም ጭምር ሲያስወነጭፍ የነበረው አሸባሪው ሕወሓት ቢሆንም አሜሪካ ግን አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ይሉት አካሄድ መምረጧን በመጠቆም ወቅሷል፡፡

መግለጫው የባይደን አካሄድ የኤርትራንና ሕዝቧን ሉኣላዊነት፣ ራስ ቻይነትና ነፃነትን የሚቃረን እንደሆነም አስምሮበታል፡፡

የአሜሪካ ፍላጎትም በጥቅሉ በምስራቅ አፍሪካ በተናጠል ደግሞ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዳይመጣ ማድረግና ቀውስን በማባባስ ጣልቃ ለመግባት የመሻት ነው ሲልም ኮንኖታል፡፡ ይህ ፍላጎት ደግሞ በበሬ ወለደ ውሸት በሚሰሩ የፅንፈኛ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች እየታየ ነው ሲል አስምሯል፡፡

ሚዛን በሳተ መርህ ላይ ተነስተው የሚጣሉ ማዕቀቦች ረሃብን ፈጥሮ ሕዝብ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ እንዲገባ ማድረግና አለመረጋጋት በመፍጠር እጅ ለማስገባት የመሻት ውጥን መሆኑን ግልፅ አድርጓል፡፡

አሜሪካ ‹‹ማዕቀቡ የኤርትራን ሕዝብ ለመጉዳት ዓላማ የለውም›› ማለቷን በመጥቀስም በዚህ የአዞ እምባ የሚሸወድ ሰው የለም ብሏል፡፡

ኤርትራ የአሜሪካን ማዕቀብ እንደማትቀበል ያሳወቀው መንግሥት ተቃውሞውን በደብዳቤ ያሳወቀም ሲሆን፤ የፍትሕና ሰላም ወዳጅ እንዲሁም የሉኣላዊነትና ነፃነት ደጋፊ የሆኑ ሕዝቦችና ኃይሎች ሁሉ ከኤርትራ ጎን እንዲቆሙ ጠይቋል፡፡

የአሜሪካ መንግሥት ኤርትራ ላይ ማዕቀብ የጣለው በኢትዮጵያ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ማዕቀቡን በመቃወም ኤርትራ በአሸባሪው ሕወሓት ሮኬት ሲተኮስባት የነበረች ሉኣላዊ አገር መሆኗን አስታውሶ ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ያቀረበችው ክስ በሌለበት 3ኛ ወገን ጠያቂና ወቃሽ ለመሆን እየሄደ ያለበትን አግባብ ኮንኗል፡፡

#Walta
#16ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ከአሁን በፊት ከነበረው በተለየ መልኩ እንደሚከበር ተገለጸ፣፣

ሰመራ-ኅዳር 11/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

16ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ከአሁን በፊት ከነበረው በተለየ መልኩ እንደሚከበር ተገለጸ፣፣

የኢትዮጵያ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ቀን ለ16ኛ ጊዜ "ወንድማማችነት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት "በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ ከተማ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ዛህራ ዑመድ በዘንድሮው ዓመት የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን አሸባሪው ሕወሓት በከፈተው ጦርነት ምክንያት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሀገርን ኅልውና ለመታደግ ያለውን ርብርብ በማጉላት አንድነታችንን የምናሳይበት ቀን በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

አሸባሪው የትሕነግ ቡድን በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በውሸት ትርክት የኢትዮጵያን ህዝብ ሲያታልል እንደነበር ገልፀው አሁን ላይም ስልጣንን ባለመጥገብ ተከብራ የኖረችን ሀገር ለሰላም እጦት ዳርጓታል ብለዋል፡፡

ሀገርን ለማፈራረስ ኢትዮጵያ ጠል ከሆኑ ምዕራባውያን ጋር በመጣመር እየተንቀሳቀሰ የሚገኘውን የሽብር ቡድን ለመመከት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የበዓሉ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ስንታየሁ ማሞ ቀኑ ከአሁን በፊት ከነበረው አከባበር በተለየ ለመከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስ፣ የህዳሴ ግድቡን ከፍፃሜ ለማድረስ የህዳሴ ዋንጫ ርክክብ በማድረግ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ሲምፖዚየም ላይ ትኩረት ያደረገ ይሆናል ብለዋል፡፡

#Walta
#የአሜሪካ ኤምባሲ ከሽብር ፈጣሪ መግለጫዎቹ እንዲቆጠብ መንግሥት አሳሰበ፣፣

ሰመራ-ኅዳር 16/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የአሜሪካ ኤምባሲ ከሽብር ፈጣሪ መግለጫዎቹ እንዲቆጠብ መንግሥት አሳሰበ፣፣


የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች ዜጎቻቸውን ለማውጣት ያደረጉት ሙከራ ስህተት መሆኑ ሲገባቸው ሀሳባቸውን እየቀየሩ ነው ሲል መንግሥት አስታወቀ፡፡

በዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን ስም ለማጠልሸት የሚደረገው ሙከራ ፍጹም ስህተት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአሜሪካ ኤምባሲ እንደዚህ ዓይነት መግለጫ ከማውጣት እንዲቆጠብ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ አሳስበዋል፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤምባሲዎችን የማስፈራራት ስራ ከመስራት እንዲቆጠቡም በሰጠው መግለጫ አስጠንቅቋል፡፡

#Walta
#16-hattoh addah Yassakaxxen Agat Kee Agattiinaay, Ummattah Ayroh Qaffaydak Fakkenti Porograam Gexsitak Geytima.

Samara-Naharsí kudok 28, 2014 (AFMMA)

16-hattoh addah Yassakaxxen Agat Kee Agattiinaay, Ummattah Ayroh Qaffaydak Fakkenti Porograam Gexsitak Geytima.

Agat caddol 16hattoh addah gexsitak geytimta tama qaffaydak Fakkenta taddeera Diredawah magaalal meqe gurral gexsitak geytinta.

Fakkentí Qaffaydah aracal Federeeshin Maláh Buxak Naharsí Afteena Massakaxxa le Agenyehu Teshaager Kee Ciggilta Caxáh Afteena Massakaxxa Le Zahra Cummad Kee Sangarâ Cokmih Buxah Perezxentih tan Gifti Meaza Ashennaafi edde anuk Federaal Kee Rakaakayittê Doolatittek Fayyale miraaciini edde angaluk geytiman.

Awakî Saaqat Rakaakayittek Temeete Qaadâ Dokonitte ken dariifal tan Qaadoodi ayballuk geytiman.

#Walta
#Ameerikak Baxsale Awlaytuh Afrikah Gaysal Suge Jefri Filtimaan Taamak Ugutem Timixxige

Samara-Ciggilta kudok 29, 2014 (AFMMA)

Ameerikak Baxsale Awlaytuh Afrikah Gaysal Suge Jefri Filtimaan Taamak Ugutem Timixxige

Tengele Ameerika Afrikah Gaysal Baxsale Farmoyta abak reedisseh sugte Jefri Filtimaan Taamak Ugusseh tan Ameerikak Afâ caagiidah Malaak Antooni Bilinken Yiysixxige.

Afâ caagiidah Malaak Twitterik isi golil tatruse ux farmol elle yescesseh yan innal Jefri Filtimaan aracat Ambasaader Xeevid Saaterfilxi reedeh yanim diggoyse.

Reedak uguteh yan Jefri Filtimaan Warreeh yan Sagla Alsih addal Afrikah Gaysal Ameerikak Baxsale Awloytu akkuk taamitak sugem tamixxige.

Afrikah Gaysal Ameerikak Qusba Awlaytu akkuk reedeh yan Ambasaader Xeevid Saaterfilxi 40 Liggidak muxxi yakke uddurih abak-raagle Raage Diplomaat kinnim warsan.

Ambasaader Xeevid Saaterfilxi ahak dumal Saquudiyaay, Libnaan, Tuunis Kee Suuriyal Diplomaat akkuk taamitem kee Ameerikak Afâ Caagiidah Malaakak Fantí Maacih Caagiida wagita Fayyale Diplomaat akkuk taamite.

Aaxigeh meqeemik, Warree Sagla Alsah Ameerikah Awlaytuh Afrikah Gaysal suge Jefri Filtimaan Ityopliyah Doolat Juntâ Qarkakisa fakte carbih gabâ gacsah ugusseh ten madqâ dagâ raaqiyyih gaadu Sadak Juntah gabbisak sugem dubuh hinnay baad ayyunti Ityoppiyah Doolatal uma mabla hayuh kaxxam macalak sugem warsan.

#Walta
#Oromiyah Rakaakayih Doolat Ummaan Alsak 4hattoh Ayro Kawsí Ayro Takkuh Faatacisse

Samara-Agda baxissok 03, 2014 (AFMMA)

Oromiyah Rakaakayih Doolat Ummaan Alsak 4hattoh Ayro Kawsí Ayro Takkuh Faatacisse

Oromiyah Rakaakay Doolat Ummaan Alsak Bilô Fareey Kawsí Ayro Abak Madaqtem diggosseh tan Qaadaa Kee Turiizim Biiro tama taddiira Beerih Ayro (Agda-baxissok 04, 2014) Xabba haanam abinnoowe lem tiysixxige.

Tama Caagid wagittaamal Maybalaalaqa yeceeh yan Oromiyah Rakaakayak Qaada Kee Turiizim Biirok Ciggiila saqalah yan Gifta Birhaanu Gute Beerih Ayroh taddiira Kawsi Aroocah (Library) Gufnee Kee Inki Saaqat Yakke uddurih Kawsal qimmise loonum diggoyse.

Tah tannal anuk, Oromiyah Rakaakayih Doolat Madaqteh tan Ummaan Alsak Farey hattoh Ayro Kawsi Ayro abaanamih taddiira aggireqekal Ummaan alsal gexsittuh Rakaakayak Qaadaa Kee Turiizim Biiro Koobahisaanamih dirki teetil tanim Gifta Birhaanu kassiise.

#Walta
#ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ለተለያዩ ግለሰቦች የአምባሳደርነት ሹመት ሰጡ፣፣

ሰመራ-ጥር 18/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለተለያዩ ግለሰቦች የሙሉ አምባሳደርነት እና የአምባሳደርነት ሹመት ሰጡ፡፡

በዚህም መሠረትም፡-
1/ አቶ ተፈራ ደርበው
2/ አቶ ደሴ ዳልኬ
3/ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)
4/ ጄኔራል ባጫ ደበሌ
5/ ጄኔራል ሀሰን ኢበራሂም
6/ ወ/ሮ ሽትዬ ምናለ
7/ ፍቃዱ በየነ (ፕ/ር)
8/ አቶ ረሻድ መሀመድ
9/ አምባሳደር ጀማል በከር
10/ አቶ ፈይሰል ኦሊይ
11/ አቶ ኢሳያስ ጎታ
12/ አቶ ፀጋአብ ክበበው
13/ አቶ ጣፋ ቱሉ
14/ ደገነት ተሾመ (ዶ/ር)
15/ አቶ ዳባ ደበሌ
16/ አቶ ፍቃዱ በየነ
የባሉሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት
እንዲሁም
1/ አቶ አሳየ አለማየሁ
2/ አቶ ኃይላይ ብርሃነ
3/ አቶ አወል ወግሪስ
4/ ወ/ሮ ብዙነሽ መሠረት
5/ አቶ አንተነህ ታሪኩ
6/ አቶ አክሊሉ ከበደ
7/ አቶ ሰይድ መሐመድ
8/ አቶ ዮሴፍ ካሳዬ
9/ አቶ ዘላለም ብርሃን
1ዐ/ ወ/ሮ ፍርቱና ዲባኮ
11/ አቶ ወርቃለማሁ ደሰታ በአምባሳደርነት የተሾሙ መሆኑን ከፕሬዝዳንት ፅሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

#Walta
#ገንዘብ ሚኒስቴር መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ በቀጥታ እንዲገቡ ወሰነ፣፣

ሰመራ- ሚያዝያ 01, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ገንዘብ ሚኒስቴር መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ በቀጥታ እንዲገቡ ወሰነ፣፣

ሚያዝያ 1/2014 (ዋልታ) መሰረታዊ የምግብ ሽቀጦች የሆኑት ዘይት፣ ስንዴ፣ ስኳር፣ የህጻናት ወተት እና ሩዝ ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፍቃድ (በፍራንኮ ቫሉታ) በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል በቀጥታ እንዲገቡ የገንዘብ ሚኒስቴር ወሰነ።

መንግሥት በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት እንዲቻል እና በርካታ የውጭ ሀገር የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን ሚና መጫወት እንዲችሉ የፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲፈቀድላቸው ጥያቄ እያቀረቡ በመሆኑ ነው ብሏል።

ቀረጥና ታክሱ በሚመለከት በገንዘብ ሚኒስቴር በ22/3/2013 ዓ.ም በተጻፈው ደብዳቤ መሰረት እንዲፈጸምና አፈጻጸሙም ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት በኩል ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግበት መወሰኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#Walta
#ሚኒስቴሩ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገ፣፣

ሰመራ-ሰኔ 28፣ 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ሚኒስቴሩ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገ፣፣

ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታኅሣሥ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሰራር እና የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ውሳኔ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
ቤንዚን - 47 ነጥብ 83 በሊትር
ነጭ ናፍጣ - 49 ነጥብ 02 በሊትር
ኬሮሲን - 49 ነጥብ 02 በሊትር

ቀላል ጥቁር ናፍጣ - 53 ነጥብ 10 በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ - 52 ነጥብ 37 በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ - 98 ነጥብ 83 በሊትር መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አስታውቋል፡፡

#Walta
#የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ745 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ፈቀደ

ሰመራ-ታኅሣሥ 5/2015 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የዓለምን ባንክ ለኢትዮጵያ ለጤና አገልግሎትና ለጎርፍ አደጋ መከላከል ሥራዎች የሚውል የ745 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ፈቀደ።

ባንኩ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በኮቪድ 19፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በግጭት ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ይህ ቀውስ ተገቢ የሆነ የጤና አገልግሎት እንዳይሰጥ ከማድረጉም በላይ ላለፉት አስርት አመታት ኢትዮጵያ በጤናው መስክ ባስመዘገበችውን መሻሻል ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል።

ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች እስከ 24 ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ በቂ የሆነ የጤና አገልግሎት እያገኘ እንዳልሆነ የጠቀሰው ባንኩ፤ የጎርፍ አደጋም በተመሳሳይ እስከ 300 ሺህ ሠዎችን ማፈናቀሉን 288 ሞት ማስከተሉንም ገልጿል።

ባንኩ ባደረገው ጥናትም በጎርፍ አደጋ እስከ 358 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ጉዳት ደርሷል። ከእነዚህ ጉዳቶች በመነሳት የባንኩ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ችግሩን ለመቋቋም ያግዝ ዘንድ ሁለት ፕሮጀክቶችን ማጽደቁን አስታውቋል።

በመጀመሪያው ፕሮጀክቱ የአንደኛ ደረጃ የጤና ተቋማት አገልግሎትን ለማጠናከር ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር (አይዲኤ) 400 ሚሊዮን ዶላር፣ ከዓለም አቀፉ ፋይናንስ ፋሲሊቲ (ጂኤፍኤፍ) 45 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን ገልጿል።

ሀለተኛው ለጎርፍ አደጋ መከላከል ሥራ የሚውልና ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር (አይዲኤ) የተገኘ የ300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መፈቀዱን ነው ባንኩ የገለጸው።

#Walta