በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ክቡር አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ እና የልዑክ ቡድናቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናው መስሪያ ቤት ተገኝተው ጉብኝት አደረጉ።
ክቡር አምባሳደሩና ልዑካኖቻቸው ከአየር መንገዳችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የአየር መንገዱ ማኔጅመንት አባላት ጋር ፍሬያማ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ስለ አጠቃላይ የአየር መንገዳችን የስራ እንቅስቃሴ እና የዕድገት ጉዞ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
ክቡር አምባሳደር ማሲንጋ ከልዑካኖቻቸው ጋር በመሆን በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ዘመናዊ የሆኑትን የተለያዩ የስራ ክፍሎቻችንን ጎብኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ

ዘመናዊ የመንገደኞች መቆያ ስፍራዎች ባልተሟሉባቸው በቀደሙት ግዜያት መንገደቾች በዚህ መልኩ በ DC-3 ሰፋፊ ክንፎች ስር በመሆን የቀትርን ፀሐይ ያሳልፉ ነበር።
#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አዲሱን በአፍሪካ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን እና 55 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መዋዕለ-ንዋይ ያፈሰሰበትን ዘመናዊ የኢኮሜርስ መሰረተ ልማት በደማቅ ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡ የዚህ በልዩ ሁኔታ ለኢኮሜርስ ሸቀጦች እንዲሁም ለፖስታ እና ጥቅል መልእክቶች የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ ወደ ስራ የሚገባው መሰረተ-ልማት የአፍሪካን የኢኮሜርስ ኢንደስትሪ ዕድገት ከማፋጠኑም ባሻገር አዲስ አበባን በአፍሪካ ብሎም በዓለም የድንብር ተሻጋሪ ኢኮሜርስ ማዕከል የሚያደርግ ነው፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያካርጎእናሎጂስቲክስአገልግሎት
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያካርጎእናሎጂስቲክስአገልግሎት
የአፍሪካ አቪዬሽን ኢንደስትሪን በዘርፈ ብዙ መስፈርቶች በቀዳሚነት እየመራ ያለው አንጋፋው አየር መንገዳችን ከ135 በላይ አለም አቀፍ የመንገደኞች በረራ መዳረሻዎች ሲኖሩት በቀጣይም ለበለጠ ስኬት ይተጋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ማሳሰቢያ
የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 1 (በተለምዶው የሀገር ውስጥ/Domestic Terminal) የማስፋፊያ እና የማዘመን ስራው ተጠናቅቆለት ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ የሀገር ውስጥ በረራ ለማድረግ ወደ ኤርፖርት የምትመጡ ክቡራን መንገደኞቻችን በቀጥታ ወደ ተርሚናል ቁጥር 1 ብቻ እንድትገቡ በትህትና እናሳውቃለን።

ስማችንን በደማቅ ቀለም ባስጻፍንበት ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ስራዎን በስኬት እንዲከውኑ፤ ከወዳጅ ዘመድ እንዲገናኙ እናደርጋለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የአክብሮት ሰላምታችን ከበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል በያላችሁበት ይድረስ። ትኬትዎን በሞባይል መተግበሪያችን ቆርጠው ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ያግኙ።
መልካም ቀን ይሁንልዎ! https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
መልካም ቀን ይሁንልዎ! https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app
#የኢትዮጵያአየርመንገድ