Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
83.4K subscribers
2.38K photos
92 videos
2 files
300 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀዳማዊ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ዓለም አቀፉን የሰራተኞች ቀን አከበረ። በክብረ በዓሉ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፣ የአየር መንገዱ አመራር አባላት፣ የሰራተኛ ማህበሩ አመራሮች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው የ #MROAFRICA2024 ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ 1971 እስከ 1975 ዓ.ም የመሩት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኮሎኔል ስምረት መድሀኔ በ”አፍሪካ አቪዬሽን ሰርቪስስ” የሕይወት ዘመን ተሸላሚ በመሆን እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
እንኳን ደስ አለዎት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
እንኳን ለ83ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ ቀን አደረሳችሁ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ማሕበራዊ ሀላፊነቱን በተለያዩ ግዜያት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን የሚወጣው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በ 2015 ዓ. ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ባስገነባው የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል።

በማዕድ ማጋራት ፕሮግራሙ ላይ አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራር አባላትና ሰራተኞች ፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወዳሰቡት መዳረሻዎ በምቹ አገልግሎት እና በኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ይብረሩ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአይነቱ የመጀመሪያ በሆነ የሰርግ ዝግጅት የሶስት ሰራተኞቹን የጋብቻ ስነ ስርዓት በድምቀት ያከበረ ሲሆን በስካይላይት ሆቴል የተደረገውን ደማቅ የሽኝት ፕሮግራም ተከትሎ ጥንዶቹ አየር መንገዱ ባዘጋጀው የሶስት ምሽት የጫጉላ ሽርሽር የጉዞ ጥቅል ወደ ዛንዚባር ተጉዘዋል። የሙሽሮች የዛንዚባር ቆይታ እንዳያመልጥዎ ይከታተሉን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኢትዮጵያንሆሊደይስ #ስካይላይትሆቴል #ዛንዚባር
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባዘጋጀው ልዩ ቅናሽ ተጠቅመው በመጪው የፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ በመታደም ልዩ ግዜ ያሳልፉ። ትኬትዎን እስከ ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ይግዙ ከ ሰኔ 24 ቀን እስከ ሐምሌ 12 ፣2016 ዓ.ም ይጓዙ። ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጉዘው ሊያዩት የሚሹት መዳረሻ የት ነው?
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠንካራ የስራ ባሕልን ከማዳበር ጎን ለጎን ቤተሰባዊነትን የተላበሰ የስራ አካባቢን ለመፍጠር ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል። አየር መንገዱ ባዘጋጀው የሶስት ምሽት የጫጉላ ሽርሽር የጉዞ ጥቅል ወደ ዛንዚባር የተጓዙት ሙሽሮች የስራ ባልደረቦቻችን ተጨማሪ ምስሎች እነሆ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኢትዮጵያንሆሊደይስ #ስካይላይትሆቴል #ዛንዚባር
በስካይ ላይት ሆቴል የተጀመረው የሰራተኞቻችን ልዩ የሰርግ ስነ-ስረአት በውቧ ዛንዚባር በሀገሬው ባህል ደማቅ አቀባበል ሞቅ ብሎ ቀጥሏል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኢትዮጵያንሆሊደይስ #የጫጉላሽርሽርጥቅል #የዛንዚባርበረራ #ስካይላይትሆቴል #ዛንዚባር
ቀጣይ የጉዞ መዳረሻዎን ይምረጡ- ከእኛ ጋር በቅንጦት ይጓዙ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ አየር መንገዶች ማህበር (AFRAA) ጋር በጥምረት ያዘጋጀው 12ኛው የአፍሪካ አየር መንገዶች ማህበር ጉባዔ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል በድምቀት በመካሄድ ላይ ይገኛል። ይህ የሶስት ቀናት ጉባዔ 'የአፍሪካን አቪዬሽን ከማገናኘት ባሻገር' በሚል መሪ ቃል የኢንዱስትሪውን ቁልፍ ተዋናዮች ያሰባሰበ ነው። #12ኛውየአፍሪካአየርመንገዶችማህበር #የአፍሪካንአቪዬሽንከማገናኘትባሻገር #የኢትዮጵያስካይላይትሆቴል #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቡርኪና ፋሶ ኦጋዱጉ የሚያደርገውን በረራ አሳድጓል። ከግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በረራውን ዕለታዊ በማድረግ ቀልጣፋ የበረራ አማራጭ ፈጥሯል። ይህን መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ትኬትዎን ከሞባይል መተግበሪያችን፣ ከድረገጻችን አልያም በአቅራቢያዎ ካሉ የሽያጭ ቢሮዎቻችን እና የጉዞ ወኪልዎ በመግዛት በምቾት ማራኪዋን ከተማ ለመጎብኘት ይዘጋጁ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከ135 በላይ ወደሆኑት ዓለም-አቀፍ መዳረሻዎቻችን በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ታጅበው ይብረሩ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ቤተሰባዊነትን የተላበሰ መስተንግዶ ያግኙ፤ የኢትዮጵያ ሆሊደይስ በሚያዘጋጅልዎ ልዩ የጉዞ ጥቅሎች ማራኪ መዳረሻዎችን እየጎበኙ የማይረሳ ግዜ ያሳልፉ!
@EthiopianSkylightHotel
@EthiopianHolidays
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኢትዮጵያንሆሊደይስ #ስካይላይትሆቴል