Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ጃኖ_ባንድ #ዘው_ዘው


ከልጅ ካዋቂው መስሎ ጓደኛ
ቀኑን ሳያርፈው ለሊት ሳይተኛ
ካዘነው ሲያዝን ከሳቀው ሲስቅ
እዚ እያጣላ እዚያ ሲያስታርቅ
ደሞ በሌላ ልቡ እስኪረታ
እቺን ሲያገባ ያቺን ሲፈታ
ወጣ ገባ ሲል እዚም እዛም ጋር
ቀደመው ጊዜው አንዱን ሳይዘው
እንዲያው ዘው ዘው ... አይ ዘው ዘው
ጥርስ የታደለው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አሞኘው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አቄለው ... አይ ዘው ዘው
ዛሬ አለፈና ... አይ ዘው ዘው
ጥርሶቹም አልቀው ... አይ ዘው ዘው
ሳይወርሰው ሽበት ... አይ ዘው ዘው
በድዱ ሳቀው ... አይ ዘው ዘው
ቀብሮ በውስጡ ከያዘው እውነት
በልጦበት ስሙ ሲምል ሲገዘት
አፈ ቅቤው ሰው ዓለም ሳይበቃው
ሰማይ ልርገጥ ሲል መሬት እርቃው
በ ጠላው ውሸት ዛሬ ተወርሶ
የኀላውን ሲያይ የፈራው ደርሶ
ጊዜ በቁጭት ዚወዘውዘው
ምኑን ይልቀቀው የቱን ይያዘው
እንዲያው ዘው ዘው ... አይ ዘው ዘው
ጥርስ የታደለው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አሞኘው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አቄለው ... አይ ዘው ዘው
ዛሬ አለፈና ... አይ ዘው ዘው
ጥርሶቹም አልቀው ... አይ ዘው ዘው
ሳይወርሰው ሽበት ... አይ ዘው ዘው
በድዱ ሳቀው ... አይ ዘው ዘው
የሸሸለት ወዳጅ ጥርስ ላይመልሰው
አትሳቅ ለይምሰል እባክህ አንተ ሰው
ከንቱ ከመናገር በቡና ቤት ወሬ
ቀን ሳለ ተመለስ ተው ስማኝ አጅሬሬሬሬ
አርገው ቸብ ቸብ ጊዜን ላይዙት
ወገብ ትከሻን ቢወዘውዙት
ወናውን ከርሞ ዕድሜ ካለለት
እንኳን ጭፈራው ወጉስ መች ሊጥም (2X)
እንዲያው ዘው ዘው ... አይ ዘው ዘው
ጥርስ የታደለው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አሞኘው ... አይ ዘው ዘው
ስንቱን አቄለው ... አይ ዘው ዘው
ዛሬ አለፈና ... አይ ዘው ዘው
ጥርሶቹም አልቀው ... አይ ዘው ዘው
ሳይወርሰው ሽበት ... አይ ዘው ዘው
በድዱ ሳቀው ... አይ ዘው ዘው
አይ ዘው ዘው


Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ጃኖ_ባንድ#
ይነጋል
አይገርምም መሽቶ ላይቀር
ፀሐይ ብትጠልቅም አይገርምም
አይደንቅም ደስታ ሊቸር
ጊዜ ቢያስጨንቅም አይገርምም
የዚች አለም ህይወት ፈተና
በዝቶ በኔ ምን ቢፀና
አስተምሮኝ ላይቀር ማለፉ
ለምን ላስብ ክፉ
ቢመሽም ቀኑ ቢጨልም
ለብርሃን እጅ አልሰጥ ቢልም
ቻል ሆድህን አስፋ
ተው አትቁረጥ ተስፋ
ብታጣም ቢፈተን ስጋህ
እናደ እሾህ ሳሩ ቢወጋህ
ቻል ሆድህን አስፋ
ተው አትቁረጥ ተስፋ
ወትሮም ሰው ባለም ፈተና
የታጨው ለድል ነውና
ጊዜ ብዙ ያረጋል
ቻል አርገው ይነጋል
ዳገቱን ላስብ ጀምሬው
አትበል ጣፋጭ ነው ፍሬው
ቻይ ሆድህን አስፋ
ተው አትቁረጥ ተስፋ
ለነፍስም ለስጋ ቅሪት
አንተው ነህ የአንተው መዳኒት
ቻይ ሆድህን አስፋ
ተው አትቁረጥ ተስፋ
መሸበር መፍራቱን ትተህ
ፅልመቱን እለፍ በርትተህ
ጊዜ ብዙ ያረጋል
ቻል አርገው ይነጋል

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics