Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#16ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ከአሁን በፊት ከነበረው በተለየ መልኩ እንደሚከበር ተገለጸ፣፣

ሰመራ-ኅዳር 11/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

16ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ከአሁን በፊት ከነበረው በተለየ መልኩ እንደሚከበር ተገለጸ፣፣

የኢትዮጵያ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ቀን ለ16ኛ ጊዜ "ወንድማማችነት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት "በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ ከተማ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ዛህራ ዑመድ በዘንድሮው ዓመት የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን አሸባሪው ሕወሓት በከፈተው ጦርነት ምክንያት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሀገርን ኅልውና ለመታደግ ያለውን ርብርብ በማጉላት አንድነታችንን የምናሳይበት ቀን በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

አሸባሪው የትሕነግ ቡድን በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በውሸት ትርክት የኢትዮጵያን ህዝብ ሲያታልል እንደነበር ገልፀው አሁን ላይም ስልጣንን ባለመጥገብ ተከብራ የኖረችን ሀገር ለሰላም እጦት ዳርጓታል ብለዋል፡፡

ሀገርን ለማፈራረስ ኢትዮጵያ ጠል ከሆኑ ምዕራባውያን ጋር በመጣመር እየተንቀሳቀሰ የሚገኘውን የሽብር ቡድን ለመመከት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የበዓሉ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ስንታየሁ ማሞ ቀኑ ከአሁን በፊት ከነበረው አከባበር በተለየ ለመከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስ፣ የህዳሴ ግድቡን ከፍፃሜ ለማድረስ የህዳሴ ዋንጫ ርክክብ በማድረግ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ሲምፖዚየም ላይ ትኩረት ያደረገ ይሆናል ብለዋል፡፡

#Walta