Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በአፍሪካ አህጉር ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና ላይ አተኩሮ በጋና አክራ በተካሄደው አመታዊው የ “2025 የአፍሪካ ፕሮስፔሪቲ ዲያሎግ” ላይ አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት በማገናኘት ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተጫወተ ላለው ሚና ላሳዩት የላቀ የአመራርነት ሚና የ “Leadership in Connecting Africa through Transport Award” ተሸላሚ ሆነዋል።
ይህ ሽልማት አፍሪካን እርስ በርስ በማገናኘት ቁርጠኛ የአመራርነት አስተዋፅዖ ላበረከቱ ግለሰቦች ዕውቅና የሚሰጥበት ሲሆን የዘንድሮው የ “2025 የአፍሪካ ፕሮስፔሪቲ ዲያሎግ” የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የታላላቅ አህጉር ዓቀፍ የንግድ ተቋማት መሪዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በተገኙበት በጋና አክራ ተካሂዷል። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-group-ceo-honored-with-prestigious-leadership-in-connecting-africa-through-transport-award
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የበረራ አድማሱን ከግዜ ወደ ግዜ እያሰፋ የመጣው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ተጨማሪ አዳዲስ አለም ዓቀፍ መዳረሻዎች በረራ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቅቋል።
እነዚህ አዳዲስ መዳረሻዎቻችንን መገመት ይችላሉ?

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወደ በርካታ አለም ዓቀፍ መዳረሻዎቻችን አብረውን ይጓዙ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ ሰኔ9 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በህንድ 5ኛ የመንገደኛ በረራ መዳረሻ ወደምትሆነው ሀይድራባድ ከተማ በሳምንት ሶስት ቀን የሚደረግ አዲስ በረራ እንደሚጀምር ሲያበስር በደስታ ነው። የዚህ በረራ መጀመር በህንድ የሚኖረንን የበረራ አድማስ ከማስፋቱም በተጨማሪ በአፍሪካ እና እስያ መካከል ያለውን ዘርፈብዙ ግንኙነት ከፍ የሚያደርግ ነው። ትኬትዎን በድረገፃችን www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app በመቁረጥ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሀይድራባድ ይጓዙ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አስደናቂ የሆኑትን የኢትዮጵያን የተፈጥሮ መስህቦች ይጎብኙ። የኢትዮጵያ ሆሊደይስ በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ የጉዞ ጥቅሎች ተጠቅመው ጥንታዊ የተፈጥሮ መስህቦችንና ማራኪ መልከዓምድሮችን ይጎብኙ። ስለጉዞ ጥቅሎቹ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ድረገፃችንን www.ethiopianholidays.com ይጎብኙ አልያም በኢሜይል አድራሻ ETHolidays@ethiopianairlines.com. ይፃፉልን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኢቲሆሊደይስ #ምድረቀደምት
ፍፁም ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ አለም ዓቀፍ ደረጃውን ከጠበቀ አገልግሎት ጋር በኢትዮጵያ አየር መንገድ! ትኬትዎን በድረገፃችን www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app ይቁረጡ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ