የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዘንድሮውን ዓመታዊ የሠራተኞች ቀን ሳምንቱን ሙሉ በሚዘልቅ ሰፊ መርሀ-ግብር እያከበረ ይገኛል። ሰኞ ዕለት በግሩፕ የሠው ሀብት አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ለመላው ሰራተኛ በይፋዊ ግብዣ የጀመረው ዓመታዊ በዓል፣ ትናንት ማክሰኞ በተደረገ የሰራተኞች ጉብኝት ቀጥሏል። በጉብኝቱም ሰራተኞች የተለያዩ ክፍሎችን እና ስራዎቻቸውን ተመልክተዋል። መርሀ-ግብሩ ዛሬም በተለያዩ ሁነቶች ይቀጥላል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #የሰራተኞችቀን2017
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሳምንቱን ሙሉ በሚዘልቅ ሰፊ መርሀ-ግብር እየተከበረ የሚገኘው የሠራተኞች ቀን በትላንትናው ዕለት በተደረገ ከመንግስት ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት በተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የመሰረተ ልማት ጉብኝት ቀጥሏል። ሃላፊዎቹ የአየር መንገዱን ዋና ዋና የስራ ክፍሎች ጎብኝተዋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #የሰራተኞችቀን2017
በተለያዩ ክብረ በዓላት ሳምንቱን ሙሉ የተከበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሰራተኞች ቀን በዛሬው ዕለት 18 ሺ የአየር መንገዱ ሠራተኞች በተጋበዙበት እንዲሁም የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ እንዲሁም የቦርድ አባላት፣ የአየርመንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ እንዲሁም ሌሎች የአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ አመራሮች በታደሙበት ታላቅ ስነ ስርአት ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ በተሠራው የአየር መንገዱ የእግር ኳስ ሜዳ ተከብሮ ውሏል።
በዝግጅቱ ላይ ከአየር መንገዱ የተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ሰራተኞች ከዋና ስራ አስፈፃሚው እና ከየክፍሎቻቸው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እጅ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል። በዛሬው
ዕለት የተከናወነው ክብረ በዓል ለአንድ ሳምንት የቆየው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች ቀን ክብረ በዓል የመዝጊያ ዝግጅት ሲሆን በሰራተኞች ዘንድ ያለውን ቅርርብ የሚያሳድግ ነው። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #የሰራተኞችቀን2017