Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት መስራች መሪዎች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ለመመስረት በሚያደርጉት ያላሰለሰ ትጋት ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለሚያደርጓቸው በረራዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሚና የላቀ ነበር።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ነጻ የአየር ትራንስፖርት እንቅስቃሴን ለመፍጠር እንዲሁም የአፍሪካን ቀጠናዊ እና አህጉራዊ ትስስር እጅግ የተቀላጠፈ ከማድረግ ባሻገር በንግድ፣ በቱሪዝም እና በመሰረተ ልማት የተሳሰረች አፍሪካን እውን ለማድረግ በማሰብ በአፍሪካ ህብረት ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን "The Single African Air Transport Market" (SAATM) የተሰኘ አጀንዳ እውን እንዲሆን የአንበሳውን ደርሻ እየተወጣ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓንአፍሪካዊአየርመንገድ