Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ህብስት_ጥሩነህ #ወግ_ነው
ውረጅ አለኝ ደጅህ እንደገና
ቁርጤን ሳላውቅ ውሎዬም አይቀና
አልጠቀመኝ አሻግሮ ማየቴ
ዛሬስ ልድፈር ይውጣ ካንደበቴ
ወጥቼ እመጣለሁ
ይሉኝታን አልፈራ
ያረፈደ ፍቅሬን አዬ
ተቀበል አደራ (2x)
ዘገየሁ መሠለኝ እኔ
ካንተው ይምጣ ብዬ (2X)
ከጄው ላይ ዘገኑህ አቤት
ይፍረደኝ አንድዬ (2)
በልቤ ሳጭህ ውዬ
ልጠየቅ ወግ ነው ብዬ
ሳልዘጋጅ ማለዳ
ተዘረፍኩኝ ከጓዳ
ወዲህ ነህ ብየ ስመካ
አርፍጄ ልብ አታይም ለካ
ፍቅርህን ይዤ በአንጀቴ
አስቀደመኝ አንደበቴ
ሠማንያም የለንም ዶሴም የለኝ ከጄ
በምን ልሟገተው ወዴት ዳኛ ሔጄ
ተጠያቂ የለበትውል የለው ከልቤ
ለፍርድ የማይመች ያጨሁት ባሳቤ
ደረሰልኝ ብዬ ስጠብቅ ቀኔን
ጃኖዬን ለበሱት ቀረሁ እርቃኔን
ይበለኝ ያጠፋሁ ራሴ
ጠላቴ የገዛ ምላሴ
አጥቼው አቤት ከምልበት
ምናለ ጥንቱን ብደፍርበት
ይበለኝ ያጠፋሁ ራሴ
ጠላቴ የገዛ ምላሴ
አጥቼው አቤት ከምልበት
ምናለ ጥንቱን ብደፍርበት
ይበለኝ…ይበለኝ…ይበለኝ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics