በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሳምንቱን ሙሉ በሚዘልቅ ሰፊ መርሀ-ግብር እየተከበረ የሚገኘው የሠራተኞች ቀን በትላንትናው ዕለት በተደረገ ከመንግስት ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት በተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የመሰረተ ልማት ጉብኝት ቀጥሏል። ሃላፊዎቹ የአየር መንገዱን ዋና ዋና የስራ ክፍሎች ጎብኝተዋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #የሰራተኞችቀን2017
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የ2025 የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ሽልማትን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ አበርክቷል። ይህ ሽልማት አየር መንገዱ ለአካባቢ ጥበቃ እና ለፅዱ ኢትዮጵያ ላበረከተው አስተዋፅኦ የተበረከተ ሲሆን አየር መንገዱ በዘርፉ እየተጫወተ ላለው ሚና ዕውቅና የሰጠ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓመታዊው የሰራተኞች ቀን ክብረ በዓል አካል የሆነው የመድረክ ውይይት በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ተከናውኗል። በመድረኩም የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ የዓመቱ የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ሰራተኞች እንዲሁም የአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ተገኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ