የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዘንድሮውን ዓመታዊ የሠራተኞች ቀን ሳምንቱን ሙሉ በሚዘልቅ ሰፊ መርሀ-ግብር እያከበረ ይገኛል። ሰኞ ዕለት በግሩፕ የሠው ሀብት አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ለመላው ሰራተኛ በይፋዊ ግብዣ የጀመረው ዓመታዊ በዓል፣ ትናንት ማክሰኞ በተደረገ የሰራተኞች ጉብኝት ቀጥሏል። በጉብኝቱም ሰራተኞች የተለያዩ ክፍሎችን እና ስራዎቻቸውን ተመልክተዋል። መርሀ-ግብሩ ዛሬም በተለያዩ ሁነቶች ይቀጥላል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #የሰራተኞችቀን2017
የኢትዮጵያአየር መንገድ ከሚድያዎች ጋር ባለው የላቀ ሞያዊ ግንኙነት እና የላቀ ሞያዊ ጨዋነት አርትስ ቲቪ ለአየር መንገዱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ዋና ሃላፊ ወ/ሮ ሃና አጥናፉ የዕውቅና ሽልማት አበርክቷል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #አርትስቲቪ