Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#የፌደራል መንግሥት መግለጫና ጥሪ፣፣

ሰመራ-ጥቅምት 12/2014 (አፍ.ብ.መ.ድ)

የፌደራል መንግሥት መግለጫና ጥሪ፣፣

ሕብረተሰቡ የሕወሓትን የሽብር ቡድን እኩይ ዓላማና እቅድ በመረዳት አገርን ለመበታተን የተነሳውን የጥፋት ኃይል ሴራ እንዲያከሽፍ መንግሥት ጥሪ አቀረበ፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል።

ሙሉ መግለጫው ቀጥሎ ቀርቧል:-

አሸባሪው የትሕነግ ቡድን ደሴ ከተማን ዒላማው አድርጎ የሚያቅዳቸው በርካታ የጥፋት ሥራዎች መኖራቸው የሚታወቅ ነው።

በሁሉም ግንባሮች በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን፣ በአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ እንዲሁም ለህልውናቸው በተሰለፉት የክልሉ ወጣቶች የሚደርስበት ከባድ ኪሳራ ሩቅ እንደማያስኬደው ግልጽ ሆኗል።

የደሴ ከተማ ላይ ያቀደው ጥፋትም ይህንኑ ሽንፈቱን በጥፋት ሥራ ለመሸፈን ማቀዱን ያሳያል። ኅብረተሰቡም የዚህን ሽብር ቡድን እኩይ ዓላማና እቅድ በመረዳት ሀገርን ለመበታተን አቅዶ የተነሳውን የጥፋት ኃይል ሴራ ማክሸፍ ይገባዋል።

የሽንፈት ገፈትን እየቀመሰ የሚገኘው የሽብርተኛው ቡድን በደሴ ብዙ ሠራዊት ሊኖር ይችላል በሚል በተጨማሪም ፋኖ የከተማ የውጊያ ስልትን ለማካሄድ ሊዘጋጅ ይችላል የሚል ግምትን በማሳደር ሰርጎ ገቦችን በመጠቀም በከተማዋ የመብራት መስመሮችን ለማቋረጥ እና በደሴ የሚገኘው የፀጥታ ኃይል ላይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናን ለማሳደር ማቀዱን የሚያሳዩ መረጃዎች ወጥተዋል።

በከተማዋ የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊትም ኾነ የክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ከመረጃ እንዲርቅ ማድረግንም በእቅዱ ይዟል። ሐሰተኛ መረጃዎችንና ምስሎችን በስፋት በማሰራጨትም የሠራዊቱንና አጠቃላይ የፀጥታ ኃይሉን ሞራል ለማዳከም ያስችሉኛል በሚል የያዛቸው እቅዶች መኖራቸው ተደርሶበታል።

ይህ የጥፋት ቡድን ሀገርን ማሸበር ዋና ዓላማው መሆኑን የሚያሳይ ነው። የአማራ ክልል ሕዝብና መላው ኢትዮጵያውያን የሽብር ቡድኑ ትህነግ ያቀዳቸውን የማወናበጃና የኅብረተሰቡን ኢኮኖሚና ማኅበራዊ ተግባራት የማወክ እንቅስቃሴን ቀድሞ በመረዳት ሰርጎ ገቦችን በማጋለጥና አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ እንደስካሁኑ ጠንካራ ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል መንግሥት መልእክት ያስተላልፋል።

#Walta
#የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በተባበሩት መንግስታት አፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ ስለተፈጠረው ሁኔታ በኮሚሽኑ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠየቀ፣፣

ሰመራ-ህዳር 16/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በተባበሩት መንግስታት አፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ ስለተፈጠረው ሁኔታ በኮሚሽኑ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠየቀ፣፣

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በተባበሩት መንግስታት አፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ ስለተፈጠረው ሁኔታ በኮሚሽኑ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠየቀ።

በኮሚሽኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ በከተማዋ ረብሻ መፈጠሩንና የኮሚሽኑ ቅጥር ግቢ እንደታወከ በማስመሰል የተቀነባበረ የቪዲዮ ምስል ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መነጋገሪያ ሁኖ ውሏል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የጠየቃቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጄላን አብዲ ሁኔታውን ኮሚሽናቸው እየተከታተለው መሆኑንና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን ማብራሪያ እንዲሰጥ መጠየቁን ነግረውናል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት በአዲስ አበባ የጸጥታ ችግር ሊፈጠር ይችላል በሚል በሬ ወለደ የውሸት ወሬ በማሰራጨት ሰራተኞቹ ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ዛሬ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተሰራው የሁከት ድራማም የዚህ የውሸት ፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ አንዱ አካል ሳይሆን እንዳልቀረ ብዙዎች ተንታኞች እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

_አካባቢህን ጠብቅ

_ ወደ ግንባር ዝመት

_ መከላከያን ደግፍ

#የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ