Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.78K photos
142 videos
2 files
413 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ጉዞዎን በቅንጦት ያድርጉ::

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
103👍39🥰19👏6
በረራዎን አይረሴ ለማድረግ ከእኛ ዘንድ ሁሉም ተሰናድቷል። መልካም ሳምንት ይሁንልዎ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
72👍42🥰26👏10
ሳምንቱን በስኬት ከፍታ ላይ ሆነው ያሳልፉ! ከዘመናዊ አውሮፕላኖቻችን ውስጥ በየትኞቹ በርረዋል?

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
86👍30🥰7👏3
በቀደሙት ግዜያት ስንከተለው የነበረው “አፍሪካውያንን እርስ በርስ ማስተሳሰር” የተሰኘው መርሀችን ዛሬም በድምቀት ቀጥሎ ለ37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በአፍሪካዋ መዲና አዲስ አበባ የተገኙ 20 የአፍሪካ አገራት መሪዎችን በግዙፉ እና ዘመናዊው የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በክብር ተቀብለን አስተናግደናል። የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በአፍሪካ ከሚገኙ ትላልቅ ሆቴሎች አንዱ ሲሆን በውስጡም 1024 ክፍሎች አሉት። የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል እንደ አህጉራችን አፍሪካ ሁሉ በህብረ ቀለማት አሸብርቆ እንግዶቹን በክብር አስተናግዶ ሸኝቷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያስካይላይትሆቴል #ፓንአፍሪካዊ
👍8934🥰9
ያሳለፍነው የፍቅረኞች ቀን በመላው አለም ደምቆ እንዲከበር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ60 በላይ የበረራ አገልግሎቶች 250 ሚሊዮን (4500 ቶን) የሚጠጉ የአበባ ዘለላዎችን ከአዲስ አበባ፣ ናይሮቢ እና ቦጎታ ወደ መላው የዓለም ክፍል አጓጉዟል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍8524👏12🎉7😍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው 37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የመጡትን ከ50 በላይ የሀገራት መሪዎችንና ልዑካን አውሮፕላኖች ከተለያዩ “ቪአይፒ” እና “ቪቪአይፒ” እንግዶች አውሮፕላኖች ጭምር በአዲስ አበባ ቦሌ አለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ከመደበኛ በረራዎቹ ጎን ለጎን በተቀላጠፈ እና ሙያዊ ብቃትን ባጣመረ መልኩ በስኬት አስተናግዷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍12135👏22🎉4🥰3
ከፎቶ ማህደራችን። በፎቶው ላይ ከሚታዩት የቀድሞ ባልደረቦቻችን ማንን ያስታውሳሉ?

#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
96👍27🥰21
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲን ተቀላቅለው ህልምዎን ያሳኩ!
https://etau.edu.et/
#የኢትዮጵያአቪዬሽንዩኒቨርሲቲ
😍71👍4526🥰5🎉5
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን እርስ በርስ ብሎም ከዓለም ጋር የማስተሳሰር ትልሙን አጠንክሮ በመቀጠል ከ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በብሩኪና ፋሶ ዋጋዱጉ በኩል የሴራሊዮን ዋና ከተማ ወደሆነችው ፍሪታውን ከተማ በሳምንት ሶስት ቀን የሚደረግ የመንገደኞች በረራ የሚጀምር መሆኑን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
😍53👍3721🎉8👏7
በበረራዎቻችን ላይ ሁሉ በኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ልናገለግልዎ ዝግጁ ነን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍9957😍9🥰7
የአክብሮት ሰላምታችን ከበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል በያላችሁበት ይድረስ። መልካም ቀን ይሁንልዎ!
 
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍12663😍8👏6🥰5🎉3
ሁሌም በፈገግታ በታጀበው አገልግሎታችን ይደሰቱ! መልካም ቀን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍8930🥰16
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደንቢዶሎ በሳምንት ሶስት በረራዎችን ዛሬ በደማቅ ስነ-ስረአት መልሶ አስጀምሯል፡፡ይህ በረራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ የሚሰጠውን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት የማስፋፋት አንዱ አካል ነው።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የሀገር ውስጥ በረራዎን በምቾት ያድርጉ።
https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-expands-its-domestic-network-with-three-weekly-passenger-services-to-dembi-dollo-ethiopia
#ኢትዮጵያአየርመንገድ
64👍33🎉7🥰6👏5