Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ማዲንጎ_አፈወርቅ# ሞኙ_ልቤ

ካምናው ካልተማርኩኝ ተመልሼ
እኔም ዛሬም ከደገመኝ
እርምን አላቅ ብዬ እንደገና
አዬ ሰው ማመን ካመመኝ
አሀ ሞኙ ልቤ አሀ ያልተደለ
አሀ ምን ሊፈይድ ከታለለ
የካብኩት ተናደ ባለማወቅ ስገነባው ፈርሶ
ባፀዳው ቆሸሸ እንደገና የፀዳው ደፍርሶ
ወርቅ አይደለ ነገር አይጣራ በእሳት አልፈትሸው
የቸገረ ነገር ግራ ገባኝ በምን ይለያል ሰው
ቀድሞ አለመጠንቀቅ ጥንቱን አለመፍራት
ሀይለኛ ዱላ ነው ያረፈብኝ
ማገገሜን እንጃ ምን ተሻለኝ
እንደማንገናኝ ልቤ እያወቀው
አፍቅሮ መለየት መንፈሴን ጨነቀው
አንቺም ላታገኚኝ እኔም ያንቺ ላልሆን
ያለመረሳትሽ ምስጢሩ ምን ይሆን
ካምናው ካልተማርኩኝ ተመልሼ እኔም ዛሬም ከደገመኝ
እርምን አላቅ ብዬ እንደገና አዬ ሰው ማመን ካመመኝ
አሀ ሞኙ ልቤ አሀ ያልታደለ
አሀ ምን ሊፈይድ አሀ ከታለለ
መቁረጥ ከተሳነኝ ምን ይደረግ አውቆ እንዳላወቀ
ይበለው ምናለ ልቤንማ ዳግም ከወደቀ
ቁስሌም ላይጠገን የበፊቱ ጠባሳዉ ላይጠፋ
ከተመለስክበት ሞኙ ልቤ በል እንግዲህ ልፋ
በትካዜ ብሩሽ በሀሳብ ሸራ ላይ
ስስል ከረምኩና ሳሳምርሽ
ህልም እልም ሆንሽና ዛሬም የለሽ
እንደማንገናኝ ልቤ እያወቀው
አፍቅሮ መለየት መንፈሴን ጨነቀው
አንቺም ላታገኚኝ እኔም ያንቺ ላልሆን
ያለመረሣትሽ ምስጢሩ ምን ይሆን
አሀ ሞኙ ልቤ አሀ ያልታደለ
አሀ ምን ሊፈይድ አሀ ከታለለ....

Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ማዲንጎ_አፈወርቅ #
አባይ_ወይስ_ቬጋስ

ፍጥረትህ ዥንጉርጉር ውሀና በረሀ
ሁሉም በያለበት የውበት አማህ
አንዱ በተፈጥሮ አንዱ በሰው ጥበብ
አይን የማያስነቅል ታይቶ ማይጠገብ
ወይ ስጋ ሳይሉ መፍረድ ነው እንደ ራስ
እውነት የሰው ሀገር አባይ ወይስ ቬጋስ
ደመና ከጸሀይ ለምለምና ደማቅ
ትንግርት ህብረ ቀለም ያ'ባይ ሰምና ወርቅ
በነዲድ በረሀ ትንፋሽ በሚያሳጣ
የህንጻ ጫካ አይቶ ቬጋስ ተንቆጥቁጣ
ህይወት የትም አለ በህንጻና በዳስ
ግን የሰው መኖርያው አባይ ወይስ ቬጋስ
ፍጥረትህ ዥንጉርጉር ውሀና በረሀ
ሁሉም በያለበት የውበት አማህ
አንዱ በተፈጥሮ አንዱ በሰው ጥበብ
አይን የማያስነቅል ታይቶ ማይጠገብ
ወይ ስጋ ሳይሉ መፍረድ ነው እንደ ራስ
እውነት የሰው ሀገር አባይ ወይስ ቬጋስ
ፈጣሪን አስቦ እንደ እምነት ማህደር
አባይ ይጨርሳል ፍቅርን በሚስጥር
ምጡቅና ስልጡን ቬጋስ ሴቱ ወንዱ
ሀጥያቱም ግልጽ ነው ላ'ብዬ መንገዱ
ምን ግዜ አለው ቬጋስ የምራቅ መዋጫ
ሁል ግዜ ባተሌ ሰው ከሰው እሩጫ
እንደ ራስ ነው መፍረድ ለነፍስም ለስጋ
አባይ ወይስ ቬጋስ ለሰው ልጆች ፀጋ
የሰው ማድሀኒቱ የሰው ልጅ ነውና
አባይ ወይስ ቬጋስ ላ'ዳም ዘር ፈተና

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics