Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#አስቴር_አወቀ # አይዞኝ

ደርሶ ድንገት ቢቸግረኝ
ውሃ ውሃ ቢጠማኝ
ሰውነቴ ቢደክምብኝ
የፈጠረኝ ጥሎ አይጥለኝም
አይዞኝ አይዞኝ አይዞኝ አይዞኝ (2x)
አይዞኝ
አይዞኝ አይዞኝ አይዞኝ አይዞኝ(2x)
አረ አይዞኝ
ስራ ጠፍቶ ቢቸግርህ
ጤና ጠፍቶ ብተኛ ታመህ
ቀን ጨልሞ ቢታይህ
የሚደርስልህ ዘመድ አለህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ አይዞህ (2x)
አይዞህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ አይዞህ(2x)
አረ አይዞህ
ዙርያው ገደል ሆኖ እህህ..
ቢጨልምብህ እህህ...
ሃገርና ወገን እህህ..
ዘመድም አለህ ህህ..
በጣምም ቢጨንቅ እህህ..
ብታጣም መድረሻም አሃሃ..
ሃገር ወገን አለህ..
የሚሆን መሸሻ አአ..
ይመጣል ይሄዳል ፍቅርና ሰው
ወስዶ ማይመልስያ ሞት ብቻ ነው
ሆዴ ረጋ ረጋ በል እረጋ ረጋ
አትወርድ ቆላ አትውጣ ደጋ
አረ ወዴት ወዴት ወዴት ወዴት ነው
አንድም መኖር ነው
አንድም መሞት ነው (2x)
አው...
በሰው ሃገር ቢከፋሽ
የሰው ክፉ ቢያሳዝንሽ
ሃገር ወገንሽ ቢናፍቅሽ
እስኪያልፍ ያለፋል እቴ አይክፋሽ
አይዞሽ አይዞሽ አይዞሽ አይዞሽ(2x)
አይዞሽ
አይዞሽ አይዞሽ አይዞሽ አይዞሽ(2x)
አረ አይዞሽ
ሃገር ነፃ ሲሆን እኛም ነፃነን
ሰላም እንደር ሰላም ያውለም
መልካም እንዲሆን ለሁላችን
እንፀልያለን በህሊናችን
አይዞን አይዞን አይዞን አይዞን(2x)
አይዞን አይዞን
አይዞን አይዞን አይዞን (2x)
አረ አይዞን
Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
# ጥላሁን_ገሰሰ # ሞናሊዛዬ_ነሽ

ቃላቶች ያጥሩኛል ምን ብዬ ላድንቅሽ
እንዲያው በደፈናው ሞናሊዛዬ ነሽ
ሞናሊዛዬ ነሽ
ቃላቶች ያጥሩኛል ምን ብዬ ላድንቅሽ
እንዲያው በደፈናው ሞናሊዛዬ ነሽ
ሞናሊዛዬ ነሽ
የአሁኒቷ እመቤት የፊቷ ተማሪ
እግዚአብሔርን አማኝ አካልሽን አክባሪ
ሆነሽ በማግኘቴ አድናቆት ይዞኝ
ላደንቅሽ ተነሳሁ ሰው እስኪሰማኝ
ቃላቶች ያጥሩኛል ምን ብዬ ላድንቅሽ
እንዲያው በደፈናው ሞናሊዛዬ ነሽ
ሞናሊዛዬ ነሽ
ቃላቶች ያጥሩኛል ምን ብዬ ላድንቅሽ
እንዲያው በደፈናው ሞናሊዛዬ ነሽ
ሞናሊዛዬ ነሽ
ጠቢባን ሊያደንቁሽ ቢፈልጉ ቃላት
ፍጽም አቃታቸው አልቻሉም ለማግኘት
በምን ላስመስልሽ ምን ብዬ ላድንቅሽ
የሸጋዎች ሸጋ ሞናሊዛዬ ነሽ
ቃላቶች ያጥሩኛል ምን ብዬ ላድንቅሽ
እንዲያው በደፈናው ሞናሊዛዬ ነሽ
ሞናሊዛዬ ነሽ
ቃላቶች ያጥሩኛል ምን ብዬ ላድንቅሽ
እንዲያው በደፈናው ሞናሊዛዬ ነሽ
ሞናሊዛዬ ነሽ
እንዳንቺ ውብ የለም በምድሪቱ ላይ
ብዬ ባዳንቅሽ ይበቃሻል ወይ
ሲሰራሽ የዋለ ሲሰራሽ ያደረ
የኔ በመሆንሽ ክብሬ ተከበረ
ቃላቶች ያጥሩኛል ምን ብዬ ላድንቅሽ
እንዲያው በደፈናው ሞናሊዛዬ ነሽ
ሞናሊዛዬ ነሽ
ቃላቶች ያጥሩኛል ምን ብዬ ላድንቅሽ
እንዲያው በደፈናው ሞናሊዛዬ ነሽ
ሞናሊዛዬ ነሽ
ሞ ና ሊ ዛ ዬ እህ ነሽ
Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
# ህብስት_ጥሩነህ # ተጣልተናል_ወይ
ኖረን ኖረን ኖረን ስንዋደድ
አብረን ስንቆይ ስንቆይ ስንላመድ
ወድሻለሁ ማለት ምን ይከብዳል ቃሉ
አልደፈር ያለው b’adam ዘር በሙሉ ሆኖ አመሉ
እንደመጀመሪያው ምነው ዛሬ
አወድሻለሁ ማለት ቀረ ፍቅረ
ተጣልተናል ወይ ተጣልተናል
ተጣልተናል ወይስ ተጣልተናል
ሆኘይልህ የቃል በረኛ
ናፍቀይ አቂፈይው ልተኛ
ስጠብቅ የልብህን ካፍህ
ዘጋሄኝ አጥነግረግንም ሳይህ
ትተሃል ትተሃል ere’titehal
ማቆለማመቱን አረስተሃል
ብሎ አንደው ብሎ አይል wogileh?
ደስ ይላል ስትነግረኝ ሲሰማህ
ተጣልተናል ወይ ተጣልተናል (wey)
ተጣልተናል ወይ ተጣልተናል (wey)
ተጣልተናል ወይ ተጣልተናል (wey)
ተጣልተናል ወይ ተጣልተናል (wey)
[Bridge 2x]
አፏቹ አረቂቅ ምስጢር
ዝምታው ቃልም ነዑው ፍክር
አንደነ የምአምርልኝ ቀነ
መዉደደ ስትለኝ ነዑው አነ
ማፍቀረይ ብትለኝ አንዴ ጥንቱ
Min’ale ቢሰማኝ ልጅነቱ
ያንን በማር ለዉስ ቃልህን
ወዴት አደረሰቀው ፍቅረይህን
ተጣልተናል ወይ ተጣልተናል ወይ
ተጣልተናል ወይ ተጣልተናል ወይ
ተጣልተናል ወይ ተጣልተናል ወይ
ተጣልተናል ወይ ተጣልተናል ወይ
ወድሻለሁ በል የዉጣ ቃሉ
አነይ አወድሃለሁ ይብቃ አመሉ
ወድሻለሁ በል የዉጣ ቃሉ
አነይ አወድሃለሁ ይብቃ አመሉ
ተጣልተናል ወይ ተጣልተናል ወይ
ተጣልተናል ወይ ተጣልተናል ወይ
ተጣልተናል ወይ ተጣልተናል ወይ
ተጣልተናል ወይ ተጣልተናል ወይ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
# ኤፍሬም_ታምሩ#

አማን_ነሽ_ዎይ
ፍቅሬ ያለሽበት አገር አማን ነው ዎይ
አገር አማን ነው ዎይ
አንቺስ ሰላም ነሽ ዎይ ሰሞኑን አማን ነሽ ዎይ
አገር አማን ነው ዎይ
ይጨንቀኛል ዝም ብሎ
ይጨንቀኛል
አልቻልኩም እኔ
እስካይሽ ባይኔ
ፍቅሬ ያለሽበት አገር አማን ነው ዎይ
አገር አማን ነው ዎይ
አንቺስ ሰላም ነሽ ዎይ ሰሞኑን አማን ነሽ ዎይ
አገር አማን ነው ዎይ
ይጨንቀኛል ዝም ብሎ
ይጨንቀኛል
አልቻልኩም እኔ
እስካይሽ ባይኔ
ትዝታዬን ሁሉ ብስለው ስፅፈው
አልቻልኩም ጭንቀቴን መናፈቄን አልተው
እንቅልፍም አላሻኝ ተኛም አላለኝ
እንዳላርፍ አይደል ዎይ ከሀሳብ የጣለኝ
አልጋዬን አንጥፌ እንዴት ልደርበት
አንሶላው ትራሱ ያንቺ ሀሳብ አለበት
ጎኔን ከመኝታ ከኩታው ባገናኝ
ገላዬ ብደርብ ውስጤ መች አስተኛኝ
መች እችላለሁ እኔ ልደብቀው ጉዳቴን
ጭንቅ እያለኝ እኔ እኖራለው ምኞቴን
ሰነበተ መንፈሴ ናፍቆት ሲመትነው
ወገን ዘመድ ጎረቤት ሀገሩስ እንዴት ነው
ሰነበተ መንፈሴ ናፍቆት ሲመትነው
ወገን ዘመድ ጎረቤት ሀገሩስ እንዴት ነው
እቴ ያለሽበት አገር አማን ነው ዎይ
አገር አማን ነው ዎይ
አንቺስ ናፍቀሻል ዎይ ሰሞኑን አማን ነሽ ዎይ
አገር አማን ነው ዎይ
ይጨንቀኛል ዝም ብሎ
ይጨንቀኛል
አልቻልኩም እኔ
እስካይሽ ባይኔ
ፍቅሬ ያለሽበት አገር አማን ነው ዎይ
አገር አማን ነው ዎይ
አንቺስ ሰላም ነሽ ዎይ ሰሞኑን አማን ነሽ ዎይ
አገር አማን ነው ዎይ
ይጨንቀኛል ዝም ብሎ
ይጨንቀኛል
አልቻልኩም እኔ
እስካይሽ ባይኔ
የሚያየው ነገር ላይ እየሳለሽ አይኔ
ልረሳሽ አልቻልኩም ተጎዳሁኝ እኔ
እድሌ ሆነና መናፈቅ አይለቀኝ
መሬቱ እንደሰማይ ይውላል ሲርቀኝ
ወዳንቺ ያለውን ወደኔ ስስበው
እንደው ምንም የለ ዞሬ ማላስበው
ማን ያምጣልኝ ወሬ አንቺን ተመልክቶ
ፀጋ ሰውነቴ አማን ነሽ ወይ ከቶ
መች እችላለሁ እኔ ልደብቀው ጉዳቴን
ጭንቅ እያለኝ እኔ እኖራለው ምኞቴን
ሰነበተ መንፈሴ ናፍቆት ሲመትነው
ወገን ዘመድ ጎረቤት ሀገሩስ እንዴት ነው
ሰነበተ መንፈሴ ናፍቆት ሲመትነው
ወገን ዘመድ ጎረቤት ሀገሩስ እንዴት ነው

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#አበባ_ደሳለኝ#

ህይወት_እንደ_ሸክላ
እድሜው መገስገሱን ከንቱ ሰው ዘንግቶ
ነገ አልፎልኝ ይላል ማለፉን ረስቶ/2x/
አይቀር መንፈራገጥ ያ ሆድ እስኪሞላ
ወድቃ እስክትሰበር ህይወት እንደ ሸክላ/2x/
አይቀር መንፈራገጥ ያ ሆድ እስኪሞላ
ወድቃ እስክትሰበር ህይወት እንደ ሸክላ/2x/
ጣራ እና ግድግዳው በወርቅ በሰራ
ገንዘብ ተቆልሎ ቢመስል ተራራ
በከፋው ጨለማ በዛ በሞት መንገድ
ተከትሎ አይሄድም ሃብት የስጋ ዘመድ /2x/
በከፋው ጨለማ በዛ በሞት መንገድ
ተከትሎ አይሄድም ሃብት የስጋ ዘመድ /2x/
ያለው ከሌለው ጋር ተካፍሎ እንደመብላት
ለምን ይሰስታል እድሜ አይለውጥም ሃብት/2x/
የለለው ዘመዱን ሸኝቶት በጥርሱ
ችግር ይዞት ሲሞት ምንድነው ማልቀሱ
ያለው ከሌለው ጋር ተካፍሎ እንደመብላት
ለምን ይሰስታል እድሜ አይለውጥም ሃብት/2x/
ያለው ከሌለው ጋር ተካፍሎ እንደመብላት
ለምን ይሰስታል እድሜ አይለውጥም ሃብት/2x/

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#አስቴር_አወቀ #
እኔም_ሀገር_አለኝ
ሁሉም ሀገር ሀገር ሀገር ይላል
ይህ ሀገረ ብርቁ /2x
የሀገር ፍቅር ስሜት ልቤን አቃጠለው
መጥቼ የማያት ሀገሬን መቼ ነው
ሰላም ላንቺ ይሁን ለውዲቷ እናቴ
ካለሁበት ቦታ ከልብ ከናፍቆቴ
ካለሁበት ቦታ ከልብ ከናፍቆቴ
አመት በዓል ደረሠ ይገዛ አዲስ ልብስ
በጉ ዶሮ ይቅረብ ዳቦም ይቆረስ
ጨዋታው ሲደራ ዘመድ ሲደሰት
ትዝ ይለኝ ጀመረ እርቄ ስሄድ
ሀገሬ ኢትዮጵያ ለምለሟ አበባዬ
ሳስብሽ ይፈሳል እምባዬ በላዬ
ብደሰት ብጫወት ሳይነካ ክብሬ
ባምር ብንቆጠቆጥ እኔስ በሀገሬ
የወንዜ ፏፏቴ አቀማመጥሽ
ለምለሟ ሀገሬ እምዬ ድምቀትሽ
ሁሉም ሀገር ሀገር ሀገር ይላል
ይህ ሀገረ ብርቁ
እኔም ሀገር ሀገር ሀገር አለኝ
የሚታይ በሩቁ
ሁሉም ሀገር ሀገር ሀገር ይላል
ይህ ሀገረ ብርቁ /2x
Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ማዲንጎ_አፈወርቅ #
አባይ_ወይስ_ቬጋስ

ፍጥረትህ ዥንጉርጉር ውሀና በረሀ
ሁሉም በያለበት የውበት አማህ
አንዱ በተፈጥሮ አንዱ በሰው ጥበብ
አይን የማያስነቅል ታይቶ ማይጠገብ
ወይ ስጋ ሳይሉ መፍረድ ነው እንደ ራስ
እውነት የሰው ሀገር አባይ ወይስ ቬጋስ
ደመና ከጸሀይ ለምለምና ደማቅ
ትንግርት ህብረ ቀለም ያ'ባይ ሰምና ወርቅ
በነዲድ በረሀ ትንፋሽ በሚያሳጣ
የህንጻ ጫካ አይቶ ቬጋስ ተንቆጥቁጣ
ህይወት የትም አለ በህንጻና በዳስ
ግን የሰው መኖርያው አባይ ወይስ ቬጋስ
ፍጥረትህ ዥንጉርጉር ውሀና በረሀ
ሁሉም በያለበት የውበት አማህ
አንዱ በተፈጥሮ አንዱ በሰው ጥበብ
አይን የማያስነቅል ታይቶ ማይጠገብ
ወይ ስጋ ሳይሉ መፍረድ ነው እንደ ራስ
እውነት የሰው ሀገር አባይ ወይስ ቬጋስ
ፈጣሪን አስቦ እንደ እምነት ማህደር
አባይ ይጨርሳል ፍቅርን በሚስጥር
ምጡቅና ስልጡን ቬጋስ ሴቱ ወንዱ
ሀጥያቱም ግልጽ ነው ላ'ብዬ መንገዱ
ምን ግዜ አለው ቬጋስ የምራቅ መዋጫ
ሁል ግዜ ባተሌ ሰው ከሰው እሩጫ
እንደ ራስ ነው መፍረድ ለነፍስም ለስጋ
አባይ ወይስ ቬጋስ ለሰው ልጆች ፀጋ
የሰው ማድሀኒቱ የሰው ልጅ ነውና
አባይ ወይስ ቬጋስ ላ'ዳም ዘር ፈተና

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ጃኖ_ባንድ#
ይነጋል
አይገርምም መሽቶ ላይቀር
ፀሐይ ብትጠልቅም አይገርምም
አይደንቅም ደስታ ሊቸር
ጊዜ ቢያስጨንቅም አይገርምም
የዚች አለም ህይወት ፈተና
በዝቶ በኔ ምን ቢፀና
አስተምሮኝ ላይቀር ማለፉ
ለምን ላስብ ክፉ
ቢመሽም ቀኑ ቢጨልም
ለብርሃን እጅ አልሰጥ ቢልም
ቻል ሆድህን አስፋ
ተው አትቁረጥ ተስፋ
ብታጣም ቢፈተን ስጋህ
እናደ እሾህ ሳሩ ቢወጋህ
ቻል ሆድህን አስፋ
ተው አትቁረጥ ተስፋ
ወትሮም ሰው ባለም ፈተና
የታጨው ለድል ነውና
ጊዜ ብዙ ያረጋል
ቻል አርገው ይነጋል
ዳገቱን ላስብ ጀምሬው
አትበል ጣፋጭ ነው ፍሬው
ቻይ ሆድህን አስፋ
ተው አትቁረጥ ተስፋ
ለነፍስም ለስጋ ቅሪት
አንተው ነህ የአንተው መዳኒት
ቻይ ሆድህን አስፋ
ተው አትቁረጥ ተስፋ
መሸበር መፍራቱን ትተህ
ፅልመቱን እለፍ በርትተህ
ጊዜ ብዙ ያረጋል
ቻል አርገው ይነጋል

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ጎሳዬ_ተስፋዬ#
ሰላም_ይስጠን
ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለው እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል በአይኔ]2X
እንዲያው አንዳንዴ ይገርማል
ኧረ እንደው አንዳንዴስ ይደንቃል
እንዴት ተንዶ ፍቅራችን
ማነው ያራራቀን የእውነት ቃል
በጊዜ አስታከን በዘመን
እራስ መውደድን አስቀድመን
ይቅርታ ራቀ ካፋችን
ስናይ እየተቀማ ልባችን
አንቃን ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
አንቃን ቅድስቷን ምድር ሰላም አውርሳት ደስታ
አንቃን ከቁጣ አብርደህ ቅን ወዳጅ አርገህ አንቃን
አንቃን የት ይደረሳል ምን ይወረሳል ይብቃን
አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ
ማረን እግዚኦ ማረን ከክፋ አድነን
አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን ከክፋ አድነን
አፋ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን ከዚ ፈተና
አፋ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን እግዚኦ ማርና
ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለው እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል በአይኔ]2X
በሀሜት በወሬ ታጅበን
በግላዊ ምቾት ተከበን
በዚች ጊዜአዊ ከንቱ ዓለም
ዘላለም ቋሚ ግን አንድ የለም
ንብረት ከሰው ልጅ አብልጠን
ክፋት ምቀኝነትን መርጠን
ዘመን አለፈ ስንኖር
የፅድቁን መንገድ የሚያሳይ አጥተን
አንቃን ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
አንቃን ቅድስቷን ምድር ሰላም አውርሳት ደስታ
አንቃን ከቁጣ አብርደህ ቅን ወዳጅ አርገህ አንቃን
አንቃን የት ይደረሳል ምን ይወረሳል ይብቃን
አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ
እግዚኦ ማረን ማረን ከክፋ አድነን
አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን ከክፋ አድነን
አፋ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን ከዚ ፈተና
አፋ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን እግዚኦ ማርና

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ጥላሁን_ገሠሠ #ፍቅር_ከኛ_እንዳይለየን
ፍቅር ከኛ እንዳይለየን
እንዲቃናልን ስራችን
መጨቃጨቅ ይወገድና
ሰላም ይሁን ለሁላችን /2X
ኑሮ ለሰው ልጆች
በእውነት ቀላል ስላልሆነች ዋዛ
በሆነው ባልሆነው ይቅር
ጭቅጭቃችን አይብዛ
ንዝንዝ ንትርክ ካለ
በኑሮአችን መሀከል
ወዳቻችንም ይቀራል
ሀብትም ቢሆን ይርቃል
ገንዘብ ፍቅር ከሌለው
የማይጠቅም ከንቱ ነው
ለጊዜው ያስደስት እንጂ
ሲረግፍ እንደ ጤዛ ነው
በየተሰማራበት መልኩ
የሰው ልጅ እንደሙያው
ነጋዴውም ወደ ንግዱ
ገበሬውም ወደ እርሻው
ተሰማርቶ ውሎ
ተደስቶ የሚኖረው
ከመተዛዘብ በስተቀር
መጨቃጨቅ ላይኖረው
ሰላም እና መተዛዘን
ከጠፉ ግን ከኛ ዘንድ
ህይወትም መሪር ይሆናል
ኑሮም እኮ አይወደድ
ፍቅር ከኛ እንዳይለየን
እንዲቃናልን ስራችን
መጨቃጨቅ ይወገድና
ሰላም ይሁን ለሁላችን /2X

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#አስቴር_አወቀ #ወይኔ_ጉዴ_ፈላ
ልቤን እንደበላ ልብህን ሳልበላ
ስታንሰፈስፈኝ አንጀቴን ስትበላ
ዘንድሮስ ተሸነፍኩ ወይኔ ጉዴ ፈላ (2x)
እኔስ ጉዴ ፈላ ወይኔ ጉዴ ፈላ (4x)
ስትልብኝማ ዝንጥንጥ ቅብጥብጥ
ሆዴን እክክ አድርገክ ምራቄን ስታስውጥ
አመለጠኝ ብዬ ስፈራ ስፈራ
ጭንቀቴ አይወራ ውሉ አይወራ
ውይ ውዩ ውዩ ውሉ አይወራ(4x)
አካልክ በሙሉ ፍቅርን ያነገቡ
አድፍጠው ከቃሉ በሰዎች ሲገቡ
ስነሳ ተነሳው ስተኛ እተኛለሁ
በሱስክ ተጠምደው አንተን ያዛጋሉ
ዎዬ ኦ ዎዬ ኦ
በፍቅርክ ሞቅታ አካሌን ስትረታ
መንፈሴን ሰብስበክ ስታለብስ እርካታ
ከስንቶቹ ወንዶች ከብዙ ጋጋታ
በፍቅር ጨዋታ ነህ እኮ አንድ ጌታ
አንድ ጌታ(4X)
ልቤን እንደበላ ልብህን ሳልበላ
ስታንሰፈስፈኝ አንጀቴን ስትበላ
ዘንድሮስ ተሸነፍኩ ወይኔ ጉዴ ፈላ (2x)
እኔስ ጉዴ ፈላ ወይኔ ጉዴ ፈላ(4X)
አንተ የወንድ አውራ የፍቅር ሳተና
ሲፈጥርክ የተቻርክ መለሎ ቁመና
የአካሉ ንጉስ የጀግኖቹ ጀግና ተው አታንገላታኝ ቶሎ ና ቶሎ ና
ዎዬ ኦ ዎዬ ኦ
ስትልብኝማ ዝንጥንጥ ቅብጥብጥ
ሆዴን እክክ አድርገክ ምራቄን ስታስውጥ
አመለጠኝ ብዬ ስፈራ ስፈራ
ጭንቀቴ አይወራ ውሉ አይወራ
ውይ ውዩ ውዩ ውሉ አይወራ(4x)
ልቤን እንደበላ ልብህን ሳልበላ
ስታንሰፈስፈኝ አንጀቴን ስትበላ
ዘንድሮስ ተሸነፍኩ ወይኔ ጉዴ ፈላ (2x)
እኔስ ጉዴ ፈላ ወይኔ ጉዴ ፈላ (4x)

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ህብስት_ጥሩነህ #ወግ_ነው
ውረጅ አለኝ ደጅህ እንደገና
ቁርጤን ሳላውቅ ውሎዬም አይቀና
አልጠቀመኝ አሻግሮ ማየቴ
ዛሬስ ልድፈር ይውጣ ካንደበቴ
ወጥቼ እመጣለሁ
ይሉኝታን አልፈራ
ያረፈደ ፍቅሬን አዬ
ተቀበል አደራ (2x)
ዘገየሁ መሠለኝ እኔ
ካንተው ይምጣ ብዬ (2X)
ከጄው ላይ ዘገኑህ አቤት
ይፍረደኝ አንድዬ (2)
በልቤ ሳጭህ ውዬ
ልጠየቅ ወግ ነው ብዬ
ሳልዘጋጅ ማለዳ
ተዘረፍኩኝ ከጓዳ
ወዲህ ነህ ብየ ስመካ
አርፍጄ ልብ አታይም ለካ
ፍቅርህን ይዤ በአንጀቴ
አስቀደመኝ አንደበቴ
ሠማንያም የለንም ዶሴም የለኝ ከጄ
በምን ልሟገተው ወዴት ዳኛ ሔጄ
ተጠያቂ የለበትውል የለው ከልቤ
ለፍርድ የማይመች ያጨሁት ባሳቤ
ደረሰልኝ ብዬ ስጠብቅ ቀኔን
ጃኖዬን ለበሱት ቀረሁ እርቃኔን
ይበለኝ ያጠፋሁ ራሴ
ጠላቴ የገዛ ምላሴ
አጥቼው አቤት ከምልበት
ምናለ ጥንቱን ብደፍርበት
ይበለኝ ያጠፋሁ ራሴ
ጠላቴ የገዛ ምላሴ
አጥቼው አቤት ከምልበት
ምናለ ጥንቱን ብደፍርበት
ይበለኝ…ይበለኝ…ይበለኝ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ቴዲ_አፍሮ #ኡኡታዬ
ዘመን ያገነነው ጅብ ቆሟል ከበሬ
አፌ እዳታስበላኝ ባለመናገሬ
እያየ ስትወጣ ልትጫወት በሳት
ምን ያረጋል አፌ ካለፈ ብትወቅሳት
አልፎ በዝምታ በስተመጨረሻ
ቢጮህ ምን ያረጋል ጅብ ከሄደ ውሻ
ተናገራት አፌ ሳይመጣ ደመና
ጅቡ ከበራፌ ላይ ነውና
ኡኡ በል እንጂ አፌ ውጣ ከተራራ
ድምፅ ሳይገጫጭ አንዱ ከአንዱ ጋራ
ኡኡ ሳትል አፌ ዛሬ በሰዓቱ
ጅብ ከሄደ ውሻ ይሆናል ጩኸቱ
ኡኡታዬ ላይሰማ ያኔ
እሪ ብል አሁን እስክነቃ ልሳኔ
እሪታዬ ቃል ላይሰማ
ኡሳልል ኡባልል ኡሳልል ያኔ
አፌ አፌ ሰሚ ለሌለው ያኔማ
ዘመን ያገነነው ጅብ ቆሟል ከበሬ
አፌ እዳታስበላኝ ባለመናገሬ
እያየ ስትወጣ ልትጫወት በሳት
ምን ያረጋ አፌ ካለፈ ብትወቅሳት
አልፎ በዝምታ በስተመጨረሻ
ቢጮህ ምን ያረጋል ጅብ ከሄደ ውሻ
ተናገራት አፌ ሳይመጣ ደመና
ጅቡ ከበራፌ ላይ ነውና
ኡኡታዬ ላይሰማ ያኔ
እሪ ብል አሁን እስክነቃ ልሳኔ
እሪታዬ ቃል ላይሰማ
ኡሳልል ኡባልል ኡሳልል ያኔ
አፌ አፌ ሰሚ ለሌለው ያኔማ
ቀለበትሽ ከ'ኔ ልብሽ ከሌላ ሰው
ይሄ አለመታመን ቤትን ከፈረሰው
ለሶስቱ ጉልቻ ገባው ስል ከቤቴ
ነፍሴ እዳትጠራ በቀለበት ጣቴ
አፌ በዝምታ ብታልፋት በንቀት
ከነባለቤት ነው የጥሪ ወረቀት
ተናገራት አፌ ሳይመጣ ደመና
ጅቡ ከበራፌ ላይ ነውና
ኡኡታዬ ላይሰማ ያኔ
እሪ ብል አሁን እስክነቃ ልሳኔ
እሪታዬ ቃል ላይሰማ
ኡሳልል ኡባልል ኡሳልል
ያኔ አፌ አፌ ሰሚ ለሌለው ያኔማ
ኡኡታ ተይ መኝታ ከ'ኔ ሌላ....

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics