Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ጃኖ_ባንድ #ዘው_ዘው


ከልጅ ካዋቂው መስሎ ጓደኛ
ቀኑን ሳያርፈው ለሊት ሳይተኛ
ካዘነው ሲያዝን ከሳቀው ሲስቅ
እዚ እያጣላ እዚያ ሲያስታርቅ
ደሞ በሌላ ልቡ እስኪረታ
እቺን ሲያገባ ያቺን ሲፈታ
ወጣ ገባ ሲል እዚም እዛም ጋር
ቀደመው ጊዜው አንዱን ሳይዘው
እንዲያው ዘው ዘው ... አይ ዘው ዘው
ጥርስ የታደለው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አሞኘው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አቄለው ... አይ ዘው ዘው
ዛሬ አለፈና ... አይ ዘው ዘው
ጥርሶቹም አልቀው ... አይ ዘው ዘው
ሳይወርሰው ሽበት ... አይ ዘው ዘው
በድዱ ሳቀው ... አይ ዘው ዘው
ቀብሮ በውስጡ ከያዘው እውነት
በልጦበት ስሙ ሲምል ሲገዘት
አፈ ቅቤው ሰው ዓለም ሳይበቃው
ሰማይ ልርገጥ ሲል መሬት እርቃው
በ ጠላው ውሸት ዛሬ ተወርሶ
የኀላውን ሲያይ የፈራው ደርሶ
ጊዜ በቁጭት ዚወዘውዘው
ምኑን ይልቀቀው የቱን ይያዘው
እንዲያው ዘው ዘው ... አይ ዘው ዘው
ጥርስ የታደለው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አሞኘው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አቄለው ... አይ ዘው ዘው
ዛሬ አለፈና ... አይ ዘው ዘው
ጥርሶቹም አልቀው ... አይ ዘው ዘው
ሳይወርሰው ሽበት ... አይ ዘው ዘው
በድዱ ሳቀው ... አይ ዘው ዘው
የሸሸለት ወዳጅ ጥርስ ላይመልሰው
አትሳቅ ለይምሰል እባክህ አንተ ሰው
ከንቱ ከመናገር በቡና ቤት ወሬ
ቀን ሳለ ተመለስ ተው ስማኝ አጅሬሬሬሬ
አርገው ቸብ ቸብ ጊዜን ላይዙት
ወገብ ትከሻን ቢወዘውዙት
ወናውን ከርሞ ዕድሜ ካለለት
እንኳን ጭፈራው ወጉስ መች ሊጥም (2X)
እንዲያው ዘው ዘው ... አይ ዘው ዘው
ጥርስ የታደለው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አሞኘው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አቄለው ... አይ ዘው ዘው
ዛሬ አለፈና ... አይ ዘው ዘው
ጥርሶቹም አልቀው ... አይ ዘው ዘው
ሳይወርሰው ሽበት ... አይ ዘው ዘው
በድዱ ሳቀው ... አይ ዘው ዘው
አይ ዘው ዘው


Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics