Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ጎሳዬ_ተስፋዬ# ሰርክ_አዲስ

ባይሽ ሳይሽ ብዉል መች ጠግባለሁ
እርሜን ባላገኝሽ ጭንቄ ለጉድ ነዉ።
ባይሽ ሳይሽ ብዉል መች ጠግባለሁ
እርሜን ባላገኝሽ ጭንቄ ለጉድ ነዉ።
ሰርክ አዲስ እርቅ ነሽ ለኔ
ስያይሽ ያስዉባል አለምን አይን።
እንዳንቺ ማን ተፈጠረ
ያየሽ ሰዉ ሁሉ ተደንቆ ቀረ።
ልቤ…………ሄይ ሄይ ሄይ
ያልደረሰበት ድንቅ ጣእም አለዉ
ያዉብ አንደበት
ባይኔ…………ሄይ ሄይ ሄይ
ምስልሽ ተስሏል ካንቺ ወድያዎ
አላዉቅም ብሏል
እስካዬዉ ጓጓዉ
እስካዬዉ ደርሶ
የኔ ያንቺ ነገር ስንቴ ጣእም ይዞ።
እስካዬዉ ጓጓዉ
እስካዬዉ ደርሶ
የኔ ያንቺ ነገር ስንቴ ጣእም ይዞ።
ሲን ያዳ ጂሩንኮ ሱማ ወሊን ባረዳ
ኢጂኮ ዮሲአርጉ ጋማዳ
ሲምቦኮ ጃላሊኬን ሃዋ sin yaadaa
ሲን ያዳ ጂሩንኮ ሱማ ወሊን ባረዳ
ኢጂኮ ዮሲአርጉ ጋማዳ
ሲምቦኮ ጃላሊኬን ሃዋዳ
ጋሩኒቁ ሂንሲቁ ሲራ
ሲንጃላዻ ኩኖዳዳባሌ
ጋሩኒቁ ሂንሲቁ ሲራይ
ሃሳ ናማን ፈዹ ካንኬ ማሌ
ጋሩኒቁ ሂንሲቁ ሲራ
ሲንጃላዻ ኩኖዳዳባሌ
ጋሩኒቁ ሂንሲቁ ሲራይ
ዱቢ ናማን ፈዹ ካንኬ ማሌ
ባይሽ ሳይሽ ብዉል መች ጠግባለሁ
እርሜን ባላገኝሽ ጭንቄ ለጉድ ነዉ።
ሰርክ አዲስ እርቅ ነሽ ለነ
ስያይሽ ያስዉባል አለምን አይን።
እንዳንቺ ማን ተፈጠረ
ያየሽ ሰዉ ሁሉ ተደንቆ ቀረ።
ዉዴ…………ሄይ ሄይ ሄይ
የፍቅር ፍሬ የሌት ጠላቴ ነሽ አዲስ ነገረ
ዉቤ………… ሄይ ሄይ ሄይ
ድንቄ ጣሜኔሽ ልኑር ስወድ ሺደጋግሜ
እስካዬዉ ጓጓዉ
እስካዬዉ ደርሶ
የኔ ያንቺ ነገር ስንቴ ጣእም ይዞ።
እስካዬዉ ጓጓዉ
እስካዬዉ ደርሶ
የኔ ያንቺ ነገር ስንቴ ጣእም ይዞ።
ሲን ያዳ ጂሩንኮ ሱማ ወሊን ባረዳ
ኢጂኮ ዮሲአርጉ ጋማዳ
ሲምቦኮ ጃላሊኬን ሃዋ sin yaadaa
ሲን ያዳ ጂሩንኮ ሱማ ወሊን ባረዳ
ኢጂኮ ዮሲአርጉ ጋማዳ
ሲምቦኮ ጃላሊኬን ሃዋዳ
ጋሩኒቁ ሂንሲቁ ሲራ
ሲንጃላዻ ኩኖዳዳባሌ
ጋሩኒቁ ሂንሲቁ ሲራይ
ዻራ ናማን ቃቡ ካንኬ ማሌ
ጋሩኒቁ ሂንሲቁ ሲራ
ሲንጃላዻ ኩኖዳዳባሌ
ጋሩኒቁ ሂንሲቁ ሲራይ
ያዶ ናማን ቃቡ ካንኬ ማሌ
ካንኬ ማሌ
ካንኬ ማሌ
ካንኬ ማሌ
ካንኬ ማሌ
ካንኬ ማሌ
ካንኬ ማሌ
ካንኬ ማሌ
ካንኬ ማሌ
ካንኬ ማሌ
ካንኬ ማሌ
ካንኬ ማሌ
ካንኬ ማሌ
ካንኬ ማሌ
Shear to your beloved one
@ethiopian_music_lyrics
#ቴዎድሮስ_ታደሰ# ፍቅር_ፍርጃውን

አመጣው ፍቅር ፍርጃውን
እንጃልኝ መሰንበቻውን /2x/
ቀልዱን ተይ የቀን ቅዥቱን
አብርጅውየ ነገር እሳቱን
ያምጣልን እስኪ ምህረቱን
እኔን ሲኦል ጥለሽ
ጓዝሽን ጠቅልለሽ
ገነት ገባሁ ያልሽው
ከኔ ተለይተሽ ስቴጂ ከመንገድ
ማር አገኘሁ ያልሽው
ወለል ካለው ሜዳ ወርቅ አልማዝ ልብ በይ
ዕንቁ አገኘሁ ያልሽው
በገሃድ አልታየም ያንቺስ ህልም አልሆነም
አንቺ እንደፈታሽው
ልፍታልሽ እኔ ህልምሽ ቅዠት ነው
ያሰብሽው ሁሉ እንቆቅልሽ ነው
ገነቱም ሲኦል ሜዳው ገደል ነው
አልማዙም ነሃስ ማሩም እሬት ነው
እኔማ ከሃዲ ብዬ አልሰይምሽም
ዘንድሮስ ጠላሽኝ ብዬ ስም አልሰጥሽም
አጀብ ነው ኮኮብ ቆጣሪው አዋቂው በዝቶ
ማን ይመን ማን ይርታ
በዳይ ተበዳይ ግራ ተጋብቶ
እምባ ካይንሽ ሽፋን
ከጉንጭሽ ካይንሽ ዳር
ሲታፈስ ሲቀዳ
ብያኔው ተዛባ እውነት ነው ተባለ
አረግሽኝ ባለ እዳ
ፍርዱ ደፈራርሶ ጉሽ ሆኖ ባይጠራም
ቅራሬው ባይቀርም
በሰፈሩት ቁና እያደር አንድቀን
መሰፈር አይቀርም
እኛው ተማምነን ፈር ካልያሲያዝነው
ስንክብ ኖረን ካፈራረሰነው
ቅዠቱን ሁሉ እውን ነው ካልነው
ምኑን ከረምነው ምኑን ገፋነው
እኔማ ብካሰስሽም አላገኝ ፍርዴን
ልቻለው ያቃጥለው እንጂ ይብላው ሆድ ሆዴን
እንግዲህ በዳይ ተበዳይ እስከሚታወቅ
ይበቃል በሆድ ቂም ይዞ ባፍ ከመታረቅ
እንግዲህ ሳንተማመን እንዴት እንዝለቅ
ዘንድሮስ ስንተዋወቅ አንተላለቅ
እኔማ በብቸኝነት ልኑር ያለሰው
ዘንድሮስ እሱ ያመጣውን እሱ ይመልሰው
Shear to your beloved one
@ethiopian_music_lyrics
#ታምራት_ደስታ# ለምን_የለኝም_አልሽ
ሰው ኖሮሽ እንደሌለዉ ለይምሰል መታየቱ
ማስረዳት መንገር ስትችይ ሁሉንም በስራቱ
ፍቅር ፍቅር ሲያሰኘኝ ትዝ ሲለኝ ስሜቱ
ቆይ ለምን አስፈለገ ማስመሰል መዋሸቱ
ይህን ሁሉ ጊዜ የኖርኩት ራሴን ገትቼ
ዉስጤ እንዳይጎዳ ብዬ ነዉ ይህኑ ፈርቼ
አንቺን ሰበብ አርጎ ትካዜዉ በፍቅር ስሜቴ
ይሄዉ የፈራሁት አልቀረም ዞሮ ገባ ቤቴ
(እህህ) ፍቅርን ምዬ (እህህ) ባልል ሁለተኛ
(እህህ) ሰዉ አልቀርብም (እህህ) ሳልሆን እርግጠኛ
(እህህ) ፍቅር ህይወት (እህህ) መሆኑን ባላጣም
(እህህ) ግን ቸኩዬ (እህህ) ሰበብ አላመጣም
ሰው ኖሮሽ እንደሌለዉ ለይምሰል መታየቱ
ማስረዳት መንገር ስትችይ ሁሉንም በስራቱ
ፍቅር ፍቅር ሲያሰኘኝ ትዝ ሲለኝ ስሜቱ
ቆይ ለምን አስፈለገ ማስመሰል መዋሸቱ
ሰው ኖሮሽ እንደሌለዉ ለይምሰል መታየቱ
ማስረዳት መንገር ስትችይ ሁሉንም በስራቱ
ፍቅር ፍቅር ሲያሰኘኝ ትዝ ሲለኝ ስሜቱ
ቆይ ለምን አስፈለገ ማስመሰል መዋሸቱ
አንድም ነገር ሳትቀር ላትሆኚኝ ፍቅራችን ላይፀና
ዘክዝኬ መንገሬ ነደደኝ የቤቴን ገመና
እዉነት መስሎኝ ያልሽኝ አመንኩሽ አወይ ሞኝነቴ
ስንት አቅጄ ነበር ለፍቅርሽ እኔማ በቤቴ
(እህህ) አልወቅስሽም (እህህ) መቼም ሆኗል አንዴ
(እህህ) ሰዉ ልርቅ ነዉ (እህህ) ደግሞ እንደልማዴ
(እህህ) ሳልጀምረዉ (እህህ) ሳላገኝ እንዳጣሽ
(እህህ) ሰዉ እያለሽ (እህህ) ለምን የለኝምአልሽ
ለምን ለምን የለኝም አልሽ
ለምን ለምን የለኝም አልሽ
ግን ለምን ለምን የለኝም አልሽ
ቆይ ለምን ለምን የለኝም አልሽ

Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ማዲንጎ_አፈወርቅ# ሞኙ_ልቤ

ካምናው ካልተማርኩኝ ተመልሼ
እኔም ዛሬም ከደገመኝ
እርምን አላቅ ብዬ እንደገና
አዬ ሰው ማመን ካመመኝ
አሀ ሞኙ ልቤ አሀ ያልተደለ
አሀ ምን ሊፈይድ ከታለለ
የካብኩት ተናደ ባለማወቅ ስገነባው ፈርሶ
ባፀዳው ቆሸሸ እንደገና የፀዳው ደፍርሶ
ወርቅ አይደለ ነገር አይጣራ በእሳት አልፈትሸው
የቸገረ ነገር ግራ ገባኝ በምን ይለያል ሰው
ቀድሞ አለመጠንቀቅ ጥንቱን አለመፍራት
ሀይለኛ ዱላ ነው ያረፈብኝ
ማገገሜን እንጃ ምን ተሻለኝ
እንደማንገናኝ ልቤ እያወቀው
አፍቅሮ መለየት መንፈሴን ጨነቀው
አንቺም ላታገኚኝ እኔም ያንቺ ላልሆን
ያለመረሳትሽ ምስጢሩ ምን ይሆን
ካምናው ካልተማርኩኝ ተመልሼ እኔም ዛሬም ከደገመኝ
እርምን አላቅ ብዬ እንደገና አዬ ሰው ማመን ካመመኝ
አሀ ሞኙ ልቤ አሀ ያልታደለ
አሀ ምን ሊፈይድ አሀ ከታለለ
መቁረጥ ከተሳነኝ ምን ይደረግ አውቆ እንዳላወቀ
ይበለው ምናለ ልቤንማ ዳግም ከወደቀ
ቁስሌም ላይጠገን የበፊቱ ጠባሳዉ ላይጠፋ
ከተመለስክበት ሞኙ ልቤ በል እንግዲህ ልፋ
በትካዜ ብሩሽ በሀሳብ ሸራ ላይ
ስስል ከረምኩና ሳሳምርሽ
ህልም እልም ሆንሽና ዛሬም የለሽ
እንደማንገናኝ ልቤ እያወቀው
አፍቅሮ መለየት መንፈሴን ጨነቀው
አንቺም ላታገኚኝ እኔም ያንቺ ላልሆን
ያለመረሣትሽ ምስጢሩ ምን ይሆን
አሀ ሞኙ ልቤ አሀ ያልታደለ
አሀ ምን ሊፈይድ አሀ ከታለለ....

Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ደረጄ_ዱባለ# ግድ_የለም_ልቤ_ይችላል
ግድ የለም ልቤ ይችላል
ችላለሁ ይሁን ቢያመኝም
ጨክኖ አንቺን ሚጠላ
አረ እኔስ አንጀት የለኝም ፪
ያን ፍቅር ባወራ አንደበት
ስምሽን እንዲያ አወድሼ
ግድ የለም ሕመሙን እችላለሁ
ጠላዃት አልልም መልሼ
ከንግዲህ ከኔ ጋር የለችም
እያልኩኝ ስምሽን ላቦካ
እሺ የሚል ልቦና የለኝም
ፍቅርሽን አረሳም እኔ `ኳ
ስምሽን ለሰው አላነሳም ሄጄ
የለኝም አቅሙ ብትወጪም ከሄጄ
እሺ አይልም የለመደሽ ጎኔ
ባንቺ ልጨክን አልችልም እኔ ፪
ግድ የለም ልቤ ይችላል
ችላለሁ ይሁን ቢያመኝም
ጨክኖ አንቺን ሚጠላ
አረ እኔስ አንጀት የለኝም ፪
ማረፍያ ቢያሳጣኝም ፍቅርሽ
ናፍቆትሽ ቢያሳየኝ አበሳ
ምን አንጀት ምንስ መቻያ አለኝ
ያ ጣፋጭ ፍቅርሽን ሚረሳ
ቀን ከሌት ሂወቴ ቢመርም
ቢሰበር መውደዴ ቢደማ
አንጀቴን አስሬ እችላለሁ
ክፉሽን መጥፎሽን አልስማ
ያለፈው ፍቅር ያ ጣፋጭ ደስታ
ስንቅ ይሆነኛል ያንቺ ትዝታ
ግድ የለም ባትኖሪም ከጎኔ
ባንቺ ልጨክን አልችልም እኔ ፪

Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ሄለን_በርሄ # የኔ_ፍቅር

ባትኖርም ካጠገቤ ከጎኔ ብትለየኝም
እኔስ አይሃለሁ አንተ ባታየኝም
ሳይህ ሳይህ ባድር ብዉል አይወጣልኝም
ፍቅር ያንተስ ፍቅር ፍቅር ያንተስ ፍቅር
ካጠገብህ ሁኜ ባላጫዉትህም
ገላህን አቅፌ ምንም ባልስምህም
በመንፈስ ካንተዉ ነኝ መቸም አልለይም
በሃሳብ መነጸር ሁሌ ነዉ የማይህ
ዉቅያኖስ ባህሩ አድማስ ብጋርደኝ
ወሳንተ መምጣቴን ማንም አያግደኝ መምጫ መንገድ ሁሉ ቢዘጋ
ቢታገድ
ፍቅር ያደርሰኛል ባሳብ አየር መንገድ
የኔ ፍቅር ፍቅር አገናኝተህ ከምትለየኝ
የኔ ፍቅር ፍቅር ምነዉ በፊት ባታሳየኝ
የኔ ፍቅር ፍቅር ወይ ዉሰደኝ ወይ አምጣልኝ
የኔ ፍቅር ፍቅር ያለዚያማ ጉዴ ነዉ እንጃልኝ ቀኑን በትካዜ ብቻየን
ሳወራ
ደግሞ ሊተካልኝ ሌሊቱም በተራ
ገና ገደም እንዳልኩ ካልጋዉ ስንገናኝ
የሃሳብ ሰመመን ጉዞ ነዉ የሚቀናኝ
ድንገት ከተፍ ስል ካለህበት ቦታ
እየተላቀስን በናፍቆት በደስታ ታዲያ ምን ያደርጋለ ነበር ቢሆን
በዉኔ
ለካስ በህልሜ ነዉ የማገኝህ እኔ
የኔ ፍቅር ፍቅር እዉን አርገዉ ፍታዉ ህልሜን
የኔ ፍቅር ፍቅር እንድወጣዉ ርሃብ ጥሜን
የኔ ፍቅር ፍቅር ወይ ዉሰደኝ ወይ አምጣልኝ
የኔ ፍቅር ፍቅር ያለዚያማ ጉዴ ነዉ እንጃልኝ
Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ዲጄ_ሮፍናን# ፒያሳ_ላይ

ትዝ ይለኛል እንደ ትላንት
የመጀመሪያ ቀን ሳያት
ያኔ የቬል ሱሪው ነገር
አፍሮ ብጥር ብጥር ብጥር
ከአዲስ ከተማ በቶሎ
(አይ በቶሎ)
ጎዞዬ ቤቴ አራት ኪሎ
(አይ አራት ኪሎ)
ልጅት ነች ከናዝሬት ስኩል
(ናዝሬት ስኩል)
ነገሯ በአራዳ በኩል።
በግርግሩ መሀል ተያየን
አኔ እና እሷ ያኔ ተገናኘን
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ
ትዝ ይለኛል አይኔ ከአይንሽ
መጀመሪያ ስተዋወቅሽ
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ
ታሪክ ያለው እጅ ወደላይ።
አዲስ አበባን
ሳያት ሰባዎቹ መሀል
ትዝ ይለኛል ብዙ ነገር
ሮሀ እና የአንቺ ፍቅር
አባትሽ ያ ጀነራል
(ያ ጀነራል)
አስረው ሲገርፉ ወንድሜን
(ወነድሜን ወንድሜን)
እኔ እና አንቺ ግን አልፈናል
(አው አልፈናል)
ፍቅርን በባለአንጣዎች መሀል
(አዬ አዬ)
አስታውሳለው መፅሀፍቶቹን
ሳመጣልሽ የሀዲስ በአሉ ሎሬት ፀጋዬን
ከአራዳው ስር ብለን ተቀጣጥረን
አውቶቢሷ ሳትመጣ በእግሬ እቀድማት ነበር።
በግርግሩ መሀል ላይሽ
ከራዳው ስር አንቺን ላገኝሽ
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ
አይረሳም የጥንቱ ነገር
ያሳለፍነው ከደጉ መንደር
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ
ታሪክ ያለው እጅ ወደላይ።
ጨዋታ ጨዋታ ከአራዳው ቦታ
(ጨዋታ ጨዋታ ከአራዳው ቦታ)
ሳሚልኝ ቤቱን ጊዮርጊስን አዬ
(ሳሚልኝ ቤቱን ጊዮርጊስን አዬ)
ጥምቀት ነው ጨዋታ ከአራዳው ቦታ
(ጥምቀት ነው ጨዋታ ከአራዳው ቦታ)
ሸኘው ታቦቱን አድዋ ዘማቹን አዬ (ሸኘው ታቦቱን አድዋ ዘማቹን
አዬ)
ዘራፍ ዘራፍ ዘራፍ

Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
ለወጣቱ አቀንቃኝ እርዳታ ተጠየቀ!

ተወዳጁ ሙዚቀኛ ሙሌ ሐመልማሎ በተለይም ከኤፍሬም አማረ ጋር "ተሸንፊያለሁ" በሚለው ስራው በስፋት የሚታወቀው አርቲስት ሙሉአለም በደረሰበት የኩላሊት ህመም ዲያለሲስ እንዲያደርግ በሀኪሞች ተነግሮታል።

እንደሚታወቀው ይህ ሂደት ከፍተኛ ገንዘብን የሚጠይቅ ሲሆን በአርቲስቱ አቅም ደግሞ እስከ መጨረሻው መግፋት የማይቻል በመሆኑ ሁሉም ሰው ድጋፉን ያሳየው ዘንድ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን...

ይህ ወጣት አርቲስት ብዙ የሚጠበቅበት ገና ሙዚቃን ጀመርኳት እያለ እሩቅ በሚያስብበት በዚህ ሰዓት እንዲህ ባለው አደጋ ተደናቅፎ እንዳይቀር ሁላችንም በመረባረብ የበኩላችንን ማድረግ ይኖርብናል።

አርቲስት የህዝብ ሀብት ነው። ህይወቱን እና ጊዜውን ለህዝብ ሰቶ የሚሰራ ጥበበኛ መጠለያው መሸሸጊያው ይኼው ያገለገለው ህዝብ ነውና ሁላችን ወደ ህዝብ እንጮሃለን..? ድጋፋችሁን ሽተን ደጃቹን የምንረግጥ ድርጅቶችም ትተባበሩን ዘንድ በዙሁ አጋጣሚ ለመጠየቅ እንገደዳለን።

ከፀሎት ጀምሮ ሁላችንም በምንችለው አቅም ከአርቲስቱ ጎን በመሆን እንርዳው (ጓደኞቹ) Mulualem Takele 1000182044184 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
#share #share #share #share
@ethiopian_music_lyrics
#አብነት_አጎናፍር#ኢትዮጵያ#

አያውቁንም ለካ አያውቁንም
አያውቁንም እኛን አያውቁንም
አያውቁንም እንዴት አያውቁንም
ላላወቀን ኢትዮጵያዊ እንደሆንን
ኢትዮጵያ ይገባሻል ክብር ውዳሴ እናቴ
ምን ቢርቁም የማትረሺ የልጅነቴ/2x/
ኢትዮጵያ የማንነት ልዩ ቀለሜ ኩራቴ
ከፍ ላርገው ሰንደቅ አርማሽን እንደልጅነቴ/3x/
ምን አላት ምን ሰሩ ማን አላት ለሚሉ ያሆ አገሬ ያሆ
ሊንቁሽ ላሰቡ የቱ ጋር ናት ላሉ ያሆ አገሬ ያሆ
የማዕዘን ድንጋይ አንቺ የታሪክ ሙዳይ ያሆ አገሬ
ቀድመሽ ብትዘገይም ትሆኛለሽ ከላይ ያሆ አገሬ ያሆ
ሀገሬ ሀገሬ ሀገሬ ሀገሬ
ውሃም ሳይጠማን ሰላም ሳይርበን
ችግር ሳይደፍረን ኢትዮጵያ ኑሪልን
ቁጣው የነብር ግርማው ያንበሳ
እሳት ነው ህዝብሽ ሆ ብሎ ሲነሳ
አሀ እሆ አሀ
ልክ እንደግማድ የተሸከመው ማተብ መለያው
ሰንደቅ አላማው ነው
ያሆ በልጃሌው ያሆ በል ምነው
ያሆ በልጃሌው ያላወቀህ ማነው
አሀ እሆ አሀ
ኢትዮጵያ ልብሽ ካባ ውጪ አደባባይ ኩራቴ
ጥላ ክብሬ መስታወቴ ነሽ የልጅነቴ/2x/
ኢትዮጵያ የመንታ እናት እንቅልፍ የሌለሽ እናቴ
የደስታዬ የቁጭቴ ቀን የልጅነቴ/4x/
እንዲህ ነን እያለ ኢትዮጵያዊ ማለት ያሆ ሀገሬ ያሆ
ቀና ብሎ ይሂድ አንገት በደፋበት ያሆ አገሬ ያሆ
ይመርብሽ ሁሌ ስምሽ ያስተጋባ ያሆ ሀገሬ ያሆ
ድል በድል ሁኝልኝ ሁሌም ውሮ ወሸባ ያሆ ሀገሬ ያሆ
ሀገሬ ሀገሬ ሀገሬ ሀገሬ
ውሃም ሳይጠማን ሰላም ሳይርበን
ችግር ሳይደፍረን ኢትዮጵ ኑሪልን
ቁጣው የነብር ግርማው ያንበሳ
እሳት ነው ህዝብሽ ሆ ብሎ ሲነሳ
አሀ እሆ አሀ
ልክ እንደግማድ የተሸከመው ማተብ መለያው
ሰንደቅ አላማው ነው
ያሆ በልጃሌው ያሆ በል ምነው
ያሆ በልጃሌው ያላወቀህ ማነው
አሀ እሆ አሀ

Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ሃመልማል_አባተ #ወድሃለሁ

መች ጠላሁህ ወድሃለሁ
እዉነት እዉነት እልሃለሁ
እንደኔ ሚወድህ ባለም ላይ
ሰው አለ ወይ(2x)
ፍቅር በቃ ተከተተ
ብየ ልቤን ሰጠዉ ላንተ
በመዉደድህ ገዝተኽኛል
ካንተ ወዲያ ምን ያምረኛል
እንደምወድህ ልብህ ያዉቀዋል
እንደበትህ ግን ይደብቀዋል
አታቃልብኝ የፍቅሬን ዋጋ
ሃሳቤ አንተ ነህ ሲመሽ ሲነጋ
አትወጅኝም አትበለኝ
ካንተ ወዲያ ማን አለኝ
በሙሉ ልብ እመነኝ
ዛሬም ነገም ያንተዉ ነኝ(2x)
እኔ ዛሬም እወድሃለሁ
ነገም እወድሃለሁ
መች እጠላሃለሁ(2)
ከቤተሰብ ተነጥየ
ስለፍቅር ሁሉን ጥየ
ያንተ ልሆን ወስኛለሁ
ሌላ ለምን እመኛለሁ
ሁሉ ነገርህ ተመችቶኛል
ምን ጎደለብኝ ሁሉ ሞልቶኛል
አቋሜ ግልጽ ነዉ አይወላዉልም
እኔ ካላንተ መኖር አልችልም
አትወጅኝም አትበለኝ
ካንተ ወዲያ ማን አለኝ
በሙሉ ልብ እመነኝ
ዛሬም ነገም ያንተዉ ነኝ(2)
እኔ ዛሬም እወድሃለሁ
ነገም እወድሃለሁ
መች እጠላሃለሁ
እወድሃለሁ እወድሃለሁ(2).

Shear to your friends for more lyrics@ethiopian_music_lyrics
#ዘቢባ_ግርማ #ገራገር

ገራገር አንተ ልጅ አራዳ ሆዴ ነፍስ ነገር
"ገራገር"
ገራገር እንዴት አረክልኝ የመውደዴን ነገር
"ገራገር"
ገራገር አንተን ባዩ በዝቶ ልቤ ከሚቸገር
"ገራገር"
ገራገር ምነው ባወቀልኝ የአኔ እንደሆንክ ሀገር
"ገራገር"
"ገራገር"
ውድ ያረገህን የፍቅር አድባር
እያባበልኩት በሜሪ ክራር
"ወይ አራዳ" ጭንቀት ምንገዴን
"ስንት አሳየኝ" አንተን መውደዴን
ሆንክብኝና የማልተውህ ሰው
አለሁ ዱካህን ሳድን ሳስሰው
"ወይ አራዳ" እያልኩ አጅሬ
"ስንት አሳየኝ" አንተን ማፍቀሬ
ከስንቱ አይናባይ አስኮብላይ
ከስንቷስ የብርሌ አንገት
መግባባት ችዬ እንላዳህ
የኔ ነው ብዬ ልሟገት
አለሁልህ "እሺ እንዳልኩልህ"
አለሁልህ "ማሬ እያልኩልህ"
አለሁልህ "እሺ እንዳልኩልህ"
አለሁልህ "ማሬ እያልኩልህ"
ገራገር አንተ ልጅ አራዳ ሆዴ ነፍስ ነገር
"ገራገር"
ገራገር እንዴት አረክልኝ የመውደዴን ነገር
"ገራገር"
ገራገር አንተን ባዩ በዝቶ ልቤ ከሚቸገር
"ገራገር"
ገራገር ምነው ባወቀልኝ የአኔ እንደሆንክ ሀገር
"ገራገር"
"ገራገር"
ካይንህ እያጣው ያይኔን መድሀኒት
አልለይ አለኝ ቀንና ለሊት
"ወይ አራዳ" ጭንቀት ምንገዴን
"ስንት አሳየኝ" አንተን መውደዴን
ፈርዶብኝ ባንተ ሳልውጥ ምራቄን
ፈራሁ ሰሞኑን አንዳልጥል ጨርቄን
"ወይ አራዳ" እያልኩ አጅሬ
"ስንት አሳየኝ" አንተን ማፍቀሬ
ከስንቱ አይናባይ አስኮብላይ
ከስንቷስ የብርሌ አንገት
መግባባት ችዬ እንላዳህ
የኔ ነው ብዬ ልሟገት
አለሁልህ "እሺ እንዳልኩልህ"
አለሁልህ "ማሬ እያልኩልህ"
አለሁልህ "እሺ እንዳልኩልህ"
አለሁልህ "ማሬ እያልኩልህ"
"ወይ አራዳ" ጭንቀት ምንገዴን
"ስንት አሳየኝ" አንተን መውደዴን
"ወይ አራዳ" እያልኩ አጅሬ
"ስንት አሳየኝ" አንተን ማፍቀሬ
"ወይ አራዳ" ጭንቀት ምንገዴን
"ስንት አሳየኝ" አንተን መውደዴን
"ወይ አራዳ" እያልኩ አጅሬ
"ስንት አሳየኝ" አንተን ማፍቀሬ
"ወይ አራዳ" ጭንቀት ምንገዴን
"ስንት አሳየኝ" አንተን መውደዴን
"ወይ አራዳ" እያልኩ አጅሬ
"ስንት አሳየኝ" አንተን ማፍቀሬ

Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ጊልዶ_ካሳ #ላገባ_ነው
ልቤ አንቺን ወዶ
አይቀርም በባዶ
ታድሎሻል አንቺን ውዴን ነያ ነያ ነይ ነይ
እኔ ላንቺው ቢዬ
መጣሁኝ ቸኩዬ
ሌላ ሁሉን ቲቼ ቲቼ ዬ ይ ዬ
አይኖችሽ ካይኖቼ ይነጋገራሉ
ልብሽም ከልቤ ይተዋወቃሉ
ህይወቴ ሰመረ (ሰመረ)
በፍቅርሽ አማረ (አማረ)
መጨነቄን ጥዬ (ጥዬ ጥዬ ጥዬ)
እሰይ ላገባ ነው
እሰይ ላገባ ነው
እኔስ ላገባ ነው
አዎ ላገባ ነው
እሰይ ላገባ ነው
እሰይ ላገባ ነው
እኔስ ላገባ ነው
አዎ ላገባ ነው
ልቤ አንቺን ወዶ
አይቀርም በባዶ
ታድሎሻል አንቺን ዉዴን ኔያ ኔያ ነይ ነይ
እኔ ላንቺው ቢዬ
መጣሁኝ ቸኩዬ
ሌላ ሁሉን ቲቼ ቲቼ ዬ ይ ዬ
አይኖችሽ ካይኖቼ ይነጋገራሉ
ልብሽም ከልቤ ይተዋወቃሉ
ህይወቴ ሰመረ (ሰመረ)
በፍቅርሽ አማረ (አማረ)
መጨነቄን ጥዬ (ጥዬ ጥዬ ጥዬ)
እሰይ ላገባ ነው
እሰይ ላገባ ነው
እኔስ ላገባ ነው
አዎ ላገባ ነው
እሰይ ላገባ ነው
እሰይ ላገባ ነው
እኔስ ላገባ ነው
አዎ ላገባ ነው
ልብ የምተርክ ዉቤት አይኔ ሲያይ ጠፍቶ
ተሽሞንሙኖ ፍቅርን አዬው ባንቺው ተሞልቶ
የአይኖቿ ነፀብራ እንቁ የምያስንቅ
የጥርሷማ ፍንዳቅ ከኳክብት ሚደምቅ
ለአዳምም ሄዋንን ፈጠራት
ለሳራም አብርሃምን የሰጣት
ከዙፋኑ ሰጠኝ አንቺን ከላይ
አንቺን ከላይ
አዎ ከላይ
እሰይ ላገባ ነው
እሰይ ላገባ ነው
እኔስ ላገባ ነው
አዎ ላገባ ነው
እሰይ ላገባ ነው
እሰይ ላገባ ነው
እኔስ ላገባ ነው
አዎ ላገባ ነው

Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
ለጠቅላላ ዕውቀት...

1- የአለማችን ትልቋ ሀገር ሩስያ ስትሆን 17.09 ሚሊየን km2 የሆነ የቆዳ ስፋት አላት::

2- በአለማችን ላይ በርሀማዋ ሀገር ሊቢያ ስትሆን ከአጠቃላይ የቆዳ ስፋቷ 99% የሚሆነው በረሀማነት የሚፈረጅ ነው::

3- በአለማችን ላይ ምንም አይነት ወንዝ የሌላት ሀገር ሳውድ አረቢያ ነች::
4- ለሴቶች የመምረጥ መብትን ቀድማ የሰጠች ሀገር ኒውዝላድ ነች::

5- አሜሪካ በአለማችን ላይ ብዙ ክርሰቲያኖች የሚኖሩባት ሀገር ስትሆን ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛቷ 245.9 ሚሊየን የሚሆኑት ክርሰቲያኖች ናቸው:

6- ብዙ የሆነ የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ህዝብ ያላት ሀገር ኢንዶኔዢያ ስትሆን ከ209 ሚሊየን በላይ የሚሆነው ህዝቧ ሙስሊሞች ናቸው::

7- በአለማችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የሀይቅ ብዛት ያላት ሀገር ካናዳ ስትሆን ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ሀይቆች ሲኖራት ይህም በአለማችን ላይ ካሉት የሀይቆች ብዛት 60% ይሸፍናል::

8- በአለማችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የግድያ ወንጀል የሚፈፀምባት ሀገር ኤል ሳልቫዶር ስትሆን በአማካኝ ከ100,000 ሰዎች ውስጥ 55.5% የሚሆኑት ግድያ ይፈፀምባቸዋል::

9- በሀገሯ ፓርላማ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የሴቶች ቁጥር ያላት ሀገር ሩዋንዳ ስትሆን በፓርላማዋ ካሉት ጠቅላላ መቀመጫዎ ውስጥ 56.3% (50/80) የሚሆነው የተያዘው በሴቶች ነው::

10- ዴንማርክ በአለማችን ላይ አነስተኛ የሆነ የሙስና ወንጀል የሚፈፀምባት ሀገር ናት::

ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው ሼር
@ethiopian_music_lyrics
#መልካሙ_ተበጀ #በሳቅ_በጨዋታ
በሳቅ በጨዋታ በደስታ በሀዘን
ባለፉት አመታት ስንቱን አሳለፍን
ስንት ደስታ አየን ስንት አየን መከራ
ሲፈራረቁብን በተራ በተራ
ደቂቃ አልፎ ሰአት ሲተኩ ቀናቶች
አለፉ ተረሱ እነዚያ ጊዜያቶች
ስንት ደስታ አየን ስንት አየን መከራ
ሲፈራረቁብን በተራ በተራ
እንደጥሩ ታሪክ እንደጥሩ ዝና
ልናወራዉ በቃን ያ ሁሉ አለፈና
መከራና ስቃይ ካደረ አይቆጭ ምነዉ
በኖርነዉ ጊዜያችን ስንቱን አሳለፍነዉ
በሳቅ በጨዋታ በደስታ በሀዘን
ባለፉት አመታት ስንቱን አሳለፍን
ስንት ደስታ አየን ስንት አየን መከራ
ሲፈራረቁብን በተራ በተራ
ሰዉ ሁሉ ሲስማማ ሲፋቀር ሲዋደድ
ማታለል ሳይበዛ መዋሸት በገሀድ
በአፍ ቢለዋነት ሳይኖር ሰዉን ማረድ
ያ ደጉ ቀን ጠፋ እኛ ሳንወድ በግድ
የልጅነት ወራት የአበባዉ ጊዜአችን
ያ ለዛ ጨዋታ የዋህነታችን
ጎልማሳነት አልፎ እርጅና መጣና
ልናወራዉ በቃን ያ ሁሉ አለፈና
ያሳለፍነዉ ጊዜ ጥሩም ነዉ መጥፎም ነዉ
ግን ለተረት ያህል ስንቱን አሳለፍነዉ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ጃኖ_ባንድ #ዘው_ዘው


ከልጅ ካዋቂው መስሎ ጓደኛ
ቀኑን ሳያርፈው ለሊት ሳይተኛ
ካዘነው ሲያዝን ከሳቀው ሲስቅ
እዚ እያጣላ እዚያ ሲያስታርቅ
ደሞ በሌላ ልቡ እስኪረታ
እቺን ሲያገባ ያቺን ሲፈታ
ወጣ ገባ ሲል እዚም እዛም ጋር
ቀደመው ጊዜው አንዱን ሳይዘው
እንዲያው ዘው ዘው ... አይ ዘው ዘው
ጥርስ የታደለው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አሞኘው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አቄለው ... አይ ዘው ዘው
ዛሬ አለፈና ... አይ ዘው ዘው
ጥርሶቹም አልቀው ... አይ ዘው ዘው
ሳይወርሰው ሽበት ... አይ ዘው ዘው
በድዱ ሳቀው ... አይ ዘው ዘው
ቀብሮ በውስጡ ከያዘው እውነት
በልጦበት ስሙ ሲምል ሲገዘት
አፈ ቅቤው ሰው ዓለም ሳይበቃው
ሰማይ ልርገጥ ሲል መሬት እርቃው
በ ጠላው ውሸት ዛሬ ተወርሶ
የኀላውን ሲያይ የፈራው ደርሶ
ጊዜ በቁጭት ዚወዘውዘው
ምኑን ይልቀቀው የቱን ይያዘው
እንዲያው ዘው ዘው ... አይ ዘው ዘው
ጥርስ የታደለው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አሞኘው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አቄለው ... አይ ዘው ዘው
ዛሬ አለፈና ... አይ ዘው ዘው
ጥርሶቹም አልቀው ... አይ ዘው ዘው
ሳይወርሰው ሽበት ... አይ ዘው ዘው
በድዱ ሳቀው ... አይ ዘው ዘው
የሸሸለት ወዳጅ ጥርስ ላይመልሰው
አትሳቅ ለይምሰል እባክህ አንተ ሰው
ከንቱ ከመናገር በቡና ቤት ወሬ
ቀን ሳለ ተመለስ ተው ስማኝ አጅሬሬሬሬ
አርገው ቸብ ቸብ ጊዜን ላይዙት
ወገብ ትከሻን ቢወዘውዙት
ወናውን ከርሞ ዕድሜ ካለለት
እንኳን ጭፈራው ወጉስ መች ሊጥም (2X)
እንዲያው ዘው ዘው ... አይ ዘው ዘው
ጥርስ የታደለው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አሞኘው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አቄለው ... አይ ዘው ዘው
ዛሬ አለፈና ... አይ ዘው ዘው
ጥርሶቹም አልቀው ... አይ ዘው ዘው
ሳይወርሰው ሽበት ... አይ ዘው ዘው
በድዱ ሳቀው ... አይ ዘው ዘው
አይ ዘው ዘው


Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ሚኪያ_በኃይሉ # ደለለኝ


ደለለኝ ደለለኝ ደለለኝ (2x)
ማሬ ነሽ ብሎ አታለለኝ
ወተቴ እያሌ ሸነገለኝ
ቅቤ ምላስህ ገደለኝ
ደለለኝ
አቤትያንተ ምላስ ሂይዎት ይቀምማል
ከመዉደድ አስታሞ በፍቅር ያክማል
በፍቅርህ ደልለኝ ቃልህን ላድምጠው
የፍቅርህ ዉዳሴ ቸረይን ይታፍተው
ሁሉን ብታሞላኝ ቃልህ ቢደልለኝ
ስኳሩ ምላስህ ጠፍቶ ብያታልለኝ
ሰማዩም ምድሩም ሃብቴ የመሰለኝ
ተራራዉም ወንዙም ግዛቴ የመሰለኝ
ደለለኝ
ጨዋታህ ልዩ ነው ህዎትን ያደምቃል (2x)
ሃሳብ ምናምንቴ ጠራርጎ ያርቃል (2x)
ዉዳሰይህ ሸጋ ነው ፍቅርን ይሰብካል (2x)
ህዎትን አድስሶ ነፍስን ያረካል
ሂዎት ያድሳል ነፍስን ያረካል
[2x]
አቤት ያንተ ምላስ ሂዎት ይቀምማል
ከመዉደድ አስታሞ በፍቂር ያክማል
አንደበትህ መልካም ህመም ይፈዉሳል
የልብን ስብራት ያድሳል ያስረሳል
ደለለኝ ደለለኝ በፍቅርህ አታለለኝ
ማሬ ነሽ ስኳሬ ዎለላየ በለኝ
ቃልህ ሁሌም ጠፋጭ ቀና ትምሰለኝ
ሂዎት ሁሌም ብሩህ ሆና’ ትታየኝ
ደለለኝ
ጨዋታህ ልዩ ነው ህዎትን ያደምቃል (2x)
ሃሳብ ምናምንተይን ጠራርጎ ያርቃል (2x)
ዉዳሴ ሸጋ ነው ፍቅርን ይሰብካል (2x)
ህዎትን አድስሶ ነፍስን ያረካል
ሂዎት ያድሳል ነፍስን ያረካል

Shear to your best friends for more lyrics @ethiopian_music_lyrics
#አብነት_አጎናፍር #ለኔ_ካለሽ


አንቺን ብሎ ልቤ አልረጋ አለ
ባሳብ ካንቺ ጋር ሄዶ እየዋለ
አስቻለሽ ወይ ያለኔ ኑሮ
ከበደኝ እኔ እንጃ ዘንድሮ
አንቺን ብሎ ልቤ አልረጋ አለ
ባሳብ ካንቺ ጋር ሄዶ እየዋለ አስቻለሽ ወይ ያለኔ ኑሮ
ከበደኝ እኔ እንጃ ዘንድሮ ለኔ ካለሽ መቼም አይቀርም
ውድጅኝ ብዬ ሙጥኝ አልልም
ለኔ ካለሽ መቼም አይቀርም
ውድጅኝ ብዬ ሙጥኝ አልልም አለሁ
ይግባኝ አልጠየኩም
ክፉ ነሽ አላልኩም
ደግም ነሽ አልልም
ብቻ ግን አለሁ እራሴን ባልጥልም
አለሁ እንዳለሁ
አለሁ ይግባኝ አልጠየኩም ክፉ ነሽ አላልኩም
ደግም ነሽ አልልም
ብቻ ግን አለሁ እራሴን ባልጥልም
አለሁ እንዳለሁ ዘንድሮስ ቸገረኝ
እምባዬ አልደርቅ አለኝ
ሆዴም አልቆርጥ አለኝ
ድካሜ አሳዘነኝ
ፍቅር አልቆይም አለኝ
እየወሰወሰኝ ከማጥ ውስጥ ዘፈቀኝ
ዘንድሮስ ቸገረኝ
እምባዬ አልደርቅ አለኝ
ሆዴም አልቆርጥ አለኝ
ድካሜ አሳዘነኝ
ፍቅር አልቆይም አለኝ እየወሰወሰኝ
ከማጥ ውስጥ ዘፈቀኝ በርግጥ አታምኚም አንቺን ማሠቤ
እርቀሽ ስለሆድሽ ደፍተሽኝ እኔን
አልጠላሽም ስላልውደድሽኝ
ካሳብ እንድድን ብቻ ጠይቂኝ
በርግጥ አታምኚም አንቺን ማሠቤ
እርቀሽ ስለሆድሽ ደፍተሽኝ እኔን አልጠላሽም ስላልውደድሽኝ
ካሳብ እንድድን ብቻ ጠይቂኝ ለኔ ካለሽ መቼም አይቀርም
ውድጅኝ ብዬ ሙጥኝ አልልም
ለኔ ካለሽ መቼም አይቀርም
ውድጅኝ ብዬ ሙጥኝ አልልም አለሁ ይግባኝ አልጠየኩም
ክፉ ነሽ አላልኩም
ደግም ነሽ አልልም
ብቻ ግን አለሁ እራሴን ባልጥልም
አለሁ እንዳለሁ
አለሁ ይግባኝ አልጠየኩም ክፉ ነሽ አላልኩም
ደግም ነሽ አልልም
ብቻ ግን አለሁ እራሴን ባልጥልም
አለሁ እንዳለሁ ዘንድሮስ ቸገረኝ
እምባዬ አልደርቅ አለኝ
ሆዴም አልቆርጥ አለኝ
ድካሜ አሳዘነኝ
ፍቅር አልቆይም አለኝ
እየወሰው

Shear to your best friends for more lyrics @ethiopian_music_lyrics
#አስቴር_አወቀ # ስኳር


አለሜ መቼም እንደ ስኳር
አለሜ ይጣፍጣል ስምህ
አለሜ ደግሞም ምን ሊባል ነው
አለሜ ወደድኩኝ ደግሜ
አለሜ ጠይመይ ቀይ ዳማው
አለሜ ልዩ ነው ቀለሙ
አለሜ እንደው እንደ ስኳር
አለሜ ይጣፍታል ስሙ
እንደው እንደው ስሙ(3)
እንደው እንደው ስኳር ስኳር ስኳር ኣለኝ
ብቀምሰው ከንፈሩንተመኘሁኝ
አቤት አቤት አቤት እንዴት እሆናለው ባይ
ሰዉነቱን
አቤት አቤት አቤት(2) ያንተንስ ፈራሁኝ
እህል ኳንዳለኝ ያንተንስ ፈራሁኝ ለሩቅ
ትቀመሳለህ____ ትጣፍጣለህ እንደው እንደ ማር
እንደ ስኳር እንደ ስኳር
ስምክን ቢጠራ በየደቂቃው ኣትጠገብምበሚጣፍጠዉ እንደው
ትላለ ስኳር ስኳር
አለሜ ሳመኝ በከንፈርህ
አለሜ
አለሜ ኣዲስ ነገር የለም
አለሜ ጉዴ ኣንዲት ሰሞን ነው
አለሜ እኔም ስኳር ነኝ
አለሜ ፍቅር ነኝ ፍቅር
አለሜ ለወደደኝ ደስታ
አለሜ ላፈቀረኝ ማር
እንደው እንደው ስሙ(3)
እንደው እንደው ስኳር ስኳር ስኳር ኣለኝ
ብቀምሰው ከንፈሩን
አቤት አቤት አቤት እንዴት እሆናለው ባይ
ሰውነቱን
አቤት አቤት አቤት(2) ያንተንስ ፈራሁኝ
እህል ኳንዳለኝ ያንተንስ ፈራሁኝ ለሩቅ ተመኘሁን
ትቀመሳለህ____ ትጣፍጣለህ እንደው እንደ ማር
እንደ ስኳር እንደ ስኳር
ስምክን ቢጠራ በየደቂቃው ኣትጠገብም እንደው
ትላለ ስኳር ስኳር
አለሜ መቼም እንደ ስኳር
አለሜ ይጣፍጣል ስምህ
አለሜ ደሞም ምን ሊባል ነው
አለሜ ወደድኩኝ ደግሜ
አለሜ ጠይመይ ቀይ ዳማው
አለሜ ልዩ ነው ቀለሙ
አለሜ እንደው እንደ ስኳር
አለሜ ይጣፍታል ስሙ
እንደው እንደው ስሙ(3)
እንደው እንደው ስኳር ስኳር ስኳር ኣለኝ
ብቀምሰው ከንፈሩን
አቤት አቤት አቤት እንዴት እሆናለው ባይ
ሰዉነቱን (2)
አቤት አቤት አቤት(2) ባይ ሰውነቱንሰዉነቱን
እንዴት እሆናለው ባይ ሰዉነቱን
ስኳር ስኳር ኣለኝ ብቀምሰው ከንፈሩን
እንዴት እሆናለው
አይ
አይ ሰዉነቱን
አይ ሰዉነቱን
ባይ ሰዉነቱን
ባይ ሰዉነቱንንንንንንንንንንንንንንንንንን

Shear to your best friends for more lyrics @ethiopian_music_lyrics