Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#የደሴ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት የሞተር እና ባለ3 እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መወሰኑ ተሰማ።

ሰመራ-ጥቅምት 14/2014 (አፍ.ብ.መ.ድ)

የደሴ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት የሞተር እና ባለ3 እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መወሰኑ ተሰማ።

ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበረው ውሳኔ እስኪነሳ ወይም እስኪሻሻል ሞተር ሳይክሎች እና ባለ3 እግር ተሽከርካሪዎች በየትኛውም ሰዓት ከተማዋ ላይ መንቀሳቀስ አይችሉም።

ውሳኔው የተላለፈው የደሴ ከተማን ፀጥታና ደኅንነት ለማስጠበቅና የአሸባሪውን ሕወሓት ሰርጎ ገቦች ለመቆጣጠር እንዲቻል በሚል መሆኑን የደሴ ከተማ አስተዳደር ለዋልታ ገልጿል።

ንግድ ቤቶች በተለይም መድኃኒት ቤቶች በአስቸኳይ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ የፀጥታ ምክር ቤቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ውሳኔውን በማያከብሩ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድም ምክር ቤቱ አስጠንቅቋል።

#Walta