Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#Ameerikak Namma Maláh Buxa Doorol Joo Bayxen Yeysem Diggosse.

Samara-C/kudok 29/2013 (AFMMA)

Ameerikak Namma Maláh Buxa Tekke Doorol Joo Bayxen Yeysem Diggosse.

Ameerikah Kongirees Joo Bayxen Kee Kamaala Hariisin Ameerikal tekke Doorol Perzxentii Kee Ciggiila Perezxenti akkuk doorimen axcuk faatacise.

Namma Maláh buxa tama margaq teceem Bensilvenyaa Kee Arizoona deqsitta magaaloolul tontocowwe xongolaali dugteek laka.

Tah tannal anuk, tekke Doorol dudda le xongolo week lakal Doorol radeh yan Perezxenti Donald Tirumpi Qokolta maritte Kappitool culak Kongirees Koboxut gexkalit yakkeenik gibbateenim tama xaagi yascasse.

#FBC
#የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ::

ሰመራ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፋ.ብ.መ.ድ)

የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ::

የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ፡፡ በዚህም የተፈጥሮ ሳይንስ ለወንድ 380 ሲሆን ለሴት ደግሞ 368 መሆኑ ተገልጿል፡፡ ለማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ለወንድ 370 ሲሆን ለሴት 358 ሆኗል፡፡

#FBC
#የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ::

ሰመራ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፋ.ብ.መ.ድ)

የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ::

የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ፡፡ በዚህም የተፈጥሮ ሳይንስ ለወንድ 380 ሲሆን ለሴት ደግሞ 368 መሆኑ ተገልጿል፡፡ ለማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ለወንድ 370 ሲሆን ለሴት 358 ሆኗል፡፡

#FBC, Ministry of Science and Higher Education
#ጠ/ ሚ ዐቢይ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን የሰጡት ቃለ መጠይቅ በዚህ የጥሞና ወቅት እንዳይተላለፍ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን አሳሰበ፣፣

ሰመራ-ሰነ 10፣ 2013 (ኤ ኤፍ ኤም ኤም)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን የሰጡት ቃለ መጠይቅ በዚህ የጥሞና ወቅት እንዳይተላለፍ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን አሳሰበ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እድሪስ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ ምንም እንኳን ቃለ መጠይቁ የመንግስት የስራ ክንውኖች ላይ ያተኮረና የምርጫ ቅስቀሳ እንዳልሆነ ቢታወቅም በዚህ የጥሞና ወቅት ሊተላለፍ አይገባም።

የዘንድሮ ምርጫ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ ፍትሃዊ፣ ግልጽና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ቁርጠኝነቱን ያሳየበት ነው ያሉት አቶ መሀመድ ÷ ቃለ መጠይቁ ከምርጫ ጋር ግንኙነት ባይኖረውም ብዥታ እንዳይፈጠር ሲባል የመገናኛ ብዙሃኑ ከምርጫው በፊት እንዳያስተላልፉና ማስተዋወቃቸውንም እንዲያቆሙ አሳስበዋል።

በተመሳሳይ የማሕበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የምርጫ ቅስቀሳ የሚመስሉ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ላይ የሚገኙ አካላትም ከድርጊታቸው መታቀብ አለባቸው ብለዋል።


#FBC
#የ6ኛው ሀገር አቀፍ የምርጫ ውጤት ይፋ እየተደረገ ነው

ሰመራ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኣፋ.ብ.መ.ድ)የ6ኛው ሀገር አቀፍ የምርጫ ውጤት ይፋ እየተደረገ ነው

በዚህም ውጤት መሰረት አዲስ አበባ 10 ክልል ብልፅግና አሸንፏል።

ያሸነፈው መቀመጫ 138

አፋር ብልፅግና 17 ምርጫ ክልሎችን፣ አርጎባ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት 1 ምርጫ ክልል አሸንፏል።

አማራ ብልፅግና 114 ምርጫ ክልል፣ አብን 6 ምርጫ ክልል አሸንፈዋል።
ቤኒሻንጉል ብልፅግና 4 የምርጫ ክልሎችን አሸንፏል።

ድሬዳዋ ብልፅግና 47 የምርጫ ክልሎችን አሸንፏል።

ጋምቤላ ብልፅግና 13፡ ጋህነን 2 የምርጫ ክልሎችን አሸንፏል።

#FBC
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ለብቻው ታንክ የማረከው የአፋር ልዩ ሃይል አባል::

#FBC
#ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር እና ሩዝ ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ ተወሰነ፣፣

ሰመራ ፣ ነሐሴ 28 ፣ 2013 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር እና ሩዝ ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ ተወሰነ፣፣

የዋጋ ንረት በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር እና ሩዝ ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ወሳኝ በሆኑ ሸቀጦች ላይ ቀረጥና ታክስ ማሻሻያ መደረጉን ተናግረዋል።

በመግለጫቸውም ፖስታ እና ማካሮኒ የጉምሩክ ቀረጡ እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንደተነሳላቸውም ነው የተናገሩት።

ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር እና የሩዝ ምርቶች ከውጭም ሆነ ከሃገር ውስጥ ግዥ ሲፈጸም ከማንኛውም ቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ ተወስኗልም ብለዋል በመግለጫቸው።

ከዚህ ባለፈም በዶሮ እንቁላል ላይ የነበረው ተጨማሪ እሴት ታክስ ፍላጎት እና አቅርቦት እስከሚጣጣም ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ ለገበያ እንዲቀርብ ተወስኗልም ነው ያሉት።

ይህም ከዛሬ ጀምሮ ለሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች እና አስፈጻሚ አካላት መመሪያ መተላለፉን አንስተዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው በመግለጫቸው ያለ ውጪ ምንዛሬ ሸቀጦችን ከውጪ የማስገባት ፈቃድ (የፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ) ለ6 ወራት በመራዘሙ ምርት ማስገባት የጀመሩ መቀጠል እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

#FBC
#ከውጪ የገባው የምግብ ዘይት ለክልሎች እየተከፋፈለ ነው፣፣

ሰመራ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ከውጪ የገባው የምግብ ዘይት ለክልሎች እየተከፋፈለ ነው፣፣

የዘመን መለዋጫ በዓልን አስመልክቶ የዘይት አቅርቦት ችግር እንዳይከሰተ ከውጪ የገባው የምግብ ዘይት ወደ ክልሎች እየተከፋፈል መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ አበባ ታመነ እንደገለፁት÷ መንግስት በሃገሪቱ በአሁኑ ወቅት በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በርካታ ጫናዎች ቢኖሩበትም ጫናውን ተቋቁሞ ሃገር እንድትቀጥል ጥረቶች በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡


መንግስት የዘመን መለወጫ በዓል መምጣቱን ተከትሎ ህብረተሰቡ የዘይት አቅርቦት ችግር እንዳይገጥመው በማሰብ ያለውን ውስን የውጪ ምንዛሬ ተጠቅሞ ዘይት ከውጪ ሃገር ማስመጣቱን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም በአሁኑ ወቅት ከውጪ የገባው ዘይት በአንዳንድ ምክንያቶች በተፈለገው ጊዜ ባይደርስም÷ አሁን ግን ለክልሎች እየተሰራጨ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC
#ነገ በፌዴራል ደረጃ አዲስ መንግሥት ይመሠረታል፣፣

ሰመራ፣ መስከረም 23፣2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ነገ በፌዴራል ደረጃ አዲስ መንግሥት ይመሠረታል፣፣

በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት መሠረት ነገ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም በፌዴራል ደረጃ አዲስ መንግሥት ይመሰረታል።

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2፥ በሕዝብ ተመርጦ አዲስ የሚቋቋም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ጊዜውን መጀመር ያለበት በ“መስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ነው” ብሎ በደነገገው መሠረት ነው ነገ በፌዴራል ደረጃ አዲስ መንግሥት የሚመሠረተው።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በቅርቡ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫም፥ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ በተደረገው የሰኔ 14ቱ የምርጫ ውጤት መሰረት፤ መስከረም 24 ቀን 2014ዓ.ም አዲስ መንግሥት እንደሚመሰረትና ለዚህም ህጋዊ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ነው ያስታወቁት።

የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 56 ላይ “ በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል ያደራጃል፤ ይመራል” ብሎ በደነገገው መሠረት፥ ሰኔ 14 ቀን 2013 በተካሄደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ አሸናፊ የሆነው ፓርቲ ነው አዲስ መንግስት የመመስረት የፖለቲካ ሥልጣን ያለው።

በመሆኑም በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ እንደተደረገው የምርጫ ውጤት፥ መንግስት የመመስረት የፖለቲካ ሥልጣን ያለው ድርጅት የብልጽግና ፓርቲ መሆኑ ይታወቃል።

አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በዚህ ታሪካዊ ጉባኤው የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሾም ሲሆን፥ ተሿሚው ጠቅላይ ሚኒስትርም በአዲስ መልክ በሚዋቀረው አደረጃጀት አግባብ ካቢኔያቸውን ለምክር ቤቱ በማቅረብ ያስፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ንቁ ተሳትፎ ያደረገውና ሊመራኝ ይገባል ብሎ ላመነበት አካል ድምጹን የሰጠው ህዝብ፥ በሚቋቋመው አዲስ መንግስት የሥራ አፈጻጸም ላይ ግልጽ አስተያየት የሚሰጥበትና ጥያቄ የሚያቀርብበት የአሰራር ሥርዓት እንደሚዘረጋም አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገልጸዋል።

አዲስ የሚመሰረተው የሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት የሕዝብ ውክልና በተግባር የሚንጸባረቅበት ምክር ቤት ይሆናልም ነው ያሉት።

አደረጀጀቱም የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ለማፋጠንና የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚያስችል አግባብ አንደሚዋቀር አፈ ጉባኤው ጠቁመዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፥ ምሁራንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት፥ ወቅቱ የኢትዮጵያን በጎ ነገርና ብልጽግና ለማየት የማይሹ የውጭ ሃይሎችና የውስጥ ባንዳዎች በአገራችን ላይ አደጋ ለመፍጠር የሚረባረቡበት ጊዜ በመሆኑ፥ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት መላውን ህዝብና የፖለቲካ ሃይሎችን በማስተባበር ሀገራዊ ኃላፊነቱን በብቃት መወጣት እንደሚጠበቅበት ጠቁመዋል፡፡

አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ እየተደረገ ያለው ዘመቻ በአጭር ጊዜ መቋጨት አለበት የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ አዲስ የሚዋቀረው መንግስት ለሀገር ስጋት የሆኑ ኃይሎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድና በአገራችን ሰላምን ማስፈን ይኖርበታል ብለዋል፡፡

#FBC
#ብሔራዊ ባንክ የብድር ገደብ ላይ ማሻሻያ አደረገ፣፣

ሰመራ- መስከረም 25፣ 2014(አፋ.ብ.መ.ድ)

ብሔራዊ ባንክ የብድር ገደብ ላይ ማሻሻያ አደረገ፣፣

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ከብድር አቅርቦት ጋር በተያያዘ የጣለውን እገዳ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ የብድር ገደብ ላይ ማሻሻያ አደረገ፣፣
በማሻሻያው ባንኮች አምስት የብድር ዓይነቶችን መፍቀድ እንደሚችል አሳዉቋል፡፡

እነዚህም ባንኮች የሰጡትን ብድር ለማስመለስ ሐራጅ ያወጧቸውን ንብረቶች ለመግዛት ለሚጠይቁ ገዥዎች ስለሚሰጥ ብድር ፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ወገን መካከል የሚደረግ ግብይትና ለባንክ ሠራተኞች ስለሚሰጥ አስቸኳይ ብድር ነው፡፡

በተጨማሪም ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው መኖርያ ቤት ለመግዛት ወይም ለመገንባት ከታመነባቸው ጠያቂዎች ስለሚሰጥ ብድር፣ ከፀደቁ ድርጅቶችና ከተቋም ሠራተኞች ለሚቀርቡ የብድር ጥያቄዎች እንዲሁም በጎንደር አካባቢ ለሚገኙ የሰሊጥ አምራች ብድር ጠያቂዎች ላይ ማሻሻያዎች መደረጉን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

በዚህም በእነዚህ የብድር ዓይነቶች ላይ ብድር መስጠት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

#FBC
#የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር መወሰኛ ረቂቅ አዋጅ ላይ 22 ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ቀርበዋል::

ሰመራ- መስከረም 26፣ 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር መወሰኛ ረቂቅ አዋጅ ላይ 22 ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ቀርበዋል::

አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ 22 ሚኒሲቴር መስሪያ ቤቶች ቀርበዋል።

ዝርዝሩም የሚከተለው ነው፦
1. ግብርና ሚኒስቴር
2. የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
3. የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
4. የማዕድን ሚኒስቴር
5. የቱሪዝም ሚኒስቴር
6. የስራና ክህሎት ሚኒስቴር
7. የገንዘብ ሚኒስቴር
8. የገቢዎች ሚኒስቴር
9. የፕላንና ልማት ሚኒስቴር
10. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
11. የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር
12. የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር
13. የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
14. የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር
15. የትምህርት ሚኒስቴር
16. የጤና ሚኒስቴር
17. የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
18. የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
19. መከላከያ ሚኒስቴር
20. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
21. የፍትህ ሚኒስቴር
22. የሰላም ሚኒስቴር

#FBC
#የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ ይከበራል፡፡

ሰመራ- ጥቅምት 1፣ 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ ይከበራል፡፡

"በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል 14ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ ለ14 ጊዜ ይከበራል፡፡

ሰንደቅ ዓላማ የብሔራዊ አንድነት መገለጫ፤ የአንድ ሀገር ዜጎች ሀገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜትን የሚገልፁበት፤ ታሪካዊ ትስስርና ስነ-ልቦናዊ አንድነት የሚንፀበረቁበት የሀገራዊ አንድነትና ህብረት አርማና ምልክት ነው፡፡

በመሆኑም ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንዲከበር በህግ ተደንግጓል፡፡

በዓሉ ዛሬ ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት በፌዴራል፣ በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደር ም/ቤቶች ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል እና በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ በመፈፀም እንዲሁም በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡

የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል የሚከበረው በአንድ በኩል 6ኛው አገር አቀፍ ብሄራዊ ምርጫ ተካሂዶ በምርጫው ውጤት መሰረትም አዲስ ፓርላማ እና የመንግስት ምስረታ በተካሄደበት ማግስት እና በኢትዮጵያ እውነተኛ ዴሞክራሲ ለመገንባትና ብልፅግናን ለማምጣት አዲስ ምእራፍ በጀመርንበት ወቅት በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው የተወካዮች ምክር ቤት አመልክቷል፡፡

በሌላ መልኩ የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን ብሔራዊ አንድነታችንን እና ሉዓላዊነታችንን እየተፈታተኑ ባሉበት በዚህ ወቅት የሰንደቅ ዓላማ በዓሉን ማክበር፤ ተናበንና ተደራጅተን በተባበረ ክንድ የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ ለመመከትና ለመቀልበስ ፤ ለብሔራዊ አንድነታችንና ሉአላዊነታችን ያለንን ቁርጠኝነት በባንዲራችን ፊት ዳግም ቃላችንን የምናድስበት እለት ነውም ብሏል ምክር ቤቱ፡፡

የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መሪነት በመላው ኢትዮጵያ በፌደራል የመንግስት ተቋማት፣ በክልሎችና በሁለቱም አስተዳደር ከተሞች ፣ የመከላከያ ሰራዊት ካምፖች እንዲሁም በኢምባሲዎችና የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች በተመሳሳይ ሰዓት እንደሚከበር ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

#FBC
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#የተመረጡና የነጠሩ የአየር ኃይል እርምጃዎችና ጠቀሜታው።

#FBC
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሽብርተኛው ትህነግ የጠቀለለው ትጥቅና የሰው ኃይል ሰንሰለት፣፣

#FBC
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#በወረኢሉ፣ አጣዬ፣ ጭፍራና ቡርካ ግንባሮች የተማረኩ፣፣

#FBC
#የህወሃት የሽብር ቡድን በአዲስ አበባ እና በዙሪያው ለሽብር ተግባር ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፣፣

ሰመራ-ህዳር 14፣ 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የህወሃት የሽብር ቡድን በአዲስ አበባ እና በዙሪያው ለሽብር ተግባር ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

በከተሞች በህብረተሰቡ ውስጥ በተለያዩ መንገዶች በመመሳሰል እንዲገቡ በማድረግ አዲስ አበባ እና በዙሪያው ተልእኮ ሰጥቶ በማስገባት ለሽብር ተግባር እየተንቀሳቀሱ መሆኑን እንደተደረሰበት የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ ገልጸዋል።

የሽብር ቡድን አባላቱን በንግድ ተቋማት፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና በሌሎችም የሙያ ስራዎች ህብረተሰቡ ውስጥ ተሰግስገው እንዲገቡ በማድረግ አዲስ አበባን እና አካባቢውን ለማተራመስ አቅዶ እየሰሩ መሆኑ ተደርሶበት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በዚህም ቡድኑ ለሽብር ተልእኮ ያሰማራቸው በርካታ ግለሰቦች በርካታ ተተኳሽ ጥይቶች ከነፍስ ወከፍ እና የቡድን የጦር መሳሪያ ማለትም ቦንቦች ተቀጣጣይ ፈንጂዎች እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ገንዘቦችን ይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አብራርተዋል።

የተለያዩ የክልል እና የፌዴራል የፀጥታ መዋቅራት አልባሳትን ከነአርማው በማልበስና የተለያዩ የጦር ሜዳ ንድፍ መነፅር እና ሌሎችንም ቁሳቁሶችን በመጠቀም አሳሳስቶ ለመልበስ መሞከሩን ፖሊስ ባደረገው ፍተሻ ማገኘቱን ገልጸዋል።

ሀሰተኛ መታወቂያ ለማዘጋጀት የሚያገለግሉ ማህተሞችንና ቁሳቁሶችም ተይዘዋል ተብሏል።

ይሄንን ሃይል መንጥሮ ማውጣቱ የፀጥታ ግብረ ኃይሉ ዋነኛ ተግባር ቢሆንም የከህብረተሰቡ ድጋፍ አሁንም ከተጀመረው በላይ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ህብረተሰቡ ፀጉረ ልውጠችን ሲያይ በመጠቆም የያዘውን መታወቂያ ትክክለኛነት ማጣራትም አለበት በማለት ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ አክለዋል።

#FBC

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!
ሰበር ዜና

የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት መርሳና ግራናን በመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሠ ነው፡፡

የአትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በቆቦ ግንባር ቀደም ብሎ የዞብል ከፍተኛ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ የነበረ ሲሆን፣ በራያ ሰሜናዊ አቅጣጫ ያሉትን ከፍተኛ ቦታዎችን ጨምሮ ተቆጣጥሯል፡፡ በዞብል ደቡብ አቅጣጫ ደግሞ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ የነበረው የወገን ጦር አሁን ደግሞ የጉራ ወርቄ ከፍተኛ ሰንሰለታማ ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ በማጽዳት፣ ቀደም ብሎ የተቆረጠውን የወልድያ መቀሌ መሥመር አሰፋፍቶ፣ ወደ ወልድያ በቅርብ ርቀት እየገሠገሠ ይገኛል፡፡

ባለፈው ጊዜ ውጫሌ ከተማን ነጸ ያወጣው የወገን ጦር፣ በዚሁ ግንባር የውጫሌ ወረዳን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የውርጌሳ፣ የሊብሶ፣የግራና፣የመርሳ፣የኪሌ፣ከተሞችንና በሰሜን ወሎ የሐርቡ ወረዳን ከፍተኛ ሰንሰለታማ ተራሮችን በእጁ አስገብቷል፡፡

በእነዚህ የማጥቃት እንቅስቃሴዎች ጀግኖቹ የወገን ጥምር ጦር በንሥሮቹ አየር ኃይላችን በመታገዝ ጠላትን ከመርሳ በስተጀርባ ቆርጦ በመግባት፣ በውጫሌና ውርጌሳ መካከል የነበረውን ጠላት ሙለሉ በሙሉ ደምስሰውታል፤ ምርኮኛና ቁስለኛም አድርገውታል፡፡ የአካባቢ ኅብረተሰብ ከወገን ጥምር ጦር ጋር በመቀናጀት፣ እግሬ አውጪኝ ብሎ የሚሸሸውን ጠላት ከየጢሻው እየመነጠረ በመደምሰስ አኩሪ ጀብድ ፈጽሟል፡፡ ጠላትም የዘረፈውን ንብረትና ተተኳሾቹን ፈጽሞ ይዞ እንዳይወጣ አድርጎታል፡፡

የወገን ጥምር ጦር በወልድያና ሐራ ከተሞች መካከል የሚገኘውንና መውጫ ያጣውን ጠላት ለመደምሰስ፣ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ወደ ፊት እየገሠገሠ ነው፡፡

#FBC
#ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሰጣቸው

ሰመራ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሰጣቸው።

ዛሬ በተካሄደ ስነስርዓት ፥ ውጊያ ለመሩ ፣ ሀይል ለመሩ ፣ ድልና ውጤት ላስገኙ ከፍተኛ የጦሩ መኮንኖች በየደረጃው የማዕረግ ዕድገት ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት 1 የፍልድ ማርሻል ማዕረግ ፣ 4 የሙሉ ጀነራል ማዕረግ ፣ 14 የሌተናል ጀነራል ማዕረግ፣ 24 የሜጀር ጀነራል ማዕረግ እና 58 የብርጋዴር ጀነራል ማዕረግ ተሰጥቷል።

የጀነራል መኮንኖቹ ሹመት በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አሕመድ አቅራቢነት በርዕሰ ብሄር ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ነው የተሰጠው።

#FBC
#Leedâ Missoyna Fantí Makaadoh Dooro Gexisak Geytinta.

Samara-Qado dirrik 03, 2014 (AFMMA)

Leedâ Missoyna Fantí Makaadoh Dooro Gexisak Geytinta.

Asaaku Sidoc haytoh ayroh gexsitak geytinta Leedâ Missoynak Inik heele Amolladí Koboxul awakih uddur Missoynak Fantí Makaadoh adoytit doorak geytiman.

225 Adoyta alle-leemit kak yaaban tama Makaadoh adoytiitih dooro Qidi lennal akkelem Kee dooran mari Ityoppiyiinol yaamineeh, agat Kee agattinaaneh inkittinaanel yaamineeh, Garqiino Kee Umaadoobal yangiicille Mara takkem faxxintam warsan.

Fantí Makaadoh Dooro tekkeek lakal, Taama Selta Makaadoh adoytit Fantí Makaadoh addak doorimelem timixxigeh tan.

Illacabol, Missoynak Inispekshin Kee Meqem Kaban Komishinih adoytit Doore loonum warsan.

#FBC

#QafárTV
#የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጠቅላላ ጉባዔ እና የስራ አስፈጻሚ አባላትን መረጠ፣፣

ሰመራ፣ ሐምሌ11፣ 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጠቅላላ ጉባዔ እና የስራ አስፈጻሚ አባላትን መረጠ።

ጠቅላላ ጉባዔው ሸኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን በፕሬዚዳንትነት፣ ሸኽ አብዱልከሪም ሸኽ በድረዲን እና አብዱልዐዚዝ አብዱልወሌን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲሁም ሸኽ ሀሚድ ሙሳን በዋና ፀሐፊነት መርጧል።

በጉባኤው እንደተገለፀው፥ ሚያዚያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥና አንድነት አገር አቀፍ ጉባዔ የተመረጠው ኮሚቴ በስድስት ወራት ውስጥ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ አመራሮችን እንዲያስመርጥ ኅላፊነት ቢሰጠውም ኅላፊነቱን ሳይወጣ ለሶስት ዓመት ከስድስት ወር ቆይቷል።

በወቅቱ የተመረጠው ኮሚቴ ኅላፊነቱን ባለመወጣቱ ጉዳዩ ወደ መደበኛው ጉባዔ እንዲመጣ በተወሰነው መሰረት ዛሬ ለሁለተኛ ዙር አገር አቀፍ ጉባኤ ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ተወካዮች በተገኙበት መካሄዱ ነው የተገለፀው።

በጉባኤው ላይ በድምፅ ይሳተፋሉ ተብለው ከሚጠበቁት 300 ተሳታፊዎች መካከል 261ዱ ተገኝተዋል።

ሚያዚያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በተካሄደው ጉባኤ ከተሳተፉት መካከል 39ኙ በሞት፣ በህመም፣ ከሀጂ ጉዞ ባለመመለስና በልዩ ልዩ ምክንያቶች በዛሬው ጉባኤ አለመገኘታቸውም ታውቋል።

ጉባዔውን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የኅይማኖት አባቶች ስለምርጫው ሂደቱ ማብራሪያና የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በጉባዔው ምርጫ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ የምርጫ መስፈርቶች ለጉባዔው በንባብ ቀርበዋል።

በዛሬው ጉባዔ መጂሊሱን ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የሚመሩ አመራሮች ምርጫ ተካሂዶ የሚከተሉት 14 ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ተመርጠዋል።


1. ሸኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ

2. ሸኽ አብዱልከሪም ሸኽ በድረዲን

3. ሸኽ አልመርዲ ዐብዱላሂ

4. ሸኽ ሀሚድ ሙሳን

5. ሸኽ እድሪስ ዓሊይ ሁሴን

6. ሸኽ አብዱልዐዚዝ አብዱልወሌ

7. ሸኽ መሀመድ አህመድ ያሲን

8. ሸኽ አሚን ኢብሮ

9. ኢንጂኔር አንዋር ሙስጠፋ

10. ሸኽ አብዱልሃሚድ አህመድ

11. ሀጂ ሙስጠፋ ናስር

12. ሸኽ ዛኪር ኢብራሂም

13. ሸኽ ሁሴን ሀሰን

14. ሸኽ መሀመድ አሚን ሰይድ

ከስራ አስፈጻሚ አባላቱ መካከልም ሸኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን በፕሬዚዳንትነት፣ ሸኽ አብዱልከሪም ሸኽ በድረዲን እና አብዱልዐዚዝ አብዱልወሌን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲሁም ሸኽ ሀሚድ ሙሳን በዋና ፀሐፊነት መምረጡን ነው የኢዜአ ዘገባ የሚያመለክተው።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ሸኽ ኢብራሂም ቱፋ ባስተላለፉት መልዕክት ምርጫው ከየትኛውም አካል ጣልቃገብነት በጸዳ አግባብ በነጻነት ታሪካዊ ምርጫ እንደሆነ ተናግረዋል።

ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ታላቅ ኅላፊነት የተሰጣቸው መሆኑን የገለጹት ሸኽ ኢብራሂም ቱፋ፥ በተለይም የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት በማስጠበቅ ረገድ በትኩረት እንደሚሰሩ አረጋገጠዋል።

ህዝበ ሙስሊሙም ከጎናቸው እንዲቆም እና በጸሎት እንዲያግዛቸውም ነው ጥሪ ያቀረቡት።

የምርጫው ታዛቢዎች በበኩላችው ምርጫው ገለልተኛ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደትን የተከተለ ታሪካዊና ትክክለኛ ምርጫ ሂደት እንደነበር ገልጸዋል።

#FBC