Waliya Entertainment
289 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
March 19
ሳሚ ዳን እና ምላሽ የሚሰጥበት አነጋጋሪ ኮመንቶች

ድምፃዊ ሳሚ ዳን(ሳሙኤል ብርሀኑ) በራሱ የፌስ ቡክ ገፁ ሰዎች ኮመንት መስጫ ሐሳባቸውን ሲገልፁ እሱም ምላሽ እየሰጠ ቀናቶች አልፈዋል፡፡

አብዛኞቹ አርቲስቶች በራሳቸው ማህበራዊ ገፅ ፖስት ማድረግን እንጂ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ አይደሉም ከሰጡም ለሚያውቁት ወይም አንገብጋቢ መልስ ሲሆን ነው፡፡ ሳሚ ዳን ግን ለሁሉም መልስ ይሰጣል በማዝናናት ሆነ ቁም ነገር ለማስጨበጥ ነቃ እንዲል አስተያየቱን ሞቅ ባሉ አማርኛዎች ቅኔን የተደገፈ ያስቀምጣል፡፡

እንዲህ ማድረጉ ከበርካታ ሰዎች ጋር ቅርርብነትን ይፈጥራል፣አዲስ ነገር ለማወቅም እጅጉን ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ ድምፃዊው አልበም ማምረቱን ቀጥሎበታል መልኬ የተሰኘ ሙዚቃ በጥናት እና ቦታው ድረስ በመሄድ ከነፍሱ የሚሰራ ስራ ለመልቀቅም በዝግጅት ላይ ነው፡፡ ለመልኬ ግብሀት ይሆን ዘንድ አስተያየት ለሚፅፉለት ሰዎች ምላሽ በመስጠት ምን አይነት መልክ ይኖር ይሁን? ለአልበሙ የመልክ ግብዓት እየሰራ ያለ ይመስለኛል፡፡

አስተያየት መስጪያ ሳጥን ላይ መልሶ በመስጠት ዘለግ ላሉ ቀናቶች ቀጥሎበታል አዝናኝ መልሶች ፣ ትችትን አግባቡ ባለው መልኩ በጨዋታ መመለሱ ሊስተካከል የሚገቡ ነገሮችን እየነገረ የተከታዩን በሀሪ እያወቀ አዲስ ሌላ ተከታይ እያፈራበት ይገኛል፡፡

ብዙዎች በየዘርፉ ያሉ ታዋቂ ሰዎች የሚፈሩትን ደፍሮ እንዲህ ማድረጉ ለሌሎች ዝነኞች ምሳሌ ለመጪዎች ዝነኞች ደግሞ እንዲህ ብታደርጉ? እንዲህ ነው ምላሹ? የሚል አንድምታ ይሰጣል ስለዚህ ሊበረታታ ይገባል በግልፅ ነገሮችን ማቀበሉ በተጨማሪ ሊመሰገን ይገባል፡፡

እናንተስ እንዲህ ማድረጉ ምን ይሰማችኃል?

Follow us
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
March 22
ለሳምንታት በአንደኝነት ደረጃ ሲመራ የነበረው አሞራዉ ካሞራ የበለጠቺው ድምፃዊት..

1, ዝም - ማህሌት ወንድሙ
2, አሞራው ካሞራ - አስቻለው ፈጠነ
3, አማኑኤል የማነ - ንስኪላ
4, ያሬድ ነጉ - አለምድም
5, አንዷለም ጎሳ - ማሬ
6, ሶና ታከለ - ወራ ቡሌ
7, ይጣልሽ - ዬሃና እና ሳም ቮድ
8, ሜላት ቀለመወርቅ - ዜሮ
9, አንዷለም ጎሳ - ቢሊሌ
10, ቬሮኒካ አዳነ - ካንተ ሌላ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #top10music
March 22
አርቲስት ሜሮን ጌትነት፣ ለቀነኒ አዱኛ

ማነው ያለበሰሽ፣ ይህን ጥቁር ሸማ?
ለሞት ሙሽርነት፣ አድርጎ እንዲስማማ።
አስተያየትሽ ውስጥ፣ እልፍ መልዕክት አለ፣
ፈገግታሽን ገልጦ እውነት የከደነ፣
ለምን ሻማው በራ፣ አንቺ ጠፍተሽ ሳለ?
የዘወትር ጥያቄ፣ ባንቺ መስዋዕት ነፍስ፣
ብርሃንሽ ነው? ዕጣሽ? ለቀጣይ የሚደርስ?

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Andualemgossa
March 22
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተወዳጁ ድምፃዊ አብዱ ኪያር ከደረሰበት አደጋ አገግሞ አሁን በከዘራ ታግዞ መራመድ መጀመሩን እና በቅርቡም ያለምንም እርዳታ መራመድ እንደሚጀምር ገለጸ።

"አልሓምዱሊላህ በከዘራ ድጋፍ መራመድ ጀምሬያለሁ" በሚል በቪድዮ ያሰራጨው አብዱ፣ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ደግሞ የእናቱም ሃዘን ተደርቦበት እንደበር የሚታወቅ ሲሆን "ከአገር ውስጥ ፣ ከተለያዩ አገራት ፣ በአካል ፣ በስልክ ፣ በኢሜይልና በተለያየ መንገድ ያፅናናችሁኝ ያበረታችሁኝና የፀለያችሁልኝ ወንድምና እህቶቼ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። " ብሏል።

"አልሓምዱሊላህ ከሀዘኔ ተፅናንቻለሁ ከህመሜም አገግሜ አሁን አጥንቴ ገጥሞልኝ በከዘራ እየታገዝኩ በደንብ እየረገጥኩ እራመዳለሁ።" በሚል መልዕክት ያስተላለፈው አብዱ "በሚቀጥሉት ቀናት በደምብ ተለማምጄ በቅርብ ያለምንም እርዳታ መራመድ እጀምራለሁ። በድጋሚ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ።" በማለት መልዕክት አስተላልፏል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #abdukiar
March 24
ተወዳጇ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ከብዙ አመት በኋላ ስምንተኛ አልበሟን ልታወጣ ነው።

በብዙዎች ዘንድ የማይረሳ የሙዚቃ ቦታ ያላት አንጋፋዋ ድምፃዊ ከረጅም አመታት በኋላ ደጃዝማች የሚል የአልበም ርእስ በሰጠችው ስምንተኛ አልበሟ ተመልሳለች። አልበሙም በቅርቡ እንደሚወጣ ያሳወቀች ሲሆን በራሷ የዩቲዩብ ገፅም እንደሚለቀቅ ተናግራለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #kukusebsibe
March 24
March 25
March 26
March 26