Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#የህወሃት ጁንታ አስቦት የነበረው ሀገር የማፍረስ ህልም ከሽፏል- የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት::

ሰመራ-አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት፣ህዳር 20 ፣ 2013

የህወሃት ጁንታ አስቦት የነበረው ሀገር የማፍረስ ህልም ከሽፏል- የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት::
የህወሃት ጁንታ አስቦት የነበረው ሀገር የማፍረስ ህልም መክሸፉን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ገለጸ።

የህወሓት ጁንታ ለመቆጣጠር እስካሁን በተመዘገበው ድልም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

ከሌሎች የመረጃና ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የጁንታውን ድብቅ ሴራ በማጋለጥ ለህግ ለማቅረብ በሚደረገው ጥረትም ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሰራ መሆኑን በመግለጫው አመልክቷል።

በስግብግቡ የጁንታ ላይ የተገኘው አኩሪ ድል የመላው የአገራችን ህዝቦች በተለይም ደግሞ የትግራይ ህዝብ አኩሪ የትግል ውጤት በመሆኑ ተቋሙ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

የህወሓት ስግብግብ ጁንታ በፖለቲካው አውድ የደረሰበትን ሽንፈት ተከትሎ ትግራይ ክልል በመመሸግ ህገወጥ ተግባራትን ሲፈፅም ቆይቷልም ብሏል የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በመግለጫው።

ጁንታው የሰሜን ዕዝ የሰራዊቱ አባላትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት በመፈጸም እንዲሁም በአማራ ክልል ህዝቦች ላይ ግልፅ ጦርነት በማወጅ የአገርን ብሄራዊ ደህንነትና ጥቅም በሚጻረር ከፍተኛ ክህደት መፈፀሙንም በመግለጫው አመልክቷል።

ቡድኑ ጦርነቱን የጀመረው በግልፅ፣ በተደራጀ እና በከዳተኛ አባሎቹ ጭምር ተገቢ ጥናት ፈፅሞ የሰራዊቱን ቁልፍ ትጥቆች፣ ስንቆች፣ የማዘዣ ጣቢያዎችና የዕዝ ሰንሰለቶች ለመቆጣጠርና ለመበጣጠስም በማለም መሆኑን ጠቅሷል።

ይሁን እንጂ ህልሙ ሙሉ በሙሉ ባሰበው ልክ አልተሳካለትም፣ ከሽፏል፣ ያሳካው ነገር ቢኖር ትውልድ ይቅር የማይለው አሳፋሪ እና አስነዋሪ ታሪክ ማስመዝገብ ነው ብሏል።

የስግብግብ ጁንታ ህልም እንዳይሳካ በራሱ የግንኙነት ኔትወርክ ውስጥ ሰርጎ በመግባት፣ ተባባሪ አካላትና አባላትን፣ የወገንን ኃይል እንዲሁም ሰላም ወዳዱን የትግራይ ህዝብ በመጠቀም መረጃ በመሰብሰብና በመተንተን ለተመዘገበው ድል ድጋፍ ማድረጉንም አመልክቷል።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሌሎች የመረጃና የፀጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የጁንታው ድብቅ ሴራ እንዳይሳካ ማክሸፉንም ገልጿል።

#ምንጭ: OBN
#የህወሃት ጁንታ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክሉ የእዙ የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ተለቀቁ::

አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት- ህዳር 30/2013

የህወሃት ጁንታ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክሉ የእዙ የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ተለቀቁ::

የህወሃት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያህል የሰሜን እዝ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖችን የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በሰሩት የጋራ አሰሳ አስለቀቁ።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሃመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት የህውሃት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ የእራት ግብዣ ብሎ ከጠራ በኋላ አፍኖ በመውሰድ አግቷቸው ቆይቷል።

የጁንታው ሃይል መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖችን በሸሸበት ቦታ ሁሉ ይዟቸው ሲጓዝ ቆይቶ በቀድሞው የትጥቅ ትግል ወቅት የማዘዣ ቤዝ በነበረው አዴት በሚባል ቦታ አግቷቸው እንደነበርና የጁንታው ታጣቂ ሃይል መደበቁ በአሰሳና በጥናት ተደርሶበታል።

በዚሁ መሰረት የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ባደረጉት የጋራ አሰሳ እና እርምጃ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጁንታው አስለቅቀዋል።

ሰራዊቱ ያስለቀቃቸው 1 ሺህ ያክል የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች አሁን ላይ ሰራዊቱን መቀላቀላቸውን ሜጀር ጀነራል መሀመድ ገልጸዋል።

ሰራዊቱ ከጁንታው ካስለቀቃቸው መካከል የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴም ይገኙበታል።

የጁንታውን አባላት የማደን ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹት ሜጀር ጀነራል መሀመድ፤ የመጨረሻ ምእራፍ በሆነው ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ምእራፍ የተደበቀውን ጁንታ አስሶ የመያዙ ስራ በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ የጋራ ቅንጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

ወደፊትም የጁንታውን ቡድንና ወንጀለኞቸን ለህግ የማቅረብና የማደን ስራ ውጤት በየጊዜው ለህዝብ እንደሚገለፅ ጨምረው ገልጸዋል።

#ENA
#የህወሃት የሽብር ቡድን በአዲስ አበባ እና በዙሪያው ለሽብር ተግባር ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፣፣

ሰመራ-ህዳር 14፣ 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የህወሃት የሽብር ቡድን በአዲስ አበባ እና በዙሪያው ለሽብር ተግባር ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

በከተሞች በህብረተሰቡ ውስጥ በተለያዩ መንገዶች በመመሳሰል እንዲገቡ በማድረግ አዲስ አበባ እና በዙሪያው ተልእኮ ሰጥቶ በማስገባት ለሽብር ተግባር እየተንቀሳቀሱ መሆኑን እንደተደረሰበት የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ ገልጸዋል።

የሽብር ቡድን አባላቱን በንግድ ተቋማት፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና በሌሎችም የሙያ ስራዎች ህብረተሰቡ ውስጥ ተሰግስገው እንዲገቡ በማድረግ አዲስ አበባን እና አካባቢውን ለማተራመስ አቅዶ እየሰሩ መሆኑ ተደርሶበት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በዚህም ቡድኑ ለሽብር ተልእኮ ያሰማራቸው በርካታ ግለሰቦች በርካታ ተተኳሽ ጥይቶች ከነፍስ ወከፍ እና የቡድን የጦር መሳሪያ ማለትም ቦንቦች ተቀጣጣይ ፈንጂዎች እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ገንዘቦችን ይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አብራርተዋል።

የተለያዩ የክልል እና የፌዴራል የፀጥታ መዋቅራት አልባሳትን ከነአርማው በማልበስና የተለያዩ የጦር ሜዳ ንድፍ መነፅር እና ሌሎችንም ቁሳቁሶችን በመጠቀም አሳሳስቶ ለመልበስ መሞከሩን ፖሊስ ባደረገው ፍተሻ ማገኘቱን ገልጸዋል።

ሀሰተኛ መታወቂያ ለማዘጋጀት የሚያገለግሉ ማህተሞችንና ቁሳቁሶችም ተይዘዋል ተብሏል።

ይሄንን ሃይል መንጥሮ ማውጣቱ የፀጥታ ግብረ ኃይሉ ዋነኛ ተግባር ቢሆንም የከህብረተሰቡ ድጋፍ አሁንም ከተጀመረው በላይ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ህብረተሰቡ ፀጉረ ልውጠችን ሲያይ በመጠቆም የያዘውን መታወቂያ ትክክለኛነት ማጣራትም አለበት በማለት ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ አክለዋል።

#FBC

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!