Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ከቀኑ 10 ሰአት በብሪቲሽ ካውንስል እንገናኝ!!!
Waliya Stage Ft. Leul sisay Was really a successful event

We had an incredible time at this month's event FEaturing the the talented singer Leul Sisay which is organized by Waliya Entertainment in collaboration with the British Council and Convex Technology. A huge thank you to the amazing Leul Sisay for joining us and making the night unforgettable! 🙌

The event featured spectacular live performances by talented singers, all backed by the fantastic Damat Band. A special highlight was the surprise performance by Almaz Sisay, the incredibly talented sister of our guest artist, Leul Sisay. His reaction was priceless! 🎤🎶

Thank you to everyone who came out and made this event so special. Stay tuned for more exciting events coming your way! 🌟

#WaliyaStage #LiveMusic #LeulSisay #AlmazSisay #DamatBand #BritishCouncil #ConvexTechnology #WaliyaEntertainment #MusicEvent #EthiopianMusic

@waliyaentmt
@waliyaentmt
"በጊዜ ሂደት የገባኝ ነገር ምንድነው ሰው ማፋቀር ፤ ማግባት ፤ መውለድ የተፈጥሮን ህግ መከተሉ ፤ ማህበራዊ ህይወት ከአጓጉል ድባቴ እና ego ነፃ ያወጣዋል። የሰው ልጅ እድሜው ከፍ እያለ ሲጫጫን ፤ ብቸኝነት ሲበዛ ፤ ቅርቡ ያሉትን ከራሱ ጋር ማነፃፀር ሲጀምር ሲያይ ከባድ የሆነ ግድ የለሽነት ውስጥ ይገባል። የሚኖርለት ሃሳብ ሲኖር ግን ካለበት ጉዳይ ጋር የሚያዛምደው ብቻውን ሳይሆን በሱ እቅፍ ስር ያሉትን ያገናዘበ ውሳኔዎቹን ያደርጋል። ሰው ለራሱ የሚሆነው እስከ ትንሽ ጊዜ ነው። ከዛ መሰላቸት ቸል ማለት ተስፋ ማጣት ይጠናወተናል ለሰው ለመኖር ነው የተፈጠርነው ። በ አቅራቢያችን የተረፉትን ስመለከት ተፈጥሮን የተከተሉ ናቸው። ተፈጥሮን መከተል ልክ ነው።" - እሱባለው ይታየው

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Esubalewu
8ኛው የኦዳ አዋርድ በፊንፊኔ ሸራተን ሆቴል ትናንት ተካሄደ።

የጉቱ አበራ 'Gaaffii Koo'' የተሰኘው አልበም የ2016 የአመቱ ምርጥ አልበም በመባል ተመርጧል።

አንዱአለም ጎሳ በምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ እና በምርጥ ነጠላ ዘርፍ “Bilillee” በተሰኘው ዘፈኑ ሁለት ሽልማቶችን አግኝቷል።

የ2016 የአመቱ ምርጥ የቡድንና ጥንድ ዘፈን አደም መሀመድ መሃመድ እና ጫልቱ ቡቶ “Gadaa Malee” በተሰኘው ዘፈን ተሸልመዋል።

በየአመቱ ተወዳጅ ዘፈን ዘርፍ ዮሳን ጌታሁን “ባላ ጊዜ” በተሰኘ ዘፈን አሸናፊ ሆኗል።

ምርጥ የሴት ዘፋኝ በመባል ለምለም ሃይለሚካኤል፣ ምርጥ አዲስ ዘፋኝ በመባል ደግሞ አሳንቲ አስቹ አሸናፊ ሆነዋል።

በምርጥ ዘመናዊ ዘፈን ደግሞ C Boy “አጀብ” በተሰኘ ዘፈን አሸንፏል።

ምርጥ ልበወለድ በመባል የጂኔኑስ ደጀኔ “Gungummii Eelaa” የሰኘ ልበወለድ አሸንፊ ሲሆን፤ በምርጥ የግጥም ስብስብ መፅሐፍ ደግሞ የገመቹ ተሊላ “Miilas Miilaanis” መፅሐፍ አሸናፊ ሆኗል።

አርቲስት እልፍነሽ ቀኖን ጨምሮ ሶስት አርቲስቶች የኤድሜ ልክ ሽልማት ተሸልመዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በኦዳ አዋርድ ለ8 የምስራቅ አፍሪካ አርቲስቶች ሽልማት ተበርክቷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #odaaward
ምስጋና ከ ልኡል ሲሳይ

"ልዑል የሙዚቃ አልበም ከወጣ ዛሬ አንድ ዓመቱን አስቆጥሯል ተመስገን 🙏🏾

በብዙ ፍቅር እና መዉደድ የምወዳችሁ የማከብራችሁ የሙዚቃዬ ወዳጆች አድናቂዎች ለድጋፋችሁ በጣም አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ያክብርልኝ!"

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Leulsisay
ለተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ 5 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል በፍርድ ቤት የተወሰነበት ድርጅት መክፈል እንደማይችል አሳወቀ።

ለረጅም ጊዜ የተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት የሚታወቀው ላየን ፕሮሞሽን የተሰኘው ድርጅትእና የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ጌታነህ አንዳርጌ ከቴዲ አፍሮ ጋር በነበራቸው የፍትሐብሔርክስ ክርክር ላይ ፍርድ ቤቱ ለድምፃዊው 5 ሚሊዮን ብር ሊከፈለው ይገባል ሲል ጥቅምት 6 ቀን 2016 አ.ም ወስኖባቸው ነበር።

በዚህ ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኙት አቶ ጌታነህ አንዳርጌ ይግባኝ ጠይቀን ለጥር 27 ቀጠሮ ተሰጥቶናል በተጨማሪም ድርጅቱ አሁን ላይ ምንም አይነት ስራ እየሰራ ባለመሆኑ ገንዘብ የለውም ስለዚህም ገንዘቡን መክፈል አይችልምሲሉ አስታውቀዋል።

ክሱ የተጀመረው ኢትዬጲያ ወደ ፍቅር ጉዞ የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት የካቲት 14 ቀን 20012 አ.ም በመስቀል አደባባይ የተደረገውን ኮንሰርት በማስመልከት በፅሁም ስምምነቱ መሰረት ለቴዲ አፍሮ 10 ሚሊዮን ብር እንደሚከፈለው የተገለፀ ቢሆንም ነገር ግን ገንዘቡ ሳይከፈለው መቅረቱን በማስመልከት ክስ ተመስርቶ ነው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #teddy_afro
ኢትዮጲያዊውያን የሙዚቃ ባለሙያዎች ከክሮሺያውኑ ሙዚቀኞች ያጣመረው አልበም ለሙዚቃ አፍቃሪያን ሊደርስ ነው

ዝነኛው የባህል ሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቹ እና በተለየ የማሲንቆ አጨዋወት ስልቱ የሚታወቀው ሀዲስ አለማየሁ (ሀዲንቆ) በሙሉ የበኩር አልበም ስራውን እንዳጠናቀቀ አስታወቀ፡፡

አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የአልበም ስራው እንደተጠናቀቀ ያስታወቀው ሙዚቀኛው ከኢትዮጲያውን በተጨማሪ የተለያየ ሀገር የሙዚቃ ባለሙያዎች ተሳትፎ እንዳደረጉበት አስታውቋል፡፡

የክሮሺያ ሁለት ባንዶችን ጨምሮ የዴንማርክ፤ የጃፓን፤ የአሜሪካ እና ጃማይካ የሙዚቃ ባለሙያዎች ተሳትፎ ማድረጋቸውን የተናገረው ሀዲስ አለማየሁ በአልበም ስራው ውስጥ የተለያየ ስልተ ምት ያላቸው ሙዚቃዎች እንደተካተቱበት በተጨማሪነት አንስቷል፡፡

በርካታ የሙዚቃ መሳሪያዎች ቢካተቱበትም የማሲንቆ ድምፅ ጎልቶ እንዲወጣ እንዲሰማ መደረጉን ያስታወቀ ሲሆን ክዚህ ቀደም በማሲንቆ ብቻ ከተሰሩ ስራዎች አንፃር ምስስሎሽ እንዳይኖረው ለማድረግ መሞከሩን ሙዚቀኛው አስታውቋል፡፡

ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ እና ክሮሺያዊው የሙዚቃ ባለሙያው በአልበም ስራው ውስጥ በፕሮዲውሰርነት እንደተሳተፉበት የተናገረ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለሙዚቃ ወዳጆች እንደሚቀርብ በተጨማሪነት ገልጿል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #masinqo #haddis_alemayehu