Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን @BianoAbel ናቸው፤ እናመሰግናለን! እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ ያነሷቸውን ምስሎች ይላኩልን፤ መልሰን እናጋራዎታለን።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አፍሪካን እርስ በርስ እና ከተቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት ለዘመናት በስኬት የዘለቀ ፓን-አፍሪካዊ አየር መንገድ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአዲስ አበባ ቦሌ አለም ዓቀፍ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ውስጥ ከምንሰጣቸው የደንበኞች አገልግሎት መካከል የቢዝነስ ክፍል (Cloud Nine) ላውንጅ ይገኝበታል። በዚህ ላውንጅ ውስጥ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ መንገደኞች ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ከማግኘታቸውም በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ባህልና የቱሪስት መስህቦች ጋር የሚተዋወቁበትም ስፍራ ነው። የዛሬው “የኢትዮጵያ” መርሐግብር በዚህ ላይ ያተኮረ ነው፤ ይከታተሉን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት መስራች መሪዎች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ለመመስረት በሚያደርጉት ያላሰለሰ ትጋት ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለሚያደርጓቸው በረራዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሚና የላቀ ነበር።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ የአፍሪካ ሀገራትን በባህል እና በበርካታ እድሎች ያስተሳሰረ እንዲሁም አህጉሪቱን ከሌሎች የአለም ሀገራት ጋር በቀላሉ እንድትገናኝ እንደ ድልድይ ሆኖ እያገለገለ ያለ ፓን-አፍሪካዊ አየር መንገድ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እውነተኛ የአፍሪካ አቪዬሽን ተምሳሌት የመሆን ርእይ አንግቦ የራሱን የአቪዬሽን አካዳሚ በመመስረት እና ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ተደራሽ በመሆን ሀገራቱ የራሳቸው አየር መንገድ እንዲያቋቁሙ አስችሏል። ዛሬ ወደ ዩኒቨርስቲ ደረጃ ያደገው ይህ አካዳሚ ከመላው የአፍሪካ ሀገራት ለሚመጡ የአቪዬሽን ሰልጣኞች ተደራሽ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ነጻ የአየር ትራንስፖርት እንቅስቃሴን ለመፍጠር እንዲሁም የአፍሪካን ቀጠናዊ እና አህጉራዊ ትስስር እጅግ የተቀላጠፈ ከማድረግ ባሻገር በንግድ፣ በቱሪዝም እና በመሰረተ ልማት የተሳሰረች አፍሪካን እውን ለማድረግ በማሰብ በአፍሪካ ህብረት ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን "The Single African Air Transport Market" (SAATM) የተሰኘ አጀንዳ እውን እንዲሆን የአንበሳውን ደርሻ እየተወጣ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊአየርመንገድ
የኡጋንዳ ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዝደንት ክብርት ጄሲካ አሉፖ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ ለመካፈል የኢትዮጵያ አየር መንገድን መርጠው ከእኛ ጋር ስለተጓዙ ክብር ይሰማናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በቻይና ዢያሜን እና በብራዚል ሳኦፖሎ መካከል እየሰጠ ያለውን የዕቃ ጭነት አገልግሎት ሁለተኛ ዓመት አከበረ። ይህ በሁለቱ ከተሞች መካከል በሚደረገው የዕቃ ጭነት አገልግሎት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሁለቱን አህጉራት ንግድ ትስስር ይበልጥ ያጠናከረ ሲሆን እስካሁን በሁለት ዓመታት ውስጥ በተደረጉ 474 በረራዎች ወደ 33,226 ቶን ያህል የዕቃ ጭነት ማጓጓዝ ተችሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ ባለው አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የኢ-ኮሜርስ አገልግሎት አለም ዓቀፍ የዕቃ ጭነት አገልግሎት ላይ የላቀ አስተዋፅዖ እያበረከተ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ፓን አፍሪካዊው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የተካፈሉ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ቀዳሚ ምርጫ በመሆኑ ክብር ይሰማዋል!
በዛሬው ዕለት የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ጆሴፍ ቦካይ፣ ክቡር ኤቭራስቴ ንዳሺሚዬ የብሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት፣ ክቡር ፎውስቲን ታውዴራ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት እንዲሁም ክቡር ሙሃማድ ጃሎው የጋምቢያ ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዝደንት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ምርጫቸው በማድረግ ወደየሀገሮቻቸው ተመልሰዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰጠውን የላቀ አገልግሎት በማጠናከር አፍሪካውያንን እርስበርስና ከተቀረው ዓለም ጋር የማገናኘት ተልዕኮውን በትጋት ይወጣል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ ፤ ከ140 በላይ መዳረሻዎቻችን የማይረሱ ትዝታዎችን ያሳልፉ! ለስራ አሊያም ለመዝናናት የሚመርጧቸው መዳረሻዎቻችንን ያጋሩን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ትሶኮአኔ ሳሙኤል እንዲሁም የካሜሩን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ጆሴፍ ንጎቴ የኢትዮጵያ አየር መንገድን መርጠው ከእኛ ጋር ስለተጓዙ ክብር ይሰማናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሁሉም ጉዞ ልዩ የሚያደርገው የራሱ ማስታወሻ አለው። ቀጣዩ ጉዞዎን ከእኛ ጋር በማድረግ አዲስ ትውስታን ይፍጠሩ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በአስደናቂ የተፈጥሮ ውበቷ እና በመዝናኛ ስፍራዎቿ ወደምትታወቀው ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የማይረሳ ጉዞ ያድርጉ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ