Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.6K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ቅርንጫፍ ቢሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እና የኢትዮጵያን የቱሪዝም መስህቦች ያስተዋወቀ ልዩ መርሐግብር በኪንሻሳ አካሄደ። በመርሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዘመኑ የደረሰባቸውን አዳዲስ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን ለአፍሪካ በማስተዋወቅና አህጉሪቱን ከመላው ዓለም ጋር በማገናኘት ረገድ እያበረከተ ያለው አስተዋፅዎ የተገለፀ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ያሏትን ዕምቅ የቱሪዝም ሀብቶችና ዘርፉን ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በሰፊው ተዋውቀውበታል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ዘመናዊነትንና ዕምቅ ባህላዊ ይዘቶችን አለም አቀፍ ዕውቅና ከተቸራቸው ሙዚየሞች ጋር አጣምራ ወደያዘችው ፍራንክፈርት ከተማ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አስደሳች የበረራ ጉዞ ያድርጉ!
#ፍራንክፈርት #የኢትዮጵያአየርመንገድ
መልካም አለም ዓቀፍ የሕፃናት ቀን ለወደፊቱ አቪዬሽን ቴክኖሎጂ ተረካቢዎች!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አለምዓቀፍየሕፃናትቀን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አስደሳች በረራ እና ማራኪ እይታ ከኢትዮጵያ አየርመንገድ ጋር! በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበርሩ ያነሷቸውን ምስሎች በመልዕክት መቀበያ ሳጥን በኩል ይላኩልን፤ መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ዘመናትን በስኬት ከፍታ የተሻገረ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በግብጽ፣ካይሮ በተካሄደው 56ተኛው የAFRAA (የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር) አጠቃላይ ስብሰባ በዓለም አቀፍ አገልግሎት የዓመቱ ምርጥ አየርመንገድ (Airline of the Year - Global Operations) በመባል ለስምንተኛ ግዜ ሽልማት መቀዳጀቱን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።
ለተጨማሪ ንባብ: https://shorturl.at/5jKtg
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #AFRAA
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አራት ነጥብ አግኝተው፣ የዩኒቨርስቲ ቆይታቸውንም በወርቅ ሜዳልያ አጠናቅቀው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ካለፉት አርባ አመታት በላይ በተለያዩ የሐላፊነት ቦታዎች ላይ አገልግለው በአሁኑ ወቅት አየር መንገዳችንን በግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚነት እየመሩ የሚገኙት አቶ መስፍን ጣሰው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ያደረጉትን ቆይታ እንድትከታተሉ ጋብዘናችሗል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) https://youtu.be/mwtyuNVAsSQ
በደማቅ ፈገግታ ተቀብለን በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን የበረራ ቆይታዎን ምቹ ለማድረግ ዝግጁ ነን!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ላይ የምግብና መጠጥ ዝግጅት ክፍል (Inflight Catering) በቀን ከ100,000 ሺህ በላይ ምግቦችን ያዘጋጃል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ላይ ምግብና መጠጥ ዝግጅት ክፍል ላይ ያተኮረውን ሳምንታዊውን የኢትዮጵያ ፕሮግራም እንዲከታተሉ ጋብዘንዎታል!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእንግሊዝ ለንደን ቅርንጫፍ ቢሮ አየር መንገዳችን ወደ ለንደን ጋትዊክ አየር ማረፊያ በረራ የጀመረበትን አንደኛ አመት በድምቀት አከበረ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእንግሊዝ ለንደን ሂትሮው፣ ለንደን ጋትዊክ እንዲሁም ማንችስተር የመንገደኞች በረራ ያደርጋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የበረራ ቆይታዎን ከመቼውም ጊዜ በላይ አስደሳች ለማድረግ ዝግጅታችንን አጠናቅቀናል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ዘና ብለው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ይብረሩ፣ ምርጥ መስተንግዷችንን ያጣጥሙ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በደማቅ ፈገግታ ተቀብለን በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዷችን የበረራ ቆይታዎን ምቹ ለማድረግ ዝግጁ ነን!
መልካም የስራ ሳምንት ይሁንልዎ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ 25 የአለማችን ግዙፍ አየር መንገዶች ሕብረት የሆነው “ስታር አላያንስ” “የ2024 World Travel Awards ዓ.ም ምርጥ የአየር መንገዶች ህብረት” በመባል ለ5ኛ ተከታታይ ዓመት በፖርቹጋል ማዲዬራ በተካሄደ ልዩ መርሓግብር ተሸለመ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ስታርአላያንስ