Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.78K photos
142 videos
2 files
413 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው 37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የመጡትን ከ50 በላይ የሀገራት መሪዎችንና ልዑካን አውሮፕላኖች ከተለያዩ “ቪአይፒ” እና “ቪቪአይፒ” እንግዶች አውሮፕላኖች ጭምር በአዲስ አበባ ቦሌ አለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ከመደበኛ በረራዎቹ ጎን ለጎን በተቀላጠፈ እና ሙያዊ ብቃትን ባጣመረ መልኩ በስኬት አስተናግዷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከፎቶ ማህደራችን። በፎቶው ላይ ከሚታዩት የቀድሞ ባልደረቦቻችን ማንን ያስታውሳሉ?

#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲን ተቀላቅለው ህልምዎን ያሳኩ!
https://etau.edu.et/
#የኢትዮጵያአቪዬሽንዩኒቨርሲቲ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን እርስ በርስ ብሎም ከዓለም ጋር የማስተሳሰር ትልሙን አጠንክሮ በመቀጠል ከ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በብሩኪና ፋሶ ዋጋዱጉ በኩል የሴራሊዮን ዋና ከተማ ወደሆነችው ፍሪታውን ከተማ በሳምንት ሶስት ቀን የሚደረግ የመንገደኞች በረራ የሚጀምር መሆኑን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በበረራዎቻችን ላይ ሁሉ በኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ልናገለግልዎ ዝግጁ ነን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የአክብሮት ሰላምታችን ከበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል በያላችሁበት ይድረስ። መልካም ቀን ይሁንልዎ!
 
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ሁሌም በፈገግታ በታጀበው አገልግሎታችን ይደሰቱ! መልካም ቀን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደንቢዶሎ በሳምንት ሶስት በረራዎችን ዛሬ በደማቅ ስነ-ስረአት መልሶ አስጀምሯል፡፡ይህ በረራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ የሚሰጠውን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት የማስፋፋት አንዱ አካል ነው።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የሀገር ውስጥ በረራዎን በምቾት ያድርጉ።
https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-expands-its-domestic-network-with-three-weekly-passenger-services-to-dembi-dollo-ethiopia
#ኢትዮጵያአየርመንገድ
ከበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል እንኳን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር በደህና መጡ! ቀጣይ መዳረሻዎ የት ነው? በምቾት ልናደርስዎ ሁሌም ዝግጁ ነን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ማሳሰቢያ

የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 1 (በተለምዶው የሀገር ውስጥ/Domestic Terminal) የማስፋፊያ እና የማዘመን ስራው ተጠናቅቆለት ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ የሀገር ውስጥ በረራ ለማድረግ ወደ ኤርፖርት የምትመጡ ክቡራን መንገደኞቻችን በቀጥታ ወደ ተርሚናል ቁጥር 1 ብቻ እንድትገቡ በትህትና እናሳውቃለን።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ለኢ-ኮሜርስ ሸቀጦች እንዲሁም ለፖስታ እና ጥቅል መልእክቶች የሎጂስቲክስ አገልግሎትን የሚያቀላጥፈው እና አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርገው ከኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የሚበረከተው የምስራች ይፋ ሊደረግ ሰዓታት ብቻ ቀሩት፡፡

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያካርጎእናሎጂስቲክስአገልግሎት