Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.55K photos
134 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
መግለጫ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ. ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ ኤርትራ በየቀኑ የሚያደርገውን በረራ ለመቀጠል ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች አስመራ ውስጥ ስላጋጠሙት ከነገ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አስመራ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ማቋረጡን ለክቡራን ደንበኞቹ ከይቅርታ ጋር ይገልጻል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ ለመጓዝ ቀድመው ትኬት ለቆረጡ ውድ መንገደኞቹ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በሌሎች አየር መንገዶች የሚጓጓዙበትን ሁኔታ ያመቻቻል። አለያም እንደአማራጭ በውድ ደንበኞቹ ፍላጎት ለትኬት የከፈሉትን ገንዘብ ሙሉውን ተመላሽ ያደርጋል።

ድረገጻችንን በመጎብኘት  www.ethiopianairlines.com አልያም ወደ ዓለም-አቀፍ የጥሪ መቀበያ ማዕከላችን በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

በዚህ አጋጣሚ ከአየር መንገዳችን አቅም በላይ በሆነ ሁኔታ በተፈጠረው የበረራ መቋረጥ በውድ ደንበኞቻችን ላይ ለሚፈጠረው መጉላላት አየር መንገዱ ከልብ ይቅርታ ይጠይቃል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አላያንስ አባል
መግለጫ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከዛሬ ጀምሮ ወደ አስመራ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይህንን ውሳኔ ተከትሎ ክቡራን የአስመራ መንገደኞቻችንን ከሙጉላላት ለመታደግ አስፈላጊውን ሁሉ የበረራ አማራጭ እያቀረብን ሲሆን የመንገደኞቻችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በተለያዩ አየር መንገዶች ወደ መዳረሻቸው የማድረስ ስራችንን ቀጥለናል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ውድ የኤርትራ መንገደኞቻችን ወደ ዓለም-አቀፍ የጥሪ ማዕከላችን 6787 በመደወል እና 5 ቁጥርን በመጫን ለእናንተ ብቻ ተብሎ በተዘጋጀ ልዩ የጥሪ ማዕከል አገልግሎት ጉዟችሁን ለማቅለል ተዘጋጅተናል።

ሌሎች ውድ መንገደኞቻችን ይህንን ወቅታዊ ጉዳይ እስክንፈታ ድረስ በ6787 ብቻ በመደወል የተለመደውን አገልግሎት ማግኘት እንደምትችሉ እያስታወስን በዚሁ አጋጣሚ ለአስመራ መንገደኞቻችን ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በተፈጠረው የበረራ መቋረጥ ለሚያጋጥማችሁ መጉላላት በድጋሚ ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን Nafkot Aschenaki ናቸው፤ እናመሰግናለን!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በ “World Travel Awards” መንገደኞች በተለያዩ ዘርፎች ድምፅ የሚሰጡበት ቀን ሊጠናቀቅ ሶስት ቀናት ቀርተውታል። በስድስት ዘርፎች ዕጩ ለሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከታች በተቀመጠው ሊንክ አሊያም ምስሉ ላይ ባለው QR-Code ተጠቅመው ድምፅዎን እንዲሰጡ ተጋብዘዋል።
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በ “World Travel Awards” መንገደኞች በተለያዩ ዘርፎች ድምፅ የሚሰጡበት ቀን ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ቀርተውታል። በስድስት ዘርፎች ዕጩ ለሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከታች በተቀመጠው ሊንክ አሊያም ምስሉ ላይ ባለው QR-Code ተጠቅመው ድምፅዎን እንዲሰጡ ተጋብዘዋል።
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የቀን አቆጣጠራችን ከተቀረው ዓለም ልዩ ከሚያደርጉን ነገሮች አንዱ ነው። ይህ ልዩ የቀን አቆጣጠር ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች መጥተው ሀገራችንን ለሚጎበኙ ጎብኚዎች ልዩ ስሜትን ይፈጥራል።
በድረ ገፃችን www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app ተጠቅመው ትኬትዎን በመቁረጥ የኢትዮጵያን ልዩ ባህል ፣ታሪክ እና እሴት በአካል መጥተው ይመልከቱ ።በአዲስ ዓመት በአዲስ መንፈስ ልዩ ግዜ ያሳልፉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አዲስዓመት
ላለፉት በርካታ ዓመታት በተለያዩ የአፍሪካ መሪዎች ተመራጭ ሆኖ የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑም ወደ ቻይና ቤጂንግ የተጓዙትን የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ኤቫርስትዬ ንዲያሽሚዬ፣ ክብርት ቀዳማዊት እመቤት አንጀሊን ንዳዩባሃ እና የልዑክ ቡድናቸውን በበረራዎቻችን ላይ በክብር በማስተናገዳችንና ምርጫቸው በመሆናችን ክብር ይሰማናል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በ “World Travel Awards” መንገደኞች በተለያዩ ዘርፎች ድምፅ የሚሰጡበት የመጨረሻው ቀን ላይ እንገኛለን። በስድስት ዘርፎች ዕጩ ለሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከታች በተቀመጠው ሊንክ አሊያም ምስሉ ላይ ባለው QR-Code ተጠቅመው ድምፅዎን እንዲሰጡ ተጋብዘዋል።
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3#votenow
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ፊደል ከነአጻጻፉና ሥርዓቱ ጋር ያላት አገር ናት። እርስዎም ልንቀበለው በተቃረብነው በአዲሱ ዓመት ከወዳጅ ጓደኛዎ ጋር በድረገፃችን www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app ተጠቅመው ትኬትዎን በመቁረጥ እነዚህን በዓለም ልዩ የሆኑ እሴቶች፣ታሪኮችና ባህሎቻችንን እንዲጎበኙ እና እንዲያስጎበኙ ተጋብዘዋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አዲስዓመት
ኢትዮጵያ በቀዳሚነት አፍሪካውያንን እርስ በርስ ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር እያገናኘ ለዘመናት የዘለቀ ፓን አፍሪካዊ አየር መንገድ መገኛ አገር ናት። በመጪው አዲስ ዓመት ትኬትዎን በድረገፃችን www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app ገዝተው በአዲስ መንፈስ በአዲስ ከፍታ ከፓን አፍሪካዊው አየር መንገድዎ ጋር ይብረሩ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አዲስዓመት
ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ፤ ምድረ ቀደምት!
ትኬትዎን ባመችዎት አማራጭ ቆርጠው አገርዎን ይጎብኙ ያስጎብኙ ።
ድረ-ገፅ www.ethiopianairlines.com
ተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አዲስዓመት
ኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ አየር ትራንስፖርት እና አቪዬሽን ልህቀት ማዕከል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አዲስዓመት
ከ2016 ስኬቶቻችን በጥቂቱ። 2016ን ከነዚህ ስኬቶች ጋር በማገባደድ ለ2017 በአዲስ መንፈስ ለበለጠ ከፍታ ተዘጋጅተናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አዲስዓመት #ስኬታማዓመት
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2017 አደረሳችሁ እያለ መጪው ዘመን የሰላም፣ የስኬት እና የደስታ እንዲሆንልን ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል።
መልካም አዲስ ዓመት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያአዲስአመት
ክቡራን መንገደኞቻችን

በናይሮቢ የጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሠራተኞች በስራ ማቆም አድማ ላይ በመሆናቸው ወደ ናይሮቢ የምናደርገው በረራ በታቀደለት መርኃ ግብር እየተከናወነ አይደለም።

በዚህ አጋጣሚ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልን የምንገኝ መሆኑን እየገለጽን በክስተቱ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ እንጠይቃለን።

ለበለጠ መረጃ የዓለም አቀፍ የደንበኞች አገልግሎት ማዕከላችንን በ+251 11 617 9900 ወይም በ 6787 በመደወል አልያም ናይሮቢ የሚገኘውን ትኬት ሽያጭ ቢሯችንን እንዲጎበኙ በትህትና እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አልያንስ አባል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ፖርት ሱዳን የመንገደኛ በረራ አገልግሎት የሚጀምር መሆኑን ሲገልፅ በደስታ ነው።

ይህ አዲስ በረራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት ለማስተሳሰር ያለውን ቁርጠኝነት ማሳያ ከመሆኑም በላይ በቀጠናው ያለውን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የንግድና ቱሪዝም ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው።

ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://rb.gy/faairf

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አዲስበረራ #ፖርትሱዳን
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስታር ዋይድ አዋርድ 2016 ‘ቀልጣፋ አገልግሎት ሰጪ የመንግስት ተቋም’ በመባል በሕዝብ ድምፅ ተሸላሚ ሆኗል። ሽልማቱን አስመልክተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሽልማት ርክክብ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ይህ ሽልማት የሚያስደስተን ብቻ ሳይሆን ይበልጥ ለላቀ ደረጃ በትጋት እንድንሰራ የሚደግፈን ነው ብለዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ