Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.6K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲሺየልስ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ዋቭል ራማካላዋን፣ ቀዳማዊት እመቤት ክብርት ሊንዳ ራማካላዋን እንዲሁም ልዑካኖቻቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመብረራቸው ክብር ይሰማዋል። ፓን አፍሪካዊው አየር መንገዳችን በተለያዩ የአፍሪካ መሪዎች ተመራጭ አየር መንገድ ሆኖ ቀጥሏል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
የኢትዮጵያ አየር መንገድን እ.ኤ.አ ከ1980 እስከ 1991 ዓ.ም በዋና ስራ አስፈፃሚነት በማገልገል ለአየር መንገዳችን ዘመን ተሻጋሪ ዕድገት የበኩላቸውን የመሪነት አስተዋፅዖ ያበረከቱት ካፒቴን መሐመድ አሕመድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ካፒቴን መሐመድ አሕመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ባገለገሉበት ወቅት አየር መንገዱ ዛሬ ለደረሰበት የስኬት ደረጃ እንዲበቃ መሰረት የጣሉ ውሳኔዎችን በማሳለፍ የማይተካ የመሪነት ሚናቸውን ተጫውተው አልፈዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካፒቴን መሐመድ አሕመድ በህይወት ዘመናቸው ለአየር መንገዱ ባበረከቱት የመሪነት አስተዋፅዖ ምንግዜም ያስታውሳቸዋል።
የካፒቴን መሐመድ አሕመድ ስርዐተ ቀብር ዛሬ ሕዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ፣ የቀድሞ የስራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በኮልፌ ሙስሊም መካነ መቃብር ተፈፅሟል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሳዑዲ፣ መዲና ከተማ ወደ አፍሪካ ሁሉም የአፍሪካ መዳረሻዎቻችን ለሚጓዙ ደንበኞቹ አንድ ተጨማሪ ሻንጣ አዘጋጅቷል:: ይህ ልዩ ሽያጭ እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ስለሚቆይ ፈጥነው ትኬትዎን በመቁረጥ የዚህ ልዩ አጋጣሚ ተጠቃሚ ይሁኑ።

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
https://www.ethiopianairlines.com/en-sa/additional-baggage-allowance-to-from-medina

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለክቡራን መንገደኞቹ ምቹ የበረራ አማራጭ ሰዓት ለማቅረብ በሚያደርገው ያላሰለሰ ጥረት ከሕዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት ሶስት ቀናት ከአዲስ አበባ ሮም ከእኩለ ቀን በኋላ እንዲሁም ከሮም አዲስ አበባ በማለዳ የሚነሳ ተጨማሪ በረራ የሚጀምር መሆኑን ሲያበስር ደስታ ይሰማዋል። ትኬትዎን በድረ ገፃችን www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app በመጠቀም ይቁረጡ የዚህ አዲስ የበረራ ሰአት አማራጭ ተጠቃሚ ይሁኑ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ሮም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደምቢዶሎ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ በማሳደግ ከሕዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከአዲስ አበባ ደምቢዶሎ ዕለታዊ በረራ የሚጀምር መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቹ እያበሰረ ደንበኞች በድረ ገፅ www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app በመጠቀም ትኬታቸውን ቆርጠው በዕለታዊ በረራ አገልግሎቱ እንዲጠቀሙ ይጋብዛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አስደሳች ዜና!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሕዳር24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት ሶስት ቀናት ከአዲስ አበባ ወደ አቴንስ ከእኩለ ቀን በኋላ እንዲሁም ከአቴንስ አዲስ አበባ በማለዳ የሚነሳ ተጨማሪ በረራ የሚጀምር መሆኑን እያሳወቀ ክቡራን ደንበኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረገጽ www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app ትኬታቸውን ገዝተው የዚህ አዲስ የበረራ አማራጭ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይጋብዛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አቴንስ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የበረራ ክፍል ባልደረቦቻችን ወደ አውሮፕላን ከመግባታቸው በፊት የሚያከናውኗቸው ተግባራት እና የሚያሟሏቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምንድናቸው? በዛሬው የኢትዮጵያ መርሐግብር ይህንን ልናስቃኝዎ ወደናል፤ ይከታተሉን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአመታዊው የኡጋንዳ “ኢኩላ ቱሪዝም ሽልማት” የ2024ዓ.ም ምርጥ የቢዝነስ ክፍል ዘላቂ አገልግሎት (Best Sustainable Airline of 2024-Business Class Category) ሽልማትተቀዳጀ። መርሐግብሩ በካምፓላ ሸራተን ሆቴል የተካሄደ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኡጋንዳ ቱሪዝም ኢንደስትሪ ዕድገት ላበረከተው የላቀ አስተዋፅዖ ሽልማቱ ተበርክቶለታል። በዚህ ዓመታዊ ሽልማት ለሀገሪቱ ቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት በጎ አሻራ ያሳረፉ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዕውቅና ይሰጣቸዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
"የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአውሮፕላን ምስለ በረራ (Flight Simulator) ቴክኖሎጂ ዘመኑ የደረሰባቸው ዘመናዊ ምስለ በራራዎች ባለቤት ሲሆን እነዚህ ምስለ በረራዎች በአውሮፕላኑ ላይ ተጨማሪ ስልጠና ሳያስፈልግ ወደ በረራ የመግባት ክህሎትን የሚያስጨብጡ የአቪዬሽኑ ኢንደስትሪ የልሕቀት ማሳያዎች ናቸው።”
ካፒቴን ፍሰሀ ተስፋዬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፍላይት ኦፐሬሽን የስልጠና ክፍል ዳይሬክተር
https://www.youtube.com/watch?v=g3aigMvftMg&t=121s
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ኒውዮርክ ሲያደርገው የነበረውን አራት ሳምንታዊ በረራ በማሳደግ ከህዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ከተማዋ እለታዊ በረራ የሚጀምር መሆኑን እያበሰረ ደንበኞች በድረ ገፅ www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app በመጠቀም ትኬታቸውን ቆርጠው በዕለታዊ በረራ አገልግሎቱ እንዲጠቀሙ ይጋብዛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላይቤሪያ ሞንሮቪያ የመንገደኞች በረራውን ዛሬ ህዳር 21 ቀን 2017 ዳግም ጀምሯል።

በፕሮግራሙ ላይ የላይቤርያ ትራንስፖርት ሚኒስትር ሰርሊፍ ቴይለር፣በኢትዮጵያ የላይቤርያ አምባሳደር ሉዊስ ሻሬን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአፍሪካ አቪዬሽን ኢንደስትሪ የመሪነት ሚና እየተጫወተ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን እርስ በርስ ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር የማገናኘት መርሁን ይበልጥ በማጠናከር በቅርብ ግዜ ወደ ፖርት ሱዳን እንዲሁም ባንግላዴሽ ዳካ በረራ የጀመረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ወደ ላይቤሪያ ዋና ከተማ ሞንሮቪያ ዳግም በረራ ጀምሯል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ