Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ዝነኛው ፈንድቃ በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል ስራ መጀመሩን አስታወቀ

በካዛንቺስ ለበርካታ አመታት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ፈንድቃ ባህል ማዕከል በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል አገልግሎት መስጠቱን ዛሬ ሕዳር 29/2017 ዓም በተሰጠ መግለጫ አስታውቋል።

የባህል ማዕከሉ መስራች መላኩ በላይ እንደገለፀው ሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ፈንድቃን በሃያት ሪጀንሲ እንድንገነባ የፈቀዱ የሆቴሉን ስራ አስኪያጅ ከሪምን አመስግነው በካዛንቺስ ሲሰጥ የነበረው ሁሉም ፕሮግራም በሃያት ሪጀንሲ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ከሰኞ እስከ እሁድ ምሽት ፕሮግራሞች የሚኖሩ ሲሆን መግቢያ ዋጋ በካዛንቺስ እንደነበረው 200 ብር መሆኑ የተገለፀ ሲሆን መግቢያ በር በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በኩል እንደሆነም እውቁልኝ ብሏል።

ካዛንቺስ የነበረው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ቦታው እኛ እንድናለማ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ቦታውን ከእኛ ሰጥቶኛል ለዚህ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እናመሰግናለን ሲል መላኩ በላይ ምስጋና አቅርቧል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #fendika
ዛሬ የሙዚቃ ልደቷ ነው !
ታህሳስ 1/1970- ♾️

ስለ ሙዚቃ እና ሙዚቀኝነት ሲነሳ ተስጥኦ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል በእውነተኛ ሙዚቃ ውስጥ ሀሳብ ስሜት እውነት ፍቅር ይስተጋባል በሙዚቃ ሀገር ይገነባል ትውልድ ይቀረፃል ለትውልድ ደግሞ ታሪክ ይሰነድበታል እንዲህ ባለው ጠቃሚ ኢንዱስትሪ ላይ ከተከሰቱ እና በአጭር ጊዜ ብዙ እርምጃዎችን ከተራመዱ ሙዚቀኞች መሀል ኤልያስ መልካ ግንባር ቀደሙ ነው ። በዚህ ኢንዱስተሪ ላይ እንደ ኤልያስ መልካ ያለ ተስእጦን ከረቀቀ የሙያ ጥግ እና ከተሟላ ስብእና ጋር የተላበሰ ሙያተኛን ማግኘት መቻል ደግሞ እንደ ሙዚቃ አድማጭ በእጅጉ እድለኝነት ነው።

ኤልያስ መልካ የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ላይ ምን ማለት እንደነበር እሱን ከማጣት በላይ ማሳያ አለ ብዬ አላምንም(ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተሰማኝ ያለው ይህ ነው)

ጊታሪስት፣ኪቦርዲስት፣ቤዚስት፣ፒያኒስት፣ቼሎ ተጫዋች የሙዚቃ አቀናባሪ የዜማ እና ግጥም ደራሲ የላቀ ሀሳብ አመንጪ የባለሙያው መብት ተሟጋች ሙዚቃን በዲጂታል መንገድ የማገበያየት ሀሳብ ፈጣሪ (እንተርፕርነር) ወዘተ በመሆን ሀገሩን በትጋት በማገልገል በሙዚቃችን ላይ የማይተካ አይነተኛ ሚናን ተጫውቷል ።

ውድ ኤልያስ መልካ እንኳንም ተወለድክልን መልካም የ47ኛ አመት ሰማያዊ ልደት !!!💜💜💜

የኤልያስ መልካ አድናቂዎች ህብረት !!

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Elias_melka
"የደጋ ሰው"
የየማ የመጀመሪያ አልበም በፈረንሳይ 🇫🇷 ሀገር በሲዲ ታተመ

#Ethiopia | "የደጋ ሰው" የተሰኘው የየማ የመጀመሪያ አልበም በተለያዩ መተግበሪያዎች ከተለቀቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንሳይ ሀገር በሲዲ ታተመ።

“በዲጂታል ዘመን ሙዚቃዎቼ ታትመው በእጄ ሳገኛቸው ስሜቱ የተለየ ነው። “ ስትል በማህበራዊ ገፇ የማ አስፍራለች።

በቅርቡ በዩኤስቢ እና በሽክላ የሚታተም ይሆናል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #yema #eyuel_mengistu #yedegasew
"በቅርብ ጊዜ የሚወጣ አዲስ ሥራ ተጠናቋል" የክቡር ዶ/ር መሀሙድ አህመድ የሙዚቃ ስንብት አዘጋጆች

በቅርቡ በአሜሪካን ሀገር በተሰናዳው እና አንጋፋውን የሙዚቃ ሰው የክቡር ዶ/ር አርቲስት መሀሙድ አህመድን በዘከረው መረሀ ግብር ላይ ከ15 ሚሊዮን በላይ ብር መሰብሰቡን አዘጋጆቹ መግለፃቸው ይታወሳል።

በቆይታቸው ዝግጅቱ የተሳካ ከመሆኑ ባለፈ ከተጠበቀው በላይ ገቢ እንደተገኘበት አቶ ሸዊት ገልፀዋል።

ዝግጅቱን ለማከናወን ረዘም ያለ ጊዜን እንደጠየቀ የገለፁት አዘጋጆቹ ስንብት ከሚለው የመድረኩ ስያሜ አስቀድሞ "የክብር ምሽት" የሚል ስያሜ ለመስጠት ታስቦ እንደነበር ተናግረዋል።

ከዝግጅቱ ባለፈ የክቡር ዶ/ር አርቲስት መሀሙድ አህመድ አዳዲስ ሥራዎችን ያካተተ "ሲዲ" ለአድማጭ እንደሚደርስ አቶ ሸዊት ጠቁመዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #mehammud_ahmed
የሮፍናን የፍርድ ቤት ክስ ተዘጋ።

ድምፃዊ ሮፍናን ኑሪ አቶ ሃይለስላሴ አስረስ ተከሳሽ ሆነው የቀረቡበት የፍርድ ቤት ክርክር በስምምነት ተቋጨ።

ክሱ የተጀመረው ጥቅምት 15 ቀን 2016 አ.ም ባደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ስምምነት መሠረት ሊግባቡ ባለመቻላቸው ሲሆን ሮፍናን የአቶ ሃ/ስላሴ ቤትን በ165 ሚሊዮን ብር ለመግዛት እንደተስማማ የውል ስምምነታቸው የሚገልፅ ሲሆን ቅድመ ክፍያም ወደ 6 ሚሊዮን ብር ለ ሃ/ስላሴ ማስገባቱንም ገልጿል።

ሮፍናን በክሱ ላይም ሲያስረዳ ቅድሚያ ክፍያውን ካስገባሁ በኃላ ሻጭ የባንክ ብድር ውል አልጠብቅም በማለት የተስማማንበትን የቤት ውል ትተው ለሌላ ሰው በ170 ሚሊዮን ብር ሸጠውታል በሚል ሲሆን የወሰዱትንም ቅድምያ ክፍያ ሊመልሱልኝ ባለመቻላቸው ስለዚህም የወሰዱትን ገንዘብ ሊመልሱ ከሚገባቸው ቀን ጀምሮ በሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ሊከፍሉኝ ይገባል ሲል በመጀመሪያ ፍርድ ቤት በቦሌ ምድብ 2ተኛ ልዩ ልዩ የፍትሀብሄር ችሎት ተከሰው ነበር።

ይሁን እንጂ ተከሳሽና ከሳሽ ህዳር 22 ቀን 2017 አ.ም ለፍርድ ቤቱ የእርቅ ስምምነት በማቅረባቸው እርቃቸውም ፀድቆ መዝገቡ እንዲዘጋላቸው በጠየቁት ጥያቄ መሰረት ክሱ የተዘጋ ሲሆን ስምምነቱም ሮፍናን ቅድሚያ የከፈለው 6 ሚሊየን ብር እንዲሁም ተጨማሪ ያወጣው 100 ሺ ብር ባጠቃላይ ስድስት ሚሊየን አንድ መቶ ሺ ብር እንዲመለስለት በማድረግ ክሱ እንዲዘጋ ሆኗል።

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Rophnan
👉አርቲስት ሀመልማል አባተ የመካኒሳ ታዳጊዎች የእግር ኳስ ማሠልጠኛ ፕሮጀክት የክብር አምባሳደር ሆና ተመረጠች

"ትልቅ አደራና ኃላፊነት ነው የሠጣችሁኝ፤ከ37 ዓመታት በላይ የኖርኩበትን ሠፈር በተለይ በእግር ኳስ ሀገር የሚያስጠሩ ተጫዋቾችን ለማሳደግ እየደከመ ካለው ፕሮጀክት ጋር በሙሉ አቅሜ ለመስራት ቃል እገባለሁ" - አርቲስት ሀመልማል አባተ

"ትንሽ ከተማ ትልልቅ ህልሞች"የሚል መሪ ቃል ያነገበውና ከተመሠረተ ሶስተኛ አመቱን ያስቆጠረው የመካኒሳ ታዳጊዎች የእግር ኳስ ማሠልጠኛ ፕሮጀክት ተወዳጅዋንና ታዋቂዋን ድምፃዊ ሀመልማል አባተን የፕሮጀክቱ የክብር አምባሳደር አድርጎ መምረጡን ይፋ አድርጓል።

የመካኒሳ የታዳጊዎች የእግር ኳስ ማሠልጠኛ ፕሮጀክት በተወዳጅ ዘፈኖቿ በምታስተላልፋቸው መልዕክቶች፣በበጎ ስራዎቿና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያላትንና በአካባቢው በአርአያነት የምትጠቀሠውን ተወዳጅዋን አርቲስት ሀመልማል አባተን በሙሉ ድምፅ በመምረጥ ትናንት(ዓርብ)መካኒሳ አቦ ማዞሪያ በሚገኘው የፕሮጀክቱ ፅ/ቤት በተከናወነ ስነ-ስርዓት የክብር አምባሳደርነት ሠርተፊኬት እንደተሠጣት ታውቋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #hamelmal_abate
ቀላቲ ቢውቲ ድምጻዊ ቬሮኒካ አዳነን የብራንድ አምባሳደር ሆነች

#Ethiopia | ተወዳጅዋ ድምፃዊ ቬሮኒካ አዳነ ለቀላቲ ቢዉቲ ለቀጣይ ሁለት ዓመት የክብር አምባሳደር በመሆን ለቴሌቪዥን ፤ ለቢል ቦርድ እና ለማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያዎች ለመስራት የብራንድ አምባሳደር በመሆን ተፈራርማለች።

በ2008 ዓ.ም በአቶ ሮቤል ቀላቴ የተመሠረተው ዋና መቀመጫውም በአዲስ አበባ ያደረገው ቀላቲ ቢዉቲ የተለያዩ የውበት መጠበቂያ ምርቶችን በኦን ላይን በማዘዝ ለደንበኞች ባሉበት ስፍራ ለማድረስ የተመሠረተ ተቋም ነው።

ተወዳጅዋ ድምፃዊ ቬሮኒካ ቀላቲ ቢውቲ ጋር ለመስራት እድሉን በማግኘቷ የተሰማትን ክብር በፊርማ መርሐግብሩ ላይ ገልጻለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #veronica_adane
"ፍሬንች ሞንታና እና ልጅ ሚካኤል " በአንድ መድረክ አዲስ አበባ ላይ

ከሞሮኮ የዘር ሐረግ የተወለደው አለም አቀፍ ተወዳጅነት ያለው አፍሪካ አሜሪካዊው የሂፓፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ፍሬንች ሞንታና አገራችን ኢትዮጵያ መቶ ከኛው አመለ ሸጋው ልጃችን ልጅ ሚካኤል ጋ ስራቸውን ሊያቀርቡ እንደሆን የቅርብ ምንጮቻችን ነግረውናል::

ፍሬንች ሞንታና በሙዚቃዎቹ ውስጥ አፍሪካን በማስተዋወቅና ት/ቤቶችና ሆስፒታሎችን በማስገንባት ትልቅ አስተዋጾ እንደሚያደርግ ብዙ ስራዎቹ ላይ ይታያል በተለይ unforgettable የተባለው በዮጋንዳ ሀገር የተሰራ ሙዚቃው በዓለም በጣም ታዋቂና ዝነኛ ሙዚቃው ነው በእይታም ደረጃ ከአንድ ነጥብ ሰባት ቢሊየን በላይ ነው::

በነገራችን ላይ ልጅ ማይክም ከዓለም አቀፍ ሙዚቀኞች ጋ ሀገር ውስጥና ከሐገር ውጪ አንድ መድረክ ላይ በመስራት ብዙ ልምድ አለው:: ይህም የፍሬንች ሞንታናና የሱ የመድረክ ጥምረት አሪፍ ይሆናል ተብሎ ይገመታል::

ዝግጅቱም በሸራተንና በይሳቃል ኢንተርቴመንት አዘጋጅነት ይደረጋል ተብሏል::

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #frenchmontanna #lijmic
እንኳን ደስ ያላችሁ !!

#Ethiopia: እንኳን ደስ ያላችሁ - ድምፃዊት ቤቲ ጂ እና ወንድማችን ጋዜጠኛ ኤልያስ ወንድሙ!

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #bettyg