Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ ከታህሳስ እስከ ጥር ባሉት ጊዜያት የመራጮች ምዝገባ እንደሚካሄድ ተገለጸ

Afar Mass Media-ጥቅምት 20, 2013

ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ ከታህሳስ እስከ ጥር ባሉት ጊዜያት የመራጮች ምዝገባ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ ከታህሳስ እስከ ጥር ባሉት ጊዜያት የመራጮች ምዝገባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ በሚከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ከሲቪክ እና ከመገናኛ ብዙሃን አባላት ጋር እየመከረ ነው።

በምክክር መድረኩ መክፈቻ ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንደተናገሩት ከታህሳስ እስከ ጥር ወር 2013 ዓ.ም ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች መዝግባ ይካሄዳል።

"ከጥር የመጀመሪያው ሳምንት እስከ የካቲት አጋማሽ ደግሞ የእጩዎች ምዝገባ እንዲሁም ከየካቲት አጋማሽ ጀምሮ የምረጡኝ ቅሰቀሳ ይጀመራል" ሲሉም ተናግረዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ እና በምርጫ ሂደት ስለሚወሰዱ የኮቪድ-19 የጥንቃቄ እርምጃዎችን በተመለከተ ከሲቪክ ማህበራት እና ከመገናኛ ብዙሃን አባላት ጋር በመወያየት ግብዓት ይወሰዳል ተብሏል።

በተጨማሪም ሲቪክ ማህበራት አና መገናኛ ብዙሃንን የሚመለከቱ ዋና ዋና የምርጫ እንቅስቃሴዎች እና ዝግጅቶች ላይ ውይይት እንደሚደረግም ነው የተገለጸው።

እንደ ወይዘሪት ብርቱካን ገለጻ፣ መድረኩ የተዘጋጀው የሲቪክ ማህበራት እና የመገናኛ ብዙሃን የሚያነሷቸውን ሀሳቦች በመጨረሻ ለሚወጣው የምርጫ ጊዜ ሰለዳ እና የአፈጻጸም ዕቅድ ላይ በግብዓትነት ለመጠቀም ታስቦ ነው።

በመድረኩ በምርጫ ሂደት የሚተገበሩ የኮቪድ-19 የጥንቃቄ መመሪያ መነሻ ሀሳቦች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።

በተጨማሪም ዋና ዋና የምርጫ ተግባራት በሚተገበሩበት ጊዜ የሲቪክ ማህበራት እና የመገናኛ ብዙሃን ያላቸውን ሚና የተመለከቱና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

#ENA
#የሀሰት መረጃን ስለማጋለጥ!
የኢትዮጵያ አየር ኃይል አውሮፕላን በዘራፊው የሕውሐት ቡድን እንደተመታ ተደርጎ በዚህ ቡድን ደጋፊዎች በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው ምስል ፍፁም ሐሰት ነው።
የሀሰቱ ምስል የተወሰደው የዛሬ ዓመት ከቢሸፍቱ አየርኃይል ግቢ ለልምምድ በረራ የተነሳና ሞተሩ ላይ ባጋጠመው ችግር በተነሳ በደቂቃዎች ውስጥ የወደቀውን አውሮፕላን ነው።
በሌሎች ሀገራት ያጋጠሙ የአውሮፕላን አደጋዎችም ለዚህ የሀሰት ወሬ ማጀቢያ ጥቅም ላይ ውለዋል።
ሀሰተኛ ምስሎችን እነዚህን የማረጋገጫ መንገዶች በመጠቀም ይለዩ!
የትና መቼ ጥቅም ላይ እንደዋሉ ይነግርዎታል።
Yandex.com
• Tine Eye.com
• Foto Forensic.com
• Googel image


#AFMMA, 27/02/2013

#ENA
#EBC
ጽንፈኛው የህወሃት ቡድን የተከዜ ግድብ ተደብድቧል ሲል ያሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው–የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት-ህዳር 6/2013

ጽንፈኛው የህወሃት ቡድን የተከዜ ግድብ ተደብድቧል ሲል ያሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው–የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን “የተከዜ ኃይል ማመንጫ ግድብ በጦር ጄት ተደብድቧል” ሲል ያሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

የጽንፈኛው የህወሓት ቡድን መሪ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በቅርቡ በሰጡት መግለጫ “የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተከዜ ኃይል ማመንጫ ግድብን ደብድቧል” ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን ዛሬ ለኢዜአ እንደተናገሩት፣ ጽንፈኛው ቡድን ግድቡን በሚመለከት የተሳሳተ መረጃ እያሰራጨ ይገኛል።

የቡድኑ ታጣቂዎች ከቀናቶች በፊት ግድቡን በኃይል ለመቆጣጠር በማለም በጥበቃ ሥራ በተሰማሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላቶች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን አስታውሰዋል።

“ጥቃቱን ለመፈጸም በከፈቱት ተኩስ በግድቡ የኃይል ማስተላለፊያ ስዊች ላይ ጉዳት አድርሰዋል” ነው ያሉት።

በአሁኑ ወቅትም የቡድኑ አፈ-ቃላጤዎች የኃይል ማመንጫ ግድቡ በኢትዮጵያ የጦር ጄት እንደተደበደበ አድርገው የሀሰት መረጃ እያሰራጩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የጽንፈኛ ቡድኑ ታጣቂዎች የኃይል ማስተላለፊያ ‘ስዊች’ ላይ ካደረሱት ጥቃት ውጪ በግድቡ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን አብራርተዋል።

ግድቡ የያዘው 9 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሊትር ውሃ መደበኛ ፍሰቱን ጠብቆ ወደታችኛው ተፋሰስ እየወረደ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ “ይህም ቡድኑ ስለግድቡ ያሰራጨው መረጃ ሀሰት ስለመሆኑ ማሳያ ነው” ብለዋል።

ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን ይህን የሀሰት መረጃ የሚያሰራጨው ግድቡ በግንባታ ላይ እያለ የተነሱ ፎቶዎችን በመጠቀም መሆኑን ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።

በአሁኑ ወቅት ህብረተሰቡ ጽንፈኛ ቡድኑ በየጊዜው የሚያሰራጫቸው የሀሰት መረጃዎችና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በትክከል እየተረዳ በመሆኑ የጥፋት ቡድኑ ተስፋ ወደመቁረጥ እየተሸጋገረ መሆኑንም አመልክተዋል።

ከዚህ አንጻር ቡድኑ ስለ ተከዜ ግድብ በተደጋጋሚ የሀሰት መረጃ ማሰራጨቱ ምናልባትም በግድቡ ላይ የተሰፋ መቁረጥ ጥቃት ለመሞከር ዕቅድ እንዳለው እንደሚያመላክት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

#ENA
#የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው የህወሃት አመራሮች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ:

አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት-ህዳር 10/2013

የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው የህወሃት አመራሮች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ

የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው የህወሃት አመራሮች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ እና ተጨማሪ ግፍ ከመፈፀም እንዲታቀቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የህወሃት ቡድን ታጣቂዎች እንደ ማይካድራ ባሉ ቦታዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘገብ ቆይቷል፡፡

ይህ ቡድን ባለፉት ዓመታት ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የተቀናበሩ የወንጀል ድርጊቶችን ሲፈፅም ቆይቷል፡፡

በመሆኑም የፌዴራል መንግስት በእነዚህ የጥፋት ድርጊቶች ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍርድ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጧል፡፡

በትግራይ ክልል የተጀመረው የሕግ የባለይነትን የማስከበር ስራ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ የህወሃት ቡድን እንደ ማይካድራ ባሉ ቦታዎች ላይ የፈጸመው ድርጊት በኢትዮጵያ ሕግም ሆነ በአለም አቀፍ ሕግ በወንጀል ሊያስጠይቁ የሚችሉ ጥፋቶች መሆናቸው ቡድኑ ሊገነዘብ ይገባል ነው የተባለው።

ምንጭ-የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ

#ENA
#የህወሃት ጁንታ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክሉ የእዙ የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ተለቀቁ::

አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት- ህዳር 30/2013

የህወሃት ጁንታ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክሉ የእዙ የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ተለቀቁ::

የህወሃት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያህል የሰሜን እዝ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖችን የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በሰሩት የጋራ አሰሳ አስለቀቁ።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሃመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት የህውሃት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ የእራት ግብዣ ብሎ ከጠራ በኋላ አፍኖ በመውሰድ አግቷቸው ቆይቷል።

የጁንታው ሃይል መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖችን በሸሸበት ቦታ ሁሉ ይዟቸው ሲጓዝ ቆይቶ በቀድሞው የትጥቅ ትግል ወቅት የማዘዣ ቤዝ በነበረው አዴት በሚባል ቦታ አግቷቸው እንደነበርና የጁንታው ታጣቂ ሃይል መደበቁ በአሰሳና በጥናት ተደርሶበታል።

በዚሁ መሰረት የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ባደረጉት የጋራ አሰሳ እና እርምጃ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጁንታው አስለቅቀዋል።

ሰራዊቱ ያስለቀቃቸው 1 ሺህ ያክል የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች አሁን ላይ ሰራዊቱን መቀላቀላቸውን ሜጀር ጀነራል መሀመድ ገልጸዋል።

ሰራዊቱ ከጁንታው ካስለቀቃቸው መካከል የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴም ይገኙበታል።

የጁንታውን አባላት የማደን ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹት ሜጀር ጀነራል መሀመድ፤ የመጨረሻ ምእራፍ በሆነው ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ምእራፍ የተደበቀውን ጁንታ አስሶ የመያዙ ስራ በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ የጋራ ቅንጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

ወደፊትም የጁንታውን ቡድንና ወንጀለኞቸን ለህግ የማቅረብና የማደን ስራ ውጤት በየጊዜው ለህዝብ እንደሚገለፅ ጨምረው ገልጸዋል።

#ENA
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ተኛውን አገር አቀፍ የመጨረሻ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ::

ሰመራ-አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት-ታህሳስ 30/2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛውን አገር አቀፍ የመጨረሻ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።

ቦርዱ ታኅሣሥ 16 ቀን 2013 ዓ.ም የቦርዱ አመራሮችና ፖለቲካ ፓርቲዎች በተገኙበት የመጪው አገር አቀፍ ምርጫን ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ለውይይት አቅርቦ እንደነበር አውስቷል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አቅርበው፣ ቦርዱ እጩዎችን ለማቅረብ የሚያስፈልገውን ፊርማ የሕግ መስፈርት ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ ብቻ አገልግሎት ላይ እንዳይውል የተወካዮች ምክር ቤትን ጠይቋል።

በዚህም መሠረት የመጨረሻው የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ይፋ አድርጓል።

በዚሁ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የተግባራቱ አፈጻጸም ያሉበትን ሁኔታ እንደሚያሳውቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

#ENA
#Juntâ Qarkakisah Adoytit Desê Dariifak Kutaaberrii Kee Tewle-xerri Deqsita Aroocal Doolat Qandel Gaba Acayuk Geytiman.

Samara-Kaxxa garabluk 19, 2014 (AFMMA)

Juntâ Qarkakisah Adoytit Desê Dariifak Kutaaberrii Kee Tewle-xerri Deqsita Aroocal Doolat Qandel Gaba Acayuk Geytiman.

Warrayte nammaah Sidooca ayroh addat Agatak Kalalí Qandeey, Amcarak Baxsa le Caylaay, Miliishiyaa Kee Fanno inkittinaanel Baxsa le maaqatta elle beyak temeeteh tan Juntâ Qarkakisak mangom rabteeh, dorrit kee Coox fanat tommooqoreh sugtem niya tirgeqeek lakal isinni Qawwaddí catoonuh gaba acayuk geytiman.

Ethiopian News Agency (ኢዚኣ) oyti elle yascassennal Sidiica ayrok dumal Dese nibbixeh inta dirab farmooma ruubak ummatta wayyalisak sugte Juntâ Qarkakisa maadde aroocaak bisoh axce waytuuy, Darreh andabbe waytuh Qaran kee Ardih teetil been maaqattal Caxak ixxim elle radannal ardil radak geytiman.

Dessie Kee Kombolcha lowsis gubat hayya heeh Khamiise gexxa buttaa Kee Baatiik Milleh Asfalti tabbixe butta abeyyo inta loqô soonol gexak temeete Juntâ Qarkakisa Cato elle gee sinniih, catu elle alle-sinni Marin baaxoh addal Baaxoh alluwwah maaqo akkuk geytinta.

Diraabal orqonteeh, dirab gexsitih le Juntâ Qarkakisa teetik akkuk geytima finqaa Kee Cabaarut yabtaamak uxi kinnih Dessie lowsis gubat hayneh inta diraabitte baxcisak Carbil tefferem Arraabat orbissak gibbatak geytinta.

#Ityoppiya Aysele

#ENA+Government Communication Service
#አሸባሪው ሕወሃት በህዝብ ማዕበል ስም ለሞት የዳረገውን ወጣት ለሌላ የፈጠራ ክስ “የሁመራ እልቂት” በሚል አሰናድቶቷል

ሰመራ-ህዳር 13/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

አሸባሪው ሕወሃት ከግበረ አበሮቹ ሚዲያዎችና ተቋማት ጋር “የሁመራ እልቂት” ለሚል የፈጠራ ክስ ተሰናድቷል።

አሸባሪው ህወሃት ለዚህ የፈጠራ ክሱ ያሰናዳው በህዝብ ማዕበል ስም መስዋዕት ያደረገውን ህዝብ እንደሆነም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና የተመድ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጋራ ያደረጉት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድርጊት ምርመራ አሸባሪው ህወሃት “የአክሱም እልቂት” ሲል ያቀረበው ክስ ሀሰተኛ እና ፈጠራ መሆን መገለጹ ይታወሳል።

ይልቁንም አሸባሪው በወረራቸው አካባቢዎች በዜጎች ላይ ጭፍጨፋ ማድረጉና በመከላያ ሠራዊት አባላት ላይ ግድያ መፈጸሙ ነው የተየተረጋገጠው።

ኢዜአ ከምንጮቹ ባገኘው መረጃ መሰረት ደግሞ በፈጠራ ስራና ሐሰተኛ ትርክት ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር አሸባሪው ህወሃት ከአጋሮቹ ጋር በመሆን “የሁመራ እልቂት” በሚል ክስ ብቅ ሊል መሆኑ ተሰምቷል።

ለዚህ የፈጠራ ክሱ የተዘጋጁት የሳይበር ሰራዊቶቹ ጉዳዩን በስፋት በማራገብ ነጭ ውሸታቸው እውነት እስኪመስል ድረስ ዘመቻ ለማካሄድ መዘጋጀታቸውም ተነግሯል።

ቡድኑ ለዚህ የፈጠራ ክሱ እንዲሆነው ለጥይት ማብረጃነት የተጠቀማቸውን ሰዎች አስከሬን ማሰናዳቱም ተገልጿል።

ለዚህ የፈጠራ ክስ ከዚህ ቀደም የአሸባሪውን የፈጠራ ተውኔቶች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደርጉ የነበሩት እንደ ሲኤንኤን ያሉ ሚዲያዎች እየተዘጋጁ መሆኑም ተሰምቷል።

በተለይም አሸባሪው በህዝብ ማዕበል በመላክ ለሞት የተዳረገውን ወጣት ሬሳ በተከዜ ወንዝ አካባቢ በመሰብሰብ “የሁመራ እልቂት በማለት” የፈጠራ ክሱንና ድራማውን ሊሰራ መሆኑ ታውቋል።

ለዚህ ክስ በጎረቤት ሃገር ሱዳን የተሰባሰቡ ጋዜጠኞች ጉዳዩን ለማራገብና እውነት መስሎ እንዲታይ ለማድረግ ከሽብር ቡድኑ ጋር ዝግጅት ላይ ናቸው።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።

#ENA
#በአሸባሪው ህወሃት ወራሪ ውድመት የደረሰባቸውን የውሃና መብራት መሰረተ ልማቶችን በፍጥነት መልሶ ለመገንባት በጥናት ላይ የተመሰረተ ማስተካከያ ይደረጋል - ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ

ሰመራ-ታህሳስ 08/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

በአሸባሪው ህወሃት ወራሪ ውድመት የደረሰባቸውን የውሃና መብራት መሰረተ ልማቶችን በፍጥነት መልሶ ለመገንባት በጥናት ላይ የተመሰረተ ማስተካከያ ይደረጋል - ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ

“በአሸባሪው የህወሃት ወራሪ ኃይል ውድመት የደረሰባቸውን የውሃና መብራት መሰረተ ልማቶችን በፍጥነት መልሶ ለመገንባት በጥናት ላይ የተመሰረተ ማስተካከያ ይደረጋል” ሲሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ገለጹ።

ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የኢንዳስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋሞቻቸው ጋር በመተባበር በአሸባሪው በአሸባሪው የህወሃት ወራሪ ኃይል ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል ሰብዓዊ ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት ነው።

መስሪያ ቤቶቹ በድምሩ ከ4 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ሰብዓዊ ድጋፍ ለአፋር ክልል መንግስት አስረክበዋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ፥ አሸባሪው የህወሃት ወራሪ ኃይል በገባባቸው የአማራና አፋር ክልሎች መሰረተ ልማቶችን በማውደም እና ንጹኃን ዜጎችን በጥይት ደብድቦ ከመግደል ባሻገር እናቶችና ህፃናትን በማስራብ ዜጎች እንዲጎዱ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል።

ይህ አሸባሪ ቡድን በአፋር ክልል የፈጸመውን የወረራ ድርጊት የአፋር ህዝብ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ተቀናጅቶ መመከቱን አስታውሰዋል።

የተሸነፈው ሽብርተኛ ኃይል የንጹኃን ዜጎችን ተጠቃሚነት ለመጉዳት የውሃና የመብራት መሰረተ ልማቶችን በማውደም የጣለውን ጠባሳ ለመቀልበስ ተቋማቸው በጥናት ላይ የተመሰረተ ማስተካከያ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀደመ ቀዬአቸው ተመልሰው ኑሯቸውን እንዲጀምሩ ለማገዝ ከዚህ ቀደም ካደረገው የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ በተጨማሪ 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ብርሃኑ ሰርጃቦ፥ አሸባሪው ቡድን በአፋርና አማራ ክልሎች ሰብዓዊ ቀውስ ማድረሱን አስታውሰው፤ ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚልም የኢንዳስትሪ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በራሳቸው ተነሳሽነት ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት አልባሳት፣ የንጽህና መጠበቂያ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ድጋፉም ለአፋር ክልልና ኮምቦልቻ አካባቢ ለሚገኙ ወገኖች እንዲደርስ የታሰበ መሆኑን አመላክተዋል።

የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ሃጂ አወል አርባ፥ ተቋማቱ በሽብርተኛው ወራሪ ኃይል ተፈናቅለው ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እንዲውል በማሰብ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

አሸባሪው የህወሃት የጥፋት ቡድን የኢትዮጵያ እስትንፋስ የሆነችውን የሚሌ ኮሪደር በቀላሉ በመቆጣጠር ለድርድር እንቀርባለን ብለው ያጩት የአፋር ምድር መቃብራቸው እንዲሆን መደረጉን ተናግረዋል።

የሽብርተኛው ወራሪ ኃይል በአፋር ክልል ጦርነት በከፈተባቸው ሁሉም ግንባሮች ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት መደምሰሱንም አረጋግጠዋል።

#ENA
‹‹እድል ያልተሰጣቸው ሴቶች ወደ አመራርነት ሲመጡ ብቃታቸውን አሳይተዋል››
የተከበሩ ወ/ሮ ዛህራ ሁመድ, የኢ. ፌ. ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ

ሰመራ-የካቲት 30, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

‹‹እድል ያልተሰጣቸው ሴቶች ወደ አመራርነት ሲመጡ ብቃታቸውን አሳይተዋል››
የተከበሩ ወ/ሮ ዛህራ ሁመድ, የኢ. ፌ. ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ
በኢትዮጵያ ከለውጡ መንግሥት በኋላ ወደ አመራርነት የመጡ ሴቶች በብቃት እየሠሩ እንደሚገኙ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ ዛህራ ሁመድ ገለጹ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ ዛህራ ሁመድ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ እድል ሳይሰጣቸው የቆዩ ሴቶች ከለውጡ በኋላ ወደ አመራርነት ሲመጡ ብቃታቸውን አሳይተዋል።

ብዙ ሴቶች ዕድሉን ካገኙ በብቃት የመወጣት አቅም አላቸው ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤዋ፤ ይህንን አቅማቸውን ለመጠቀም በሁሉም የአመራርነት እርከኖች ላይ ለተሳትፎ ሳይሆን በብቃት ስኬታማ ተግባርን እንዲያከናውኑ ከዚህ በላይ ምቹ ሁኔታ መፈጠር እንዳለበት አመልክተዋል።

ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት ብቃት እና የትምህርት ዝግጅት ላይ ብቻ ትኩረት መደረግ እንዳለበትም ተናግረዋል።

የአመራርነት የልምድ ዘመንን በመቁጠር ሥልጣን መስጠት በተግባር ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ ሴቶች ወደ ፊት የሚመጡበትን ዕድል የሚዘጋ መሆኑንም አንስተዋል።

በተደጋጋሚ ሴቶችን ማስተማር እየተባለ ቢነገርም በአሁኑ ጊዜ የትምህርት ዝግጅትን በሚመለከት በስፋት በሴቶች ላይ ክፍተት የሚስተዋል አለመሆኑን ያስታወሱት ምክትል አፈጉባኤዋ፤ ከወንዶች እኩል በትምህርት ዝግጅት ሊፎካከሩ የሚችሉ ብዙ ሴቶች አሉ።

ሆኖም ግን ቀድሞ በመምራት በኩል ብዙ ሥራዎች ባለመሥራታቸው እና የአመራር ልምድ ዓመታት ሲቆጠር መስፈርቱን ስለማያሟሉ በመምራት ሂደት ውስጥ በተግባር ውጤት ሊያመጡ በሚችሉባቸው ደረጃዎች ላይ ዕድሉን የሚያገኙበት ሁኔታ ጠባብ መሆኑን ገልፀዋል።

‹‹የሴቶች እኩልነት ብዙም የእኛ ወንዶች ጆሮ ውስጥ ዘልቆ አልገባም።›› ያሉት ወይዘሮ ዛህራ፤ በተለይ አዳጊ ክልሎች አካባቢ እርሳቸው በተወለዱበት በአፋር ክልል ጎርፍ እና ድርቅ በተጨማሪ ለሁለት ዓመታት ተከታታይ ጦርነት እንደነበር አስታውሰው፤ በዚህ ችግር ውስጥ ጥንቃቄን የሚፈልጉ ትልልቅ ሥራዎች በሴቶች እየተሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሴት በትክክል በብቃት ሠርታ ውጤት ማምጣት እንደምትችል ታምኖ ዋና ዋና ሥራዎች እና ኃላፊነቶችን እንደትወጣ ተቆጥሮ ይሠጣታል። ሆኖም ግን ወደ ፊት በሚያመጡ የፖለቲካ ተሳትፎዎች ላይ የምትረሳ መሆኑን አስረድተዋል።

በዚህ ውስጥ በጥንቃቄ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ሕዝብን እያገለገሉ አቅማቸውን በማሳየት ላይ የሚገኙ ሴቶች ወደ ፊት አለመምጣታቸው እንደሚያበሳጭ እና አንዳንዴም በግልፅ ሊታዩ የማይችሉ ከፍታዎች እና ዝቅታዎች እንደሚያጋጥም ገልፀው፤ ይህ ሁሉ ቢሆንም ሴቶች በፅናት የሚሰጣቸውን ኃላፊነት አሁን ከሚታየውም በላይ ሠርቶ በማሳየት ምን ያህል ብቃት እንዳላቸው ሊያስመሰክሩ እንደሚገባም አብራርተዋል።

#ENA