Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
83.3K subscribers
2.37K photos
91 videos
2 files
300 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አዲሱን በአፍሪካ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን እና 55 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መዋዕለ-ንዋይ ያፈሰሰበትን ዘመናዊ የኢኮሜርስ መሰረተ ልማት በደማቅ ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡ የዚህ በልዩ ሁኔታ ለኢኮሜርስ ሸቀጦች እንዲሁም ለፖስታ እና ጥቅል መልእክቶች የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ ወደ ስራ የሚገባው መሰረተ-ልማት የአፍሪካን የኢኮሜርስ ኢንደስትሪ ዕድገት ከማፋጠኑም ባሻገር አዲስ አበባን በአፍሪካ ብሎም በዓለም የድንብር ተሻጋሪ ኢኮሜርስ ማዕከል የሚያደርግ ነው፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያካርጎእናሎጂስቲክስአገልግሎት
የአፍሪካ አቪዬሽን ኢንደስትሪን በዘርፈ ብዙ መስፈርቶች በቀዳሚነት እየመራ ያለው አንጋፋው አየር መንገዳችን ከ135 በላይ አለም አቀፍ የመንገደኞች በረራ መዳረሻዎች ሲኖሩት በቀጣይም ለበለጠ ስኬት ይተጋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ማሳሰቢያ

የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 1 (በተለምዶው የሀገር ውስጥ/Domestic Terminal) የማስፋፊያ እና የማዘመን ስራው ተጠናቅቆለት ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ የሀገር ውስጥ በረራ ለማድረግ ወደ ኤርፖርት የምትመጡ ክቡራን መንገደኞቻችን በቀጥታ ወደ ተርሚናል ቁጥር 1 ብቻ እንድትገቡ በትህትና እናሳውቃለን።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
እንኳን ለ128ኛው የዐድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ስማችንን በደማቅ ቀለም ባስጻፍንበት ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ስራዎን በስኬት እንዲከውኑ፤ ከወዳጅ ዘመድ እንዲገናኙ እናደርጋለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር እንኳን በደህና መጡ! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የአክብሮት ሰላምታችን ከበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል በያላችሁበት ይድረስ። ትኬትዎን በሞባይል መተግበሪያችን ቆርጠው ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ያግኙ።
መልካም ቀን ይሁንልዎ! https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንግዜም ለመንገደኞቹ ምቹ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ብሎም የአቪዬሽን ኢንደስትሪው የደረሰበትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ስራ ላይ ለማዋል ባለው ቁርጠኝነት የቦይንግ አዲስ ምርት የሆኑትን በቅርብ ግዜ እና በሂደት የሚረከባቸውን የ20 ቦይንግ 777-9 አውሮፕላኖችን ለማስገባት የሚያስችለውን ስምምነት ዛሬ ከቦይንግ ጋር ተፈራርሟል። የB777-9 አውሮፕላን የቦዪንግ ስሪት የሆኑትን የB777 እና B787 አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂዎችን ቀምሮ የያዘ የቦዪንግ ኩባንያ የቅርብ ጊዜ ምርት ነው። እንደከዚህ ቀደም ሁሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን አዲስ እና ግዙፍ አውሮፕላን በማዘዝ በአፍሪካ ቀዳሚው ሆኗል። ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የቦዪንግ ኩባንያ ለአስርት-ዓመታት የገነቡትን የንግድ ስምምነት የሚያጠናክር ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በቦትስዋና ሁለተኛ መዳረሻችን ወደሆነችው የማውን ከተማ በሳምንት ሶስት ቀን የመንገደኞች በረራ የሚጀምር መሆኑን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው። ይህን መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው የማውን ከተማን አስደናቂ ውበት ለመጎብኘት ትኬትዎን በመግዛት የመጀመሪያው ይሁኑ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሊከበር እነሆ አንድ ቀን ቀርቶታል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይህን ቀን በሴቶች ብቻ በሚደረግ በረራ ሲያከብረው ቆይቶ የዘንድሮውንም የሴቶች ቀን በተመሳሳይ መልኩ በድምቀት ሊያከብር ዝግጅቱን አጠናቅቋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ዓለምአቀፍየሴቶችቀን
ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል የመንግስት ሀላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደመቀ መልኩ ተከብሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይህን ቀን አስመልክቶ ወደ እንግሊዝ ለንደን በሴቶች ብቻ የሚደረግ በረራ ያደርጋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ዓለምአቀፍየሴቶችቀን
የማይረሳ የበረራ ትዉስታ ከእርስዎ ጋር ለማድረግ ዝግጅታችንን ጨርሰናል። ብሩህ የእረፍት ቀናት ተመኘንልዎ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ