በእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ “Asian Infrastructure Investment Bank” (AIIB) ፕሬዝደንት ጂን ሊኩን የተመራ የልዑክ ቡድን በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅጥር ግቢ ተገኝቶ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዲሁም ከአየር መንገዳችን አመራር አባላት ጋር ፍሬያማ ውይይት አደረገ።
የልዑክ ቡድኑ ከውይይቱ በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አጠቃላይ የስራ እስቅስቃሴ ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን አየር መንገዳችን በአፍሪካ አህጉር በመሪነት የሚጠቀስባቸውንና በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ያስጠበቀባቸውን የስራ ክፍሎችና የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎች ተመልክቷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የልዑክ ቡድኑ ከውይይቱ በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አጠቃላይ የስራ እስቅስቃሴ ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን አየር መንገዳችን በአፍሪካ አህጉር በመሪነት የሚጠቀስባቸውንና በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ያስጠበቀባቸውን የስራ ክፍሎችና የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎች ተመልክቷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላይቤርያ ሞንሮቪያ ዳግም የጀመረው የመንገደኞች በረራ ሞንሮቪያ ሲደርስ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ጆሴፍ ናዩማ ቦካይ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት እጅግ ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደርጎለታል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ እና በላይቤርያ መካከል የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በመጀመር የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ብሎም አፍሪካን እርስ በርስና ከተቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት እየተጫወተ ያለውን የመሪነት ሚና አጠናክሮ ይቀጥላል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ በርካታ መዳረሻዎች የበረራ አገልግሎት በመስጠት የአፍሪካን አቪዬሽን ኢንደስትሪ በማሳደግ ረገድ ላለው ቁርጠኝነት እና ለአሕጉሪቱ አቪዬሽን ልህቀት እያበረከተ ላለው አስተዋፅዖ የዕውቅና ሽልማት ከአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን (AFCAC) ተበረከተለት።
ሽልማቱ የተበረከተው በኮንጎ ሪፐብሊክ ብራዛቪል ከተማ በተካሄደው 35 ኛው የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን ጉባኤ ላይ ሲሆን የአዲስ አበባ ቦሌ አለም ዓቀፍ ኤርፖርትም እ.ኤ.አ. ከ2022 እስከ 2024 ዓ.ም ባስተናገደው ከፍተኛ የመንገደኞች ቁጥር ዕውቅና ተሰጥቶታል።
የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን (AFCAC) በአፍሪካ ሕብረት ስር የሚተዳደርና የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ጉዳዮችን የሚከታተል ልዩ ኤጀንሲ ሲሆን በሶስት አመት አንድ ግዜ ጠቅላላ ጉባኤውን ያደርጋል።