Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.58K photos
134 videos
2 files
399 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እንግሊዝ በረራ ማድረግ የጀመረበትን 50ኛ ዓመት አስመልክቶ የአየር መንገዳችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና ሌሎች ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት ብራውተን የሚገኘውን የኤርባስ A350 አውሮፕላን ክንፍ ማምረቻ ፋብሪካ ጎብኝተዋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #50ዓመታት
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣይ ለሚረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ሞዴል ሞተሮች አጠቃላይ የሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት እንግሊዝ ከሚገኘው “ሮልስ ሮይስ” የአውሮፕላን ሞተር አምራች ኩባንያ ጋር ተፈራረመ።
https://shorturl.at/koYZ9
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያአየርመንገድን ቀዳሚ ምርጫዎ በማድረግ አዲሱን ቀን፣ አዲሱን ሳምንት በስኬት ያሳልፉ! መልካም የስራ ሳምንት ተመኘን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያዊ እንግዳ አቀባበል ልናገለግልዎ ተዘጋጅተናል። እንኳን ደህና መጡ !
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ ኮሪያ ሴዑል በረራ ማድረግ የጀመረበትን 10ኛ አመት በድምቀት አከበረ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ ቦይንግ እና “ቲንክ ያንግ” ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ለተውጣጡ ታዳጊዎች እና ወጣቶች በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢንጅነሪንግ ዙሪያ የተዘጋጁ ስልጠናዎችን በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲ ሊሰጡ ነው። ስልጠናው በአቪየሽን ፣ በቴክኖሎጂ እና ተያያዥ የስራ መስኮች ላይ ዝንባሌ ላላቸው ታዳጊዎችና ወጣቶች እገዛ የሚያደርግ ነው።
በምናብ ወደኋላ ተጉዘን የቀደሙትን ስናስታውስ።
#ትውስታ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በረራዎን ምቹ እና አስደሳች ለማድረግ ሁልጊዜም እንተጋለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ጤና ይስጥልኝ!! ከእኛ ጋር ወደየት ለመጓዝ አቅደዋል ?
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮችና ሠራተኞች በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ። ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት አየር መንገዱ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ተሳትፎውን ቀጥሏል።እንደባለፈው አመት በዘንድሮ የክረምት ወቅትም 100 ሺህ ችግኞችን በተለያዩ ሥፍራዎች ለመትከል አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀን ወደ ሥራ ገብተናል ብለዋል።በዚህም የአየር መንገዱ አመራሮች ፣ሠራተኞች እና የቦርዱ አባላት በዛሬው ዕለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በመገኘት ከከተማው ፣ከክፍለ ከተማው እና ከወረዳው አመራር ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን ማኖራቸውን ተናግረዋል። የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡና በቀጣይም የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ