Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ ይከበራል፡፡

ሰመራ- ጥቅምት 1፣ 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ ይከበራል፡፡

"በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል 14ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ ለ14 ጊዜ ይከበራል፡፡

ሰንደቅ ዓላማ የብሔራዊ አንድነት መገለጫ፤ የአንድ ሀገር ዜጎች ሀገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜትን የሚገልፁበት፤ ታሪካዊ ትስስርና ስነ-ልቦናዊ አንድነት የሚንፀበረቁበት የሀገራዊ አንድነትና ህብረት አርማና ምልክት ነው፡፡

በመሆኑም ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንዲከበር በህግ ተደንግጓል፡፡

በዓሉ ዛሬ ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት በፌዴራል፣ በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደር ም/ቤቶች ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል እና በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ በመፈፀም እንዲሁም በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡

የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል የሚከበረው በአንድ በኩል 6ኛው አገር አቀፍ ብሄራዊ ምርጫ ተካሂዶ በምርጫው ውጤት መሰረትም አዲስ ፓርላማ እና የመንግስት ምስረታ በተካሄደበት ማግስት እና በኢትዮጵያ እውነተኛ ዴሞክራሲ ለመገንባትና ብልፅግናን ለማምጣት አዲስ ምእራፍ በጀመርንበት ወቅት በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው የተወካዮች ምክር ቤት አመልክቷል፡፡

በሌላ መልኩ የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን ብሔራዊ አንድነታችንን እና ሉዓላዊነታችንን እየተፈታተኑ ባሉበት በዚህ ወቅት የሰንደቅ ዓላማ በዓሉን ማክበር፤ ተናበንና ተደራጅተን በተባበረ ክንድ የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ ለመመከትና ለመቀልበስ ፤ ለብሔራዊ አንድነታችንና ሉአላዊነታችን ያለንን ቁርጠኝነት በባንዲራችን ፊት ዳግም ቃላችንን የምናድስበት እለት ነውም ብሏል ምክር ቤቱ፡፡

የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መሪነት በመላው ኢትዮጵያ በፌደራል የመንግስት ተቋማት፣ በክልሎችና በሁለቱም አስተዳደር ከተሞች ፣ የመከላከያ ሰራዊት ካምፖች እንዲሁም በኢምባሲዎችና የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች በተመሳሳይ ሰዓት እንደሚከበር ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

#FBC