Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ጥላሁን_ገሠሠ #ፍቅር_ከኛ_እንዳይለየን
ፍቅር ከኛ እንዳይለየን
እንዲቃናልን ስራችን
መጨቃጨቅ ይወገድና
ሰላም ይሁን ለሁላችን /2X
ኑሮ ለሰው ልጆች
በእውነት ቀላል ስላልሆነች ዋዛ
በሆነው ባልሆነው ይቅር
ጭቅጭቃችን አይብዛ
ንዝንዝ ንትርክ ካለ
በኑሮአችን መሀከል
ወዳቻችንም ይቀራል
ሀብትም ቢሆን ይርቃል
ገንዘብ ፍቅር ከሌለው
የማይጠቅም ከንቱ ነው
ለጊዜው ያስደስት እንጂ
ሲረግፍ እንደ ጤዛ ነው
በየተሰማራበት መልኩ
የሰው ልጅ እንደሙያው
ነጋዴውም ወደ ንግዱ
ገበሬውም ወደ እርሻው
ተሰማርቶ ውሎ
ተደስቶ የሚኖረው
ከመተዛዘብ በስተቀር
መጨቃጨቅ ላይኖረው
ሰላም እና መተዛዘን
ከጠፉ ግን ከኛ ዘንድ
ህይወትም መሪር ይሆናል
ኑሮም እኮ አይወደድ
ፍቅር ከኛ እንዳይለየን
እንዲቃናልን ስራችን
መጨቃጨቅ ይወገድና
ሰላም ይሁን ለሁላችን /2X

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics