Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ኢትዮጲያዊውያን የሙዚቃ ባለሙያዎች ከክሮሺያውኑ ሙዚቀኞች ያጣመረው አልበም ለሙዚቃ አፍቃሪያን ሊደርስ ነው

ዝነኛው የባህል ሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቹ እና በተለየ የማሲንቆ አጨዋወት ስልቱ የሚታወቀው ሀዲስ አለማየሁ (ሀዲንቆ) በሙሉ የበኩር አልበም ስራውን እንዳጠናቀቀ አስታወቀ፡፡

አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የአልበም ስራው እንደተጠናቀቀ ያስታወቀው ሙዚቀኛው ከኢትዮጲያውን በተጨማሪ የተለያየ ሀገር የሙዚቃ ባለሙያዎች ተሳትፎ እንዳደረጉበት አስታውቋል፡፡

የክሮሺያ ሁለት ባንዶችን ጨምሮ የዴንማርክ፤ የጃፓን፤ የአሜሪካ እና ጃማይካ የሙዚቃ ባለሙያዎች ተሳትፎ ማድረጋቸውን የተናገረው ሀዲስ አለማየሁ በአልበም ስራው ውስጥ የተለያየ ስልተ ምት ያላቸው ሙዚቃዎች እንደተካተቱበት በተጨማሪነት አንስቷል፡፡

በርካታ የሙዚቃ መሳሪያዎች ቢካተቱበትም የማሲንቆ ድምፅ ጎልቶ እንዲወጣ እንዲሰማ መደረጉን ያስታወቀ ሲሆን ክዚህ ቀደም በማሲንቆ ብቻ ከተሰሩ ስራዎች አንፃር ምስስሎሽ እንዳይኖረው ለማድረግ መሞከሩን ሙዚቀኛው አስታውቋል፡፡

ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ እና ክሮሺያዊው የሙዚቃ ባለሙያው በአልበም ስራው ውስጥ በፕሮዲውሰርነት እንደተሳተፉበት የተናገረ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለሙዚቃ ወዳጆች እንደሚቀርብ በተጨማሪነት ገልጿል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #masinqo #haddis_alemayehu