Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
83K subscribers
2.33K photos
91 videos
2 files
300 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ከአፍሪካ ኩራት ጋር ከፍ ብለን እንብረር!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በላቀ አገልግሎታችን እየተደሰቱ ከእኛ ጋር በምቾት ይብረሩ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለረመዳን ፆም በሰላም አደረሳችሁ። ረመዳን ከሪም!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከመንገደኞች አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ቅሬታዎች እየተነሱ መሆኑን ተገንዝቧል።
አየር መንገዱ ከክቡራን ደንበኞቹ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች እና አስተያየቶች ከፍተኛ ትኩረት የሚሠጥ በመሆኑ ሂደቱን በጥሞና ሲከታተል ቆይቷል።
በመሆኑም እየተሰሙ ያሉ ቅሬታዎችን መርምሮ መፍትሄ ለመስጠት አየር መንገዱ በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ አገልግሎት ከሚሰጡ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ቅሬታዎችን የማጣራት ስራ እየሠራ መሆኑን ለማሣወቅ እንወዳለን።
ይህንንም ተከትሎ በማጣራቱ ሥራ ላይ በሚገኙ ውጤቶች ላይ በመመርኮዝ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ በፍጥነት እንዲወሠድ ይደረጋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁልጊዜም ጥረቱ ለውድ ደንበኞቹ ቀልጣፋ እና ምቹ አገልግሎት መስጠት ነው። አሁንም የክቡራን ደንበኞቹን ጥቆማ ተቀብሎ አስፈላጊውን ማስተካከያ በማድረግ ይህንኑ ጥረቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ‘የኢትዮጵያ ተቋማት የስኬት ሽልማት’ን ተቀዳጀ። ብሔራዊ አየር መንገዱ ሽልማቱን ከክቡር የኢፊዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እጅ ተቀብሏል። አየር መንገዳችን በአህጉር አቀፍ ደረጃ ላሳየው አመርቂ እድገት በተለይም በኮሮና ወረርሽኝ ጊዜ ላበረከተው ዓለም-አቀፍ አስተዋጽኦ ሽልማቱ ተበርክቶለታል። ሽልማቱን አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተቀብለዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው ሽልማቱ ‘የመላው የአየር መንገዱ ሰራተኛ የትጋት ውጤት' መሆኑን ተናግረዋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን shalom.shewamoltot ናቸው፤ እናመሰግናለን! እርስዎም ከእኛ ጋር ሲበሩ ያነሱትን ምስል በመልዕክት መቀበያ ሳጥን በኩል ይላኩልን መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በረራዎን ምቹ እና አስደሳች ለማድረግ ሁልጊዜም እንተጋለን።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወደ ህልምዎ መዳረሻ በምቾት ልናደርስዎ ተዘጋጅተናል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ! ምቹ እና አስደሳች የበረራ ጊዜ ያሳልፉ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ምቾትዎን ጠብቀን ልናስተናግድዎ ሁሌም ዝግጁ ነን። መልካም ሳምንት ይሁንልዎ! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎትን ያግኙ።


#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን @danielaregay ናቸው፤ እናመሰግናለን! እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ ያነሷቸውን ምስሎች ይላኩልን፤ መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከፎቶ ማህደራችን። በፎቶው ላይ ከሚታዩት የቀድሞ ባልደረቦቻችን ማንን ያስታውሳሉ?

#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በእረፍት ጊዜዎ ከእኛ ጋር ወደየት ለመብረር አቅደዋል?

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ባልተቋረጠ ትጋት እና ስኬት እርስዎን ማገልገላችንን እንቀጥላለን!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ልዩ እና ኢትዮጵያዊ በሆነው መስተንግዷችን ታጅበው ይጓዙ፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአንድነትና የመተሳሰብ ምልክት የሆነውን የታላቁን የሮመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ በስካይላይት ሆቴል የኢፍጣር መርሐ-ግብር አካሔደ። በመርሐ-ግብሩ ሚኒስትሮች፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አመራሮችና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም አምባሳደሮች እና የክብር እንግዶች ታድመዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ