Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#አብነት_አጎናፍር#ኢትዮጵያ#

አያውቁንም ለካ አያውቁንም
አያውቁንም እኛን አያውቁንም
አያውቁንም እንዴት አያውቁንም
ላላወቀን ኢትዮጵያዊ እንደሆንን
ኢትዮጵያ ይገባሻል ክብር ውዳሴ እናቴ
ምን ቢርቁም የማትረሺ የልጅነቴ/2x/
ኢትዮጵያ የማንነት ልዩ ቀለሜ ኩራቴ
ከፍ ላርገው ሰንደቅ አርማሽን እንደልጅነቴ/3x/
ምን አላት ምን ሰሩ ማን አላት ለሚሉ ያሆ አገሬ ያሆ
ሊንቁሽ ላሰቡ የቱ ጋር ናት ላሉ ያሆ አገሬ ያሆ
የማዕዘን ድንጋይ አንቺ የታሪክ ሙዳይ ያሆ አገሬ
ቀድመሽ ብትዘገይም ትሆኛለሽ ከላይ ያሆ አገሬ ያሆ
ሀገሬ ሀገሬ ሀገሬ ሀገሬ
ውሃም ሳይጠማን ሰላም ሳይርበን
ችግር ሳይደፍረን ኢትዮጵያ ኑሪልን
ቁጣው የነብር ግርማው ያንበሳ
እሳት ነው ህዝብሽ ሆ ብሎ ሲነሳ
አሀ እሆ አሀ
ልክ እንደግማድ የተሸከመው ማተብ መለያው
ሰንደቅ አላማው ነው
ያሆ በልጃሌው ያሆ በል ምነው
ያሆ በልጃሌው ያላወቀህ ማነው
አሀ እሆ አሀ
ኢትዮጵያ ልብሽ ካባ ውጪ አደባባይ ኩራቴ
ጥላ ክብሬ መስታወቴ ነሽ የልጅነቴ/2x/
ኢትዮጵያ የመንታ እናት እንቅልፍ የሌለሽ እናቴ
የደስታዬ የቁጭቴ ቀን የልጅነቴ/4x/
እንዲህ ነን እያለ ኢትዮጵያዊ ማለት ያሆ ሀገሬ ያሆ
ቀና ብሎ ይሂድ አንገት በደፋበት ያሆ አገሬ ያሆ
ይመርብሽ ሁሌ ስምሽ ያስተጋባ ያሆ ሀገሬ ያሆ
ድል በድል ሁኝልኝ ሁሌም ውሮ ወሸባ ያሆ ሀገሬ ያሆ
ሀገሬ ሀገሬ ሀገሬ ሀገሬ
ውሃም ሳይጠማን ሰላም ሳይርበን
ችግር ሳይደፍረን ኢትዮጵ ኑሪልን
ቁጣው የነብር ግርማው ያንበሳ
እሳት ነው ህዝብሽ ሆ ብሎ ሲነሳ
አሀ እሆ አሀ
ልክ እንደግማድ የተሸከመው ማተብ መለያው
ሰንደቅ አላማው ነው
ያሆ በልጃሌው ያሆ በል ምነው
ያሆ በልጃሌው ያላወቀህ ማነው
አሀ እሆ አሀ

Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#አብነት_አጎናፍር #ለኔ_ካለሽ


አንቺን ብሎ ልቤ አልረጋ አለ
ባሳብ ካንቺ ጋር ሄዶ እየዋለ
አስቻለሽ ወይ ያለኔ ኑሮ
ከበደኝ እኔ እንጃ ዘንድሮ
አንቺን ብሎ ልቤ አልረጋ አለ
ባሳብ ካንቺ ጋር ሄዶ እየዋለ አስቻለሽ ወይ ያለኔ ኑሮ
ከበደኝ እኔ እንጃ ዘንድሮ ለኔ ካለሽ መቼም አይቀርም
ውድጅኝ ብዬ ሙጥኝ አልልም
ለኔ ካለሽ መቼም አይቀርም
ውድጅኝ ብዬ ሙጥኝ አልልም አለሁ
ይግባኝ አልጠየኩም
ክፉ ነሽ አላልኩም
ደግም ነሽ አልልም
ብቻ ግን አለሁ እራሴን ባልጥልም
አለሁ እንዳለሁ
አለሁ ይግባኝ አልጠየኩም ክፉ ነሽ አላልኩም
ደግም ነሽ አልልም
ብቻ ግን አለሁ እራሴን ባልጥልም
አለሁ እንዳለሁ ዘንድሮስ ቸገረኝ
እምባዬ አልደርቅ አለኝ
ሆዴም አልቆርጥ አለኝ
ድካሜ አሳዘነኝ
ፍቅር አልቆይም አለኝ
እየወሰወሰኝ ከማጥ ውስጥ ዘፈቀኝ
ዘንድሮስ ቸገረኝ
እምባዬ አልደርቅ አለኝ
ሆዴም አልቆርጥ አለኝ
ድካሜ አሳዘነኝ
ፍቅር አልቆይም አለኝ እየወሰወሰኝ
ከማጥ ውስጥ ዘፈቀኝ በርግጥ አታምኚም አንቺን ማሠቤ
እርቀሽ ስለሆድሽ ደፍተሽኝ እኔን
አልጠላሽም ስላልውደድሽኝ
ካሳብ እንድድን ብቻ ጠይቂኝ
በርግጥ አታምኚም አንቺን ማሠቤ
እርቀሽ ስለሆድሽ ደፍተሽኝ እኔን አልጠላሽም ስላልውደድሽኝ
ካሳብ እንድድን ብቻ ጠይቂኝ ለኔ ካለሽ መቼም አይቀርም
ውድጅኝ ብዬ ሙጥኝ አልልም
ለኔ ካለሽ መቼም አይቀርም
ውድጅኝ ብዬ ሙጥኝ አልልም አለሁ ይግባኝ አልጠየኩም
ክፉ ነሽ አላልኩም
ደግም ነሽ አልልም
ብቻ ግን አለሁ እራሴን ባልጥልም
አለሁ እንዳለሁ
አለሁ ይግባኝ አልጠየኩም ክፉ ነሽ አላልኩም
ደግም ነሽ አልልም
ብቻ ግን አለሁ እራሴን ባልጥልም
አለሁ እንዳለሁ ዘንድሮስ ቸገረኝ
እምባዬ አልደርቅ አለኝ
ሆዴም አልቆርጥ አለኝ
ድካሜ አሳዘነኝ
ፍቅር አልቆይም አለኝ
እየወሰው

Shear to your best friends for more lyrics @ethiopian_music_lyrics
#አብነት_አጎናፍር #ስሚኝ
እስካገኝሽ ችዬ እንዲገባሽ ብዬ
አምነሽ ብትመጭ እያልኩኝ
ናፍቄ እየቻልኩኝ
ስትሸሽኝ አጥፍተሸ ተከትዬ ባቅፍሽ
ምን ሊጠቅምሽ/2x
ለማለፍ ያቺን ቀን ሊደገም ቀን በቀን
ምን ሊጠቅመን /2X
ባዝንም ሌላው ቢያስከፋኝ
ማለፍ መተው መች ጠፋኝ
አንቺን አላልፍም የኔን ካላየሽ
ከፍቶሽ መጥቼ ከፍቶኝ ካልመጣሽ
የፍቅር ቅሬታዬን
የመውደድ ዝምታዬን
ደልቶኝ መቼ አቀፍኩት
እስክትመጭልኝ ነው ያፈንኩት
ዝም አልልም ደፍሬ
ባስከፋሽ እኔ አንቺን አፍሬ
የቃል ነውይ ኪሳራ
ለልብ ወዳጅ ላይሰራ
ናፍቆትሽ ቢያመኝም
ሸንግየሽ በርሽን አልከፍትም
ልቤ ይጽዳልሽ ዛሬ
ቢስምሽ ትርፍ ነው ከንፈሬ
ስሚኝ
ስሚኝ
ስሚኝ
አንዴ ስሚው ይንገርሽ
ያውቃል እውነቱን ልብሽ
የኔም ልብ ያውቃል ያንቺ የለውን
ካልሰማናቸው እንዳይለያዩን
ስሚኝ
ስሚኝ
ስሚኝ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics