Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
Channel created
Channel photo updated
# ኢዮብ_መኳንን # ካሁን_በጛላ_ሌላ
ወኪል ነሽ ከላይ
ደግነቱን እንዳይ
ከኔ በላይ ነው ገባኝ
ለኔ ያወቀልኝ
ፍፁም ሰላም ነው
ከኔ ጋር ሳወዳድረው
የሱ ምርጫ ነሽ
ለኔ ወዶ የሸለመሽ
መች አገኝሽ ነበር
ምርጫዬን ቢሰጠኝ
ነበር ልታመልጪኝ
ለኔ ከኔ በላይ ያሰበው ወዳጄ
አደረሰኝ ደጄ
ካሁን በጛላ ሌላ
ካሁን በጛላ ሌላ
ባይኔም አላይ ሌላ
ሌላ ሌላ ሌላ...
ካሁን በጛላ ሌላ
ቢባል ካንቺ ጛላ
ባይኔም አላይ ሌላ
ሌላ ሌላ ሌላ...
ካሁን በጛላ ሌላ
ካሁን በጛላ ሌላ
ባይኔም አላይ ሌላ
ሌላ ሌላ ሌላ...
ካሁን በጛላ ሌላ
ቢባል ካንቺ ጛላ
ባይኔም አላይ ሌላ
ሌላ ሌላ ሌላ...
ወኪል ነሽ ከላይ
ደግነቱን እንዳይ
ከኔ በላይ ነው ገባኝ
ለኔ ያወቀልኝ
ፍፁም ሰላም ነው
ከኔ ጋር ሳወዳድረው
የሱ ምርጫ ነሽ
ለኔ ወዶ የሸለመሽ
ዓይኔ ለካስ በብርሀን
አያይም ነበረ ከፊት ሲሰወር
እንቁላሉን እንጂ
ሌላውን መች አየው
እባብ እንደጣለው
ካሁን በጛላ ሌላ
ካሁን በጛላ ሌላ
ባይኔም አላይ ሌላ
ሌላ ሌላ ሌላ...
ካሁን በጛላ ሌላ
ቢባል ካንቺ ጛላ
ባይኔም አላይ ሌላ
ሌላ ሌላ ሌላ...
ካሁን በጛላ ሌላ
ካሁን በጛላ ሌላ
ባይኔም አላይ ሌላ
ሌላ ሌላ ሌላ...
ካሁን በጛላ ሌላ
ቢባል ካንቺ ጛላ
ባይኔም አላይ ሌላ
ሌላ ሌላ ሌላ...
ኬኔዲ_መንገሻ #ተገኘሽ_አሉ


ተገኘሽ አሉ ድብቅ ቦታ
ተደርጎም እንደሁ ዘለቅናታ
ታየሽ ይላሉ ስውር ቦታ
ሆኖም ከሆነ በይ ኖርናታ
መንገድ ሆንኩ እየተባለ
እንዲህ ሆንኩ እየተባለ
ለካስ ነገር አለ
በጣፋጩ ቃልሽ እኔ እንዲህ ስመካ
አንቺስ ማር ማር ያልሽው ላመል ነበር ለካ
መቼም ይህ ጎዳና ወለም ካደረገ
ካለወደቁ አይለቅም ዘመም ካላረገ
ልቤን እንደ ጧፍ እያቀለጥሽው
በፍቅር ሰደድ ጉድ አደረግሽው
ልልልል ልልልልል ልልል ከሸሸሽኝ
የኔው ማበድ ነው ጉድ ያረገኝ
ካፈቀርሽ ሰው በሰው ላይ
ከወደድሽ ሰው በሰው ላይ
በላው በላ ፍቅሬን ዋይ ዋይ
ፍቅሬን ዋይ ዋይ
ቀረሁ እኔ አላለልኝ
ካንቺ ሌላ ሰው የሌለኝ
የሳብ ፈረስ ያቀጠለኝ
ምን ቻለልኝ
ጂጂ_ሽባባው # ሳላየው

ሳላየው አላድርም አይነጋም ለሊቱ/2X
ጀንበሯን ቀድሜ እደርሳለው ቤቱ/2X
ዶፍ ዝናብ ሳይፈራ ወንዙ ሙላት ሳያግደው
ሀምሌ ነሃሴ ቆፋ ብርዱ ሳይመልሰው
ፍልቅልቅ ብራቁን ወንዙን ሽብሩን ሳይፈራ
ልቤ ገሰገሰ ዛሬ ሊኖር ካንተ ጋራ
በካህን ሸብሻቦ በሊቅ በዲያቆኖች ዜማ
ቢወደስ ቢመለክ በታላቅ ጉባኤ ቢሰማ
ሺ ቃላት የሚያንሰው የወንድ የቆንጆዎች አውራ
የታተምከው ፈሳሽ በልቤ ገነት አዝመራ
ጎምላልዬ…..ግርማው እንደአንበሳ…..ጎምላልዬ
ጎምላልዬ…..ውበቱ እንደ ጸሀይ…..ጎምላልዬ
ጎምላልዬ…..ያይኖቼ ማረፊያ…….ጎምላልዬ
ጎምላልዬ…..የልቤ ሲሳይ
ሳላየው አላድርም አይነጋም ለሊቱ 2X
ጀንበሯን ቀድሜ እደርሳለው ቤቱ
2X
በራሴ ጠል ሰፍሯል ውዴ በሹሩባዬ አንዛብ
ደረስኩ ንጋት ሳይለይ ክፈትልኝ የኔ ሰበብ
ጸሀይ ብልጭ አለ ጠራ ፈካ ገመገሙ
ክፈት አይንህን ልይ ውዴ ያገር ልጄ ድማሙ
ጠል እና አንዛቦ ብርዱ እሳትና ዋዕይ
ዝናብና ዶፉ ጎርፉ ውርጩና አመዳይ
ከንቱ ላያግደኝ አትፍራ አትሸበር ልቤ
ሳላየው አላድርም ያንን ናርዶስ ያንን ከርቤ
ጎምላልዬ…..ግርማው እንደአንበሳ…..ጎምላልዬ
ጎምላልዬ…..ውበቱ እንደ ጸሀይ…..ጎምላልዬ
ጎምላልዬ…..ያይኖቼ ማረፊያ…….ጎምላልዬ
ጎምላልዬ…..የልቤ ሲሳይ
ሳላየው አላድርም አይነጋም ለሊቱ 2X
ጀንበሯን ቀድሜ እደርሳለው ቤቱ
2X
ጎምላልዬ…..ግርማው እንደአንበሳ…..ጎምላልዬ
ጎምላልዬ…..ውበቱ እንደ ጸሀይ…..ጎምላልዬ
ጎምላልዬ…..ያይኖቼ ማረፊያ…….ጎምላልዬ
ጎምላልዬ…..የልቤ ሲሳይ
ሳላየው አላድርም አይነጋም ለሊቱ/2X
ጀንበሯን ቀድሜ እደርሳለው ቤቱ

Shear to your best friend @ethiopian_music_lyrics
# አበባ_ደሳለኝ # ቁርጠኛ_ከሆንክ

የፍቅሬ ደሴት ነህ በልቤ ዋሻ የከተምክ
አልጣህ እኔ አልችልም ስስቴን አንተም ታውቃለህ
ሊለየን የማይችል ገፃችን ሆኖ አንድላይ
ግርማ ሞገሴ ነህ አልደምቅም ያላንተ ስታይ
ቁርጠኛ ከሆንክ በል ደህና ሰንብት ብርታት ሰንቅ
የልቤ ንጉስ እንዳትረታ ፍቅርን ታጠቅ
አሳልፈናል የማይረሱ የደስታ ጊዜ
አዲስ ሆነብኝ ወዶ መለየት ክፉ ትካዜ
አሳልፈናል የማይረሱ የደስታ ጊዜ
አዲስ ሆነብኝ ወዶ መለየት ክፉ ትካዜ
ማን አለኝ ያላንተ ብቻዬን ነኝ እኮ
መለየት ግድ ሆነ ተራራቅን እኮ
ጋሻዬ እኮነህ የምመካብህ በሴትነቴ
አንተን ስላጣው ከማን ልጫወት ጭር አለ ቤቴ
ውለህ ስትገባ ከበሮ አውጥቼ የምቀበልህ
ልማዴ ቀርቶ ቆሜ ሳነባ አይኔ ሟሟልህ
ጋሻዬ እኮነህ የምመካብህ በሴትነቴ
አንተን ስላጣው ከማን ልጫወት ጭር አለ ቤቴ
ማን አለኝ ያላንተ ብቻዬን ነኝ እኮ
ሳልችል ተለያየን ግድ ሆነብን እኮ
የፍቅሬ ደሴት ነህ በልቤ ዋሻ የከተምክ
አልጣህ እኔ አልችልም ስስቴን አንተም
ታውቃለህ ሊለየን የማይችል ገፃችን ሆኖ አንድላይ
ግርማ ሞገሴ ነህ አልደምቅም ያላንተ ስታይ
እኔ ነኝ እንጂ እድለቢሷ ለኔ ማልጠቅም
ባሳብ ደንዝዤ ናፍቆት ደርሶብኝ አንተን የማልም
ልውጣ ተራራ አሻቅቤ ልይ ማዶ ማዶውን ያሳየኝ እንደው
ደመናው ስሎ አምላክ
ምስልህን ልውጣ ተራራ አሻቅቤ ልይ ማዶ ማዶውን ያሳየኝ
እንደው ደመናው ስሎ
አምላክ ምስልህን
ማን አለኝ ያላንተ ብቻዬን ነኝ እኮ
ሳልችል ተለያየን ግድ ሆነብን እኮ
ማን አለኝ ያላንተ ብቻዬን ነኝ እኮ
መለየት ግድ ሆነ ተራራቅን እኮ

ለሚወዱት ጓድኛዎ ለፍቅረኛዎ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመድዎ shear በማረግ ቻናላችን እንዲቀላቀሉ ይጋብዙ @ethiopian_music_lyrics
#አስቴር አወቀ#እርቄ ሂጃለው


ጊዜው ይርዘም እንጂ
መች እረሳሃለው
በሆነ ባልሆነው
እናፍቅሃለው
አይግረምክና
ዛሬም ወድሃለው
አንጀቴን አስሬ
ይኸው እኖራለው
እርቄ ሄጃለሁ
ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ
አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ
የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን
የአንተ ፍቅር
ተማምነው ተዋደው
አብረው የኖሩት
ሲለዩት ይፋጃል
እንደ እግር እሳት
በልቤ ወድጄ
በአፌ የማቀብጥህ
ትቼ የማልተውህ
እኔው ነኝ ወዳጅህ
አይቻልምና
የአንዳንድ ስው ናፍቆት
መውደድን በወጉ
ፍቅር ያስተማሩት
እርቄ ሄጃለሁ
ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ
አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ
የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን
የአንተ ሚስጥር
የልቤ ምሰሶ
ዘንጉ ተሠበረ
የማይመነጠር
ምሽግ የነበረ
በፅኑ ትዝታ
እራቀው መንገዴ
እስቲ ላሠላስልህ
ደግሞ እንደ ልማዴ
ኢየው ልቤ ጥሎኝ
ተነስቶ ሲሄድ
ባንተ መወስወሱን
አድርጎ ልማድ
Ethiopian music lyrics:
#አስቴር አወቀ#እርቄ ሂጃለው


ጊዜው ይርዘም እንጂ
መች እረሳሃለው
በሆነ ባልሆነው
እናፍቅሃለው
አይግረምክና
ዛሬም ወድሃለው
አንጀቴን አስሬ
ይኸው እኖራለው
እርቄ ሄጃለሁ
ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ
አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ
የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን
የአንተ ፍቅር
ተማምነው ተዋደው
አብረው የኖሩት
ሲለዩት ይፋጃል
እንደ እግር እሳት
በልቤ ወድጄ
በአፌ የማቀብጥህ
ትቼ የማልተውህ
እኔው ነኝ ወዳጅህ
አይቻልምና
የአንዳንድ ስው ናፍቆት
መውደድን በወጉ
ፍቅር ያስተማሩት
እርቄ ሄጃለሁ
ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ
አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ
የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን
የአንተ ሚስጥር
የልቤ ምሰሶ
ዘንጉ ተሠበረ
የማይመነጠር
ምሽግ የነበረ
በፅኑ ትዝታ
እራቀው መንገዴ
እስቲ ላሠላስልህ
ደግሞ እንደ ልማዴ
ኢየው ልቤ ጥሎኝ
ተነስቶ ሲሄድ
ባንተ መወስወሱን
አድርጎ ልማድ

shear to your frinds
@ethiopian_music_lyrics
# ነፃነት_መለሰ # ምነው_ጃል
ምነው ጃል ምነው ጃል
ምነው ጃል ምነው ጃል
ምነው ጃል ተው እንጂ ምነው ጃል
መውደድ መወደድን አይተነው አልፈናል
ምነው ጃል ምነው ጃል
ምነው ጃል ምነው ጃል
ምነው ጃል ተው እንጂ ምነው ጃል
ለጥቂት ቀን እንጂ የኔም ልብ ይቆርጣል
ታመሀል እንዳልል
መልዕክት አልደረሰኝ
ከአገር ወጣህ አልል
አልተሰናበትከኝ
በህይወት መኖርክን ያየሰው ነገረኝ
ለመናፈቅ ብለህ ተው አታሳዝነኝ
የተጫወትንበት ዳዋው ተላበሰ
የተነጋገርነው ውላችን ፈረሰ
ሀዘኔ ሆድ ገብቶ እንባዬ ፈሰሰ
ይህ አይደለም ፍቅር ባንተ የደረሰ
ምነው ጃል ምነው ጃል
ምነው ጃል ምነው ጃል
ምነው ጃል ተው እንጂ ምነው ጃል
መውደድ መወደድን አይተነው አልፈናል
ምነው ጃል ምነው ጃል
ምነው ጃል ምነው ጃል
ምነው ጃል ተው እንጂ ምነው ጃል
ለጥቂት ቀን እንጂ የኔም ልብ ይቆርጣል
እየታየህ መቅረት
ተው እንጂ ምነው ጃል
ፍቅር ከወጠኑ ያለነው መቻቻል
ቻል ቻል እያልከኝ ከሰው አትጣለኝ
ከሆነ በኋላ ማሪኝ እንዳትለኝ
ታወራለህ አሉ ተወደድኩኝ ብለህ
ታማኛለህ አሉ አልወዳትም ብለህ አልቀየምህም እንዳሻህ ተናገር
ባትታደለው ነው ሲያፈቅሩ ለማፍቀር
ምነው ጃል ምነው ጃል
ምነው ጃል ምነው ጃል
ምነው ጃል ተው እንጂ ምነው ጃል
መውደድ መወደድን አይተነው አልፈናል
ምነው ጃል ምነው ጃል
ምነው ጃል ምነው ጃል
ምነው ጃል ተው እንጂ ምነው ጃል
ለጥቂት ቀን እንጂ የኔም ልብ ይቆርጣል


shear to your friends @ethiopian_music_lyrics
# ጎሳዬ_ተስፋዬ # እቴ_በነጠላሽ


የቀረብኝ ነገር ምን አለ እቴ ከቀናሽኝ በኋላ
ታሪኬ የኋሊት ቢቆጠር ዘመኔ ቢቀመር ቢሰላ
እንደፍቅርሽ ታዲያ ምን አለ አንጀትና ልቤን ያራሰኝ
ነጠላው ጥበብሽ አይደል ወይ ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ
እቴ በነጠላሽ በነጠላሽ - እቴ በነጠላሽ
እቴ በነጠላሽ በነጠላሽ - እቴ በነጠላሽ
ተለክፌ በዛ በጥለቱ
አላርፍ አለኝ ልቤ እያነሳሽ
እቴ በምትወጂው በማተብሽ
እቴ ባንገትሽ ክር በማተብሽ
እቴ በምኩራቡ ሰው ባለበት
ብትገጥሚኝ ብገጥምሽ ምን አለበት
ነገር አለኝ ማዶ- (አባይ ነው ቤቷ)
ነገር አለኝ ማዶ - (አባይ ነው ቤቷ)
ያልጨረስኩት ፍቅር ሰዶኛል አንድዶ
አባይ ዳር ነው ቤቷ አባይ ላይ ነው ቤቷ
ለክፋኝ የሄደችው እቴ በጥለቷ
ሆ እናንየ ሆ እናናየ
በይ በትክሻሽ ግጠሚኝና (አባይ ነው ቤቷ)
ጀማው ይፍረደኝ እኔ ያንች ጀግና (አባይ ነው ቤቷ)
የቀረብኝ ነገር ምን እቴ ከቀናሽኝ በኋላ
ታሪኬ የኋሊት ቢቆጠር ዘመኔ ቢቀመር ቢሰላ
እንደፍቅርሽ ታዲያ ምን አለ አንጀትና ልቤን ያራሰኝ
ነጠላው ጥበብሽ አይደል ወይ ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ
መቼም መላ አታጭ መለኛ ነሽ
መች አጣሁሽ እኔ ዘዴኛ ነሽ
እንዴው በማተብሽ አደራሽን
እንዳትደርቢብኝ ብርዱን ፈርተሸ
ከሄድሽማ ወዲያ ምን ሊበጀኝ
ነገር ቁጭት እንጂ ምን ሊተርፈኝ
ምንስ ተቀይሜ ሰው ቢያዝንብሽ
ጀማው በጀም አይል አይፈርድብሽ
ነገር አለኝ ማዶ- (አባይ ነው ቤቷ)
ነገር አለኝ ማዶ - (አባይ ነው ቤቷ)
ያልጨረስኩት ፍቅር ሰዶኛል አንድዶ
አባይ ዳር ነው ቤቷ አባይ ላይ ነው ቤቷ
ለክፋኝ የሄደችው እቴ በጥለቷ
ሆ እናንየ ሆ እናናየ
በይ በትክሻሽ ግጠሚኝና (አባይ ነው ቤቷ)
ጀማው ይፍረደኝ እኔ ያንች ጀግና (አባይ ነው ቤቷ)

Shear to your friends
@ethiopian_music_lyrics
@አስቴር አወቀ

ልቤን ሲጎትተው
ቼ እያለ ናፍቆት
የኔ ማንጎራጎር
ይመስላል የቅንጦት
ፍቅር ቢሆንብኝ
ነው እንጂ መድከሜ
ለዚህች ድረስ ነው ወይ
ንገረኝ ህመሜ
ፍቅር ተሰናብቶ
አልቆለት ወረቱ
ምነው ያንተ መውደድ
ከኔ ቤት መቅረቱ
ፈረስ በቅሎ ይዤ
ወዴት ልፈልገው
እባክህ አምላኬ
መልሰው ይሄን ሰው
ሰው
በእውነት የወደደ
ምስጢሩን ያወቀው
ለፍቀር ይሞታል የታደለ ሰው
በእውነት የወደደ
ምስጢሩን ያወቀው
ለፍቀር ይሞታል የታደለ ሰው
ልቤን ሲጎትተው
ቼ እያለ ናፍቆት
የኔ ማንጎራጎር
ይመስላል የቅንጦት
ፍቅር ቢሆንብኝ
ነው እንጂ መድከሜ
ለዚህች ድረስ ነው ወይ
ንገረኝ ህመሜ
ከቤቴ ወጥቼ
ስመለከተው
ለካ እነደኔ ሰው
ፍቅር ፈላጊ ነው
ከጠዋት እስከ ቀን
መሽቶ እስከሚጨልም
እናፍቅሀለሁ እኔ አልተቻለኝም
በእውነት የወደደ
ምስጢሩን ያወቀው
ለፍቀር ይሞታል የታደለ ሰው
በእውነት የወደደ
ምስጢሩን ያወቀው
ለፍቀር ይሞታል የታደለ ሰው
ስው
ለፍቀር ይሞታል የታደለ ሰው
ለፍቀር ይሞታል የታደለ ሰው

Shear to your friends
@ethiopian_music_lyrics
# ራሔል_ጌቱ # አልጓጓም
ይሁን እንጅ ጥሩ መልካም
ላልመሰለኝ እኔ አልጓጓም
ባያድለኝ መውደድ ለእኔ
እኖራለሁ እስከማየው ፍቅርን ብዬ(2x)
ልበ ኩሩ ልበ ቀና
እስከአየው ድረስ ያንን የኔ ጀግና
ልደር እንጅ ሩቅ አልሜ
እስከአገኝ ድረስ ፍቅሬን አለሜ(2x)
አልጓጓም እኔ አልጓጓም
ቀን ሳይሄድ ሳይመሽ አይነጋም (4x)
ልከ መልካም ቁጥብ የዋህ
እስከሚሰጠኝ የእኔን እህል ውሃ
እራሴን ሆኜ እንደ አመሌ እጠብቃለሁ
እስከ አይ እድሌን (2x)
አልጓጓም እኔ አልጓጓም
ቀን ሳይሄድ ሳይመሽ አይነጋም
# አስቴር_አወቀ # ኢትዮጵያ
የፍቅርን ረድኤት አብዝቶ
የሠላምን ፀሃይ አብርቶ
ደስታና ፍቅር
እርቅ ይውረድልን
በኢትዮጵያችን
አንድነት በሠላም
አሽብርቆ
ይምጣልን በእልልታ
ታርቆ ደምቆ
እልልል እልልታ
ፍቅር ይውረድልን
በኢትዮጵያችን
በምስራቅ በምዕራብ
በደቡብ ሠሜን
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
በሁሉም መአዘን
እርቅ ይውረድልን
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ይላታል
ሲጠራ እናቱን
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ሃገር ያለፍቅር
የማይሆነውን
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
እንመኝ መልካሙን
ደስ ደስ ይበለን
ተመስገን እንበለው
ለዚህ ላደረስን
በፍቅር በደስታ
እጅ ለእጅ ተያይዘን
ይቅር እንባባል
ሥለ እናታችን
በአንድነት
በደስታ
እናቴ
ትድመቅ
በይቅር ይቅርታ
ቤታችን
ይሙቅ
አንድ ነሽ እናቴ
የምስራቅ
ጮራይቱ
የሃይማኖት ድህር
የታሪክ
ምድሪቱ
ኢትዮጵይቱ
ኢትዮጵያዬ
ኢትዮጵይቱ
ምድሪቱ
የፍቅርን ረድኤት
አብዝቶ
የሠላምን ፀሃይ
አብርቶ
ደስታና ፍቅር
እርቅ ይሁንልን
በኢትዮጵያችን
አንድነት በሠላም
አሽብርቆ
ይምጣልን በእልልታ
ታርቆ ደምቆ
እልልል እልልታ
ፍቅር ይውረድልን
በኢትዮጵያችን
ሁሉም በየእምነቱ
የሚኖርብሽ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
እምዬ እናታችን
የሁላችን ነሽ
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
አባት ያቆዩንን
አንድነታችንን
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
ለትውልድ እናቆይ
ኢትዮጵያችንን
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ
መፋቀር ትርጉም ነው
የአንድነት ሚስጢር
የማስተዋል ብቃት
የትውልድን ክብር
ደጋ ወይናደጋው
ቆላው መሬታችን
የገደል የምንጩ
ፈውስ ነው ውሃችን
በአንድነት
በደስታ
እናቴ
ትድመቅ
በይቅር ይቅርታ
ቤታችን
ይሙቅ
አንድ ነሽ እናቴ
የምስራቅ
ጮራይቱ
የሃይማኖት ድህር
የታሪክ
ምድሪቱ
ኢትዮጵይቱ
ኢትዮጵያዬ
ኢትዮጵይቱ
ምድሪቱ
ኢትዮጵያዬ
እማማዬ
ኢትዮጵያዬ
እማማዬ
ኢትዮጵያዬ
እማማዬ
ኢትዮጵያዬ
እማማዬ

Sheat to your friends
@ethiopian_music_lyrics
#ጂጂ_ሽባባው#

እማማ_እናት_ኢትዮጵያ
የማንነቴን መለኪያ ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ
የሦስት ሺህ አመት እመቤት አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ
እቴ አንች የኔ ሙሽራ ሀገሬ እስቲ ልጠይቅሽ
ያገቡሻል ይፈቱሻል ያጩሻል አሁንም ድንግል ነሽ
ከክብርሽ በታች ወደቁ ነገስታት በፍቅርሽ ተነድፈው
ደናግላን መነኑልሽ ዓለምን ደስታቸውን ጥለው
እማማ እናት ኢትዮጲያ እማማ አንቺ እናት ዓለም
ዘመን አመጣሽ የዘር በሽታ
መድሀኒት አለው የማታ ማታ
ሀገር በወገን እንዴት ይረታ
ፍቅር በነገር እንዴት ይፈታ
ዘር ሳይለያየን ወይ ሃይማኖት
ከጥንት በፍቅር የኖርንባት
እናት ኢትዮጵያ ውዴ ውዲቷ
በጎጆ አያልቅም ሙሽርንቷ
እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት አለም
የማንነቴን መለኪያ መመኪያዬ ክብሬ
የሦስት ሺህ አመት እመቤት አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ
እቴ ማነው የሞሸረሽ
አስጊጦ እንዲህ ያሳመረሽ
ያገቡሻል ይፈቱሻል ሀገሬ አሁንም ድንግል ነሽ
ከክብርሽ በታች ወደቁ ነገስታት በፍቅርሽ ተነድፈው
ደናግላን መነኑልሽ ዓለምን ደስታቸውን ትተው
እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት አለም
ሀገር በውድቀት ወጥመድ ተይዛ
የዘመን ስቃይ ጭንቅ እንደዋዛ
እናት እራቆት እንዴት ልይሽ
ክብርሽ የታለ አንድነትሽ
አርበኛ አርበኛ አርበኛ ላይ
ልውጣ መቅደላ ልበል ዋይ ዋይ
ምነው ቢነሳ መይሳው ካሳ
አልወድም ጎበዝ ጀግና ሲረሳ
እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት ዓለም

Shear to your friends
@ethiopian_music_lyrics
#ኩኩ_ሰብስቤ# እና #ቴዲ_አፍሮ# እዮሃ_አበባዬ#


የበረሃው ሀገር ስደተኛ
ሀገሬ ካልገባሁ እኔ አልተኛ
ሀገሬ ሳልገባ እኔ አልተኛ
እፎይ ባለ ልቤ የኔ ነፍስ
ሀገሬ ስገባ ስመለስ /2x/
ያሳደገኝ መሶብ የቤቴ ገበታ
እህል ማቋረሱ የቸገረው ለታ
ይህንን ለማየት ባይፈቅድልኝ ክብሬ
ስደትን መርጬ ወጣሁኝ ካገሬ
ደፋ ቀና ብዬ ሀሳቤን ላልሞላው
የበረሃው ውሎ ሰውነቴን በላው
ክረምቱ ወቶ በጋው ሲገባ
ይናፍቀኛል አዲስ አበባ
አደይ ሲፈካ እንደዘመን አጥቢያ በእንቁጣጣሹ ባገርሽ ኢትዮጵያ
እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባ
ጓዜን ጠቅልዬ መች ሀገሬ ልግባ
አበባዬ እዮሃ አበባዬ በመስከረም -----
ጃኖ አሰርቼ እንደ አደይ ፈክቼ
ታየኝ ማታ የእንቁጣጣሽ ለታ
አየሁ በህልቤ አገሬ ላይ ሁኜ
ከህልሜ ስነቃ ከህልሜ ስነቃ
እዛው ነኝ ለካ እዛው ነኝ ለካ
እዛው ነኝ ለካ እዛው ነኝ ለካ
የበረሃው ሀሀር ስደተኛ
ሀገሬ ካልገባሁ እኔ አልተኛ
ሀገሬ ሳልገባ እኔ አልተኛ
እፎይ ባለ ልቤ የኔ ነፍስ
ሀገሬ ስገባ ስመለስ /2/
በደሃው መንደሬ ተኩዬ ሳልዳር
በሰው በረሃ ላይ ሆኗል የኔስ አዳር
ወንድም እህቶቼን ላስተምር ልረዳ ቤተሰቤን ላግዝ ስደክም ለባዳ
አምላኬን ለመንኩት ----
እድሌ እንዲባረክ በኢትዮጵያ ሀገሬ
ባየሽ ሀገሬ አንቺ እናት አለም
ያለ ሀገር ኑሮ ህይወት አይደለም
የሚቆምልኝ የለኝ ጠበቃ
የሰው መሆኔ ምነው ቢያበቃ
እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባ
ጓዜን ጠቅልዬ መች ሀገሬ ልግባ
አበባዬ እዮሃ አበባዬ በመስከረም -----
ጃኖ አሰርቼ እንደ አደይ ፈክቼ
ታየኝ ማታ የእንቁጣጣሽ ለታ
አየሁ በህልቤ አገሬ ላይ ቆሜ
ከህልሜ ስነቃ ከህልሜ ስነቃ
እዛው ነኝ ለካ እዛው ነኝ ለካ
እዛው ነኝ ለካ እዛው ነኝ ለካ
እዛው ነኝ እዛው ነኝ እዛው ነኝ
እዛው ነኝ እዛው ነኝ እዛው ነኝ
መልካም በዓል

Shear to your friends
@ethiopian_music_lyrics
#ሃመልማል_አባተ# ወድሃለሁ


መች ጠላሁህ ወድሃለሁ
እዉነት እዉነት እልሃለሁ
እንደኔ ሚወድህ ባለም ላይ
ሰው አለ ወይ(2x)
ፍቅር በቃ ተከተተ
ብየ ልቤን ሰጠዉ ላንተ
በመዉደድህ ገዝተኽኛል
ካንተ ወዲያ ምን ያምረኛል
እንደምወድህ ልብህ ያዉቀዋል
እንደበትህ ግን ይደብቀዋል
አታቃልብኝ የፍቅሬን ዋጋ
ሃሳቤ አንተ ነህ ሲመሽ ሲነጋ
አትወጅኝም አትበለኝ
ካንተ ወዲያ ማን አለኝ
በሙሉ ልብ እመነኝ
ዛሬም ነገም ያንተዉ ነኝ(2x)
እኔ ዛሬም እወድሃለሁ
ነገም እወድሃለሁ
መች እጠላሃለሁ(2)
ከቤተሰብ ተነጥየ
ስለፍቅር ሁሉን ጥየ
ያንተ ልሆን ወስኛለሁ
ሌላ ለምን እመኛለሁ
ሁሉ ነገርህ ተመችቶኛል
ምን ጎደለብኝ ሁሉ ሞልቶኛል
አቋሜ ግልጽ ነዉ አይወላዉልም
እኔ ካላንተ መኖር አልችልም
አትወጅኝም አትበለኝ
ካንተ ወዲያ ማን አለኝ
በሙሉ ልብ እመነኝ
ዛሬም ነገም ያንተዉ ነኝ(2)
እኔ ዛሬም እወድሃለሁ
ነገም እወድሃለሁ
መች እጠላሃለሁ
እወድሃለሁ እወድሃለሁ(2)

Shear to your friends
@ethiopian_music_lyrics
🌼🌼🌼 መጪው ዘመን 🌼🌼🌼

መልካም መልካሙን የምናስብበት በጎ በጎውን የምናይበት ቸር ቸሩን የምንሰማበት የተባረከ የፍቅር አመት ያድርግልን!! 🤲🤲

🌼🌼🌼ይህ 2012 ዓመተ ምህረት ነው.. 🌼🌼🌼
ምህረቱን የታደልን እኛ ምህረት እናደርጋለን .. ምህረት እንጠይቃለን... 🤲🤲

ሆን ብለን አስቀይምን እንደሆን
ልብ ሳንል አስቀይምን እንደሆን
በቸልተኝነት አስቀይምን እንደሆን
ሳይገባን ቀርቶ አስቀይምን እንደሆን...

አመቱ የምህረት ነውና ይቅርታችሁን አድሉን!
🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼 መጪው ዘመን 🌼🌼🌼
🌼 መልካም አስብን የምናሳካበት🌼
🌼 መልካም ተመኝተን የሚሆንበት 🌼
🌼 መልካም አልመን የምንደርስበት 🌼
🌼ከእኔነት ወጥተን እኛ ማለትን የምንለምደበት... 🌼

ከኢትዮጵያ በላይ የምናስብላት ሀገር የለችንም እና ኢትዮጵያችንን ከፍ ከፍ የምናደርግበት የስኬት ዓመት ይሁንልን!
💚💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️❤️
ይህንን የምንለው በምክንያት ነው ምክንያቱም 👇
#ኢትዮጵያ_ብዙ_መልካምነት_ይገባታል!

መልካም አዲስ ዓመት!
🌼🌼🌼💚💛❤️🌼🌼🌼
@ethiopian_music_lyrics