Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.74K photos
140 videos
2 files
410 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተከበሩ አንጌላ ራይነር እና የልዑክ ቡድናቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለመጎብኘት በመምጣታቸው ላቅ ያለ ክብር ተሰምቶናል!
ክብርት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የልዑክ ቡድናቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በነበራቸው ቆይታ የአየር መንገዱ የሥራ ክፍሎች የሆኑትን የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ፣ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል እና የተግባራዊ በረራ ማሰልጠኛ ምስለ በረራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በመቀጠልም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከአቶ መስፍን ጣሰው እና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራር አባላት ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘመናዊ አውሮፕላኖቹ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ሂትሮው፣ ለንደን ጋትዊክ እና ማንችስተር ከተሞች አሥራ ስድስት ሳምንታዊ በረራ በማድረግ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ትስስርን ለማጠናከር እየሰራ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አመራር አባላት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ።
በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቪርስቲ፣ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል፣ የኢትዮጵያ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እና የምስለ በረራ ክፍልን የስራ እንቅስቃሴዎች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና ከአየር መንገዳችን የአመራር አባላት ጋር በአየር መንገዱ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር ከሚተዳደሩ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አንዱ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ