ሰ/መ/ቁጥር 241073 ሀምሌ 27 ቀን 2015 ዓ/ም #ውርስ_ህግ #ኑዛዜ
አመልካች፡- አቶ ዳዊት አበራ አቶ ዳዊት አበራ- ሞግዚት ፀሐይነሽ ተሾመ
ተጠሪ፡- ወ/ሮ አለምነሽ ከፈለኝ-
በሁኔታ ላይ የተመሰረተ (conditional legaty) ወይም በገደብ የተደረገ ኑዛዜ
በ#ወራሽ የገቢ ማጣት እና በጤና ሁኔታ ችግር የተነሳ ኑዛዜ ሊሻሻል ወይም ቀሪ ሊሆን ስለሚችልበት ሁኔታ
#ፍ/ሕ/ቁጥር 879/1 እና #ፍ/ሕ/ቁጥር 872
በዚህ መዝገብ አመልካች የሟች ልጅ ሲሆኑ ተጠሪ ሟች ኋላ ላይ (ከአመልካች እናት በኋላ) ያገቧት ሚስት ናት። ሟች ለልጆቻቸው ንብረታቸውን እንዲወርሱ ኑዛዜ የተዉ ቢሆንም በኑዛዜው ተጠሪ በህይወት እስካሉ የመጠቀም መብት የተሰጣቸው በመሆኑ ኑዛዜው ተፈጻሚነት የሚያገኘው ተጠሪ ከሞቱ በኋላ ነው።
የአመልካች ጥያቄ ሟች ለተጠሪ በውርስ ሐብት በህይወት እስካሉ እንዲጠቀሙ ኑዛዜ ማድረጋቸው አመልካች ያለብኝን የአይምሮ ጤና እና የኑሮ ችግር ለመወጣት እንዳልችል የሚያደርገኝ ስለሆነ (በተጨማሪም ኑዛዜው በዝምታ የነቀለኝ ስለሆነ የሚል መከራከሪያም አቅርበዋል።) ኑዛዜው ሊፈርስ ይገባል የሚል ነው።
የ#ሰበር ችሎቱ የተያዘውን ጉዳይ አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ እና የሐተታው ክፍል ከዚህ በታች ይነበባል
አመልካች ባለባቸው ጤና ችግር ምክንያት ስራዎችን በመስራት ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት የራሳቸውን ገቢ ማግኘት እና ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎችን መሸፈን የማይችሉ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ሟች ለክርክሩ መሰረት በሆነው ኑዛዜ ለተጠሪ በህይወት እስካሉ በውርስ ሀብቱ የመጠቀም መብት ባያስተላልፉ ኖሮ አመልካች የውርስ ድርሻውን በማግኘት ለኑሮ እና ለጤና አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎችን ለመሸፈን ያስችላቸዋል፡፡ የሟችን ፍላጎት ለማስጠበቅ ሲባል ብቻ የአመልካች የከፋ ችግር እየታወቀ በኑዛዜ የተቀመጠው ገደብ መቀጠል አለበት የሚባል ከሆነ የአመልካችን በህይወት የመኖር መብት አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ለሞራል ተቃራኒ ይሆናል፡፡ ተጠሪ በሰጡት መልስ የአመልካች ብቻ ሳይሆን የተጠሪም የጤና ችግር ከግምት ሊገባ ይገባል በሚል የሚከራከሩ ቢሆንም ተጠሪ ለክርክር መሰረት ከሆነው ንብረት ላይ 50% የሚስትነት ድርሻ ያላቸው ከመሆኑ አንጻር በኑዛዜው ላይ የተቀመጠው ገደብ አመልካችን በተመለከተ ብቻ ተፈጻሚነቱ ቢቀር በተጠሪ ላይ የሚደርስባቸው ጉዳት ከፍተኛ ወይም ለሞራል ተቃራኒ ነው ሊባል አይችልም፡፡
ሟች ለተጠሪ በህይወት እስካሉ የውርስ ድርሻቸውን የመጠቀም መብት በኑዛዜ አስተላልፈዋል፡፡ በኑዛዜው መሰረት የሟች ወራሾች ድርሻቸውን ማግኘት የሚችሉት ተጠሪ ከዚህ አለም በሞት ሲለዩ ብቻ ነው፡፡ ይህም ሟች ለወራሾቻቸው ያረጉት ኑዛዜ በሁኔታ ላይ የተመሰረተ (conditional legaty) ወይም በገደብ የተደረገ ኑዛዜ መሆኑን ያሳያል፡፡ በኑዛዜ የተጠቀሰው ሁኔታ ወይም በወራሾች ላይ በኑዛዜ የተደረገው ገደብ እንዳልተደረገ ሊቆጠር የሚችለው ግዴታው የማይቻል ወይም ለህግ ወይም ለመልካም ጠባይ ወይም ለሞራል ተቃራኒ ሆኖ ሲገኝ መሆኑን በፍ/ሕ/ቁጥር 879/1 ስር ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም በፍ/ሕ/ቁጥር 872 ስር ሟቹ በፊት ካደረገው ጋብቻ የተገኙ ተወላጆች ያሉት ከሆነ ለኋላኛው ባል ወይም ሚስት ጥቅም የተደረገ የኑዛዜ ቃል በዳኞች ሊቀነስ ወይም ሊሻር እንደሚችል ተመልከልቷል፡፡
እነዚህ ሁለት ድንጋጌዎች ሟች ከቀድሞ ትዳር የተፈሩ ልጆች እያሉ ለኋላኛው ሚስት ወይም ባል የተደረገ ኑዛዜ ከቀድሞ ትዳር የተወለዱትን ልጆች ጥቅም የሚጎዳ ከሆነ በተወላጆቹ ጠያቂነት ዳኞች ኑዛዜውን ለማሻሻል ወይም ሙሉ ለሙሉ ቀሪ ሊያደርጉ እንደሚችሉ፤ በተለይም ኑዛዜው በግዴታ ላይ የተመሰረተ ከሆነ እና ግዴታው ለህግ፣ ለሞራል ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ ከሆነ በኑዛዜው የተመለከተው ገደብ ወይም ግዴታ በኑዛዜው እንዳልተጻፈ ይቆጠራል፡፡ በእርግጥ እነዚህ ድንጋጌዎች ተግባራዊ ሲደረጉ በጥንቃቄ ሊሆን ይገባል፡፡ ምክንያቱም ኑዛዜ የተናዛዙን ፍላጎት መግለጫ እና ሟች ንብረቱን ለሚፈልገው ሰው የማስተላለፍበት አንዱ መንገድ በመሆኑ ኑዛዜው ሲቀነስ ወይም ሲሻሻል ወይም በኑዛዜ የተቀመጠው ገደብ እና ግዴታ ቀሪ ሲደረግ የተናዛዙን ፍላጎት እንዳይቃረን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ በሌላ በኩል ኑዛዜው ላይ የተገለጸው ግዴታ ለመፈጸም የማይቻል ወይም ለህግ ወይም ለሞራል ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ መሆኑ በጥንቃቄ በዳኞች ተመርምሮ ግዴታው ሊፈጸም የማይችል ወይም ለህግ ወይም ለሞራል ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ ሆኖ ከተገኘ በኑዛዜ ላይ የተመለከተው ገደብ ወይም ግዴታ ቀሪ ሊሆን ይገባል፡፡

👍15❤3👎2
በውርስ ሕግ አተረጓጎም ዙሪያ በተሰጡ አንዳንድ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጎሞች ላይ የቀረበ ትችት
በ፦ መላከ ጥላሁን አየነው
ጸሐፊው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ሲሆኑ በውርስ ሕግ ላያ ያላቸውን ሰፊ ዕወቀትና ልምድ መሠረት በማድረግ በጽሑፋቸው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጧቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች የውርስ ሕጉን ያልተከተሉ መሆኑን ያብራራሉ። በጽሑፋቸው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በጽሑፋቸው በሚያነሷቸው የሰበር ውሳኔዎች የሕግ ትርጉሞቹ ርስበርስ የሚጋጩ፣ ወጥነት የሌላቸው መሆናቸውን እንዲሁም ለዚህ ምክንያት ነው ያሏቸውን የሕግ ትንታኔ ያቀርባሉ።
የጽሑፉ ዓላማ በሰበር ችሎት የውርስ ሕግ አተረጓጎም ላይ ያለውን ችግር እና የመፍትሄ ሃሳቦች በማሳየት ወደ ፊት የሰበር የሕግ ትርጉሞች ተለውጠው ችግሮቹ ተፈትው የውርስ ክርክሮች ሕጉን መሠረት አድርገው ወጥ፣ ተገማች እና ተመሳሳይ መፍተሄ እንዲያገኙ አስተዋጽዖ ለማድረግ መሆኑን ያሳስባሉ።
ጽሑፉን ቢያነቡ እጅጉን ያተርፋሉ!
መልካም ንባብ
#abyssinialawblog #ውርስ #የሰበርውሳኔትችት
https://www.abyssinialaw.com/blog/criticism-of-some-binding-legal-interpretations-of-the-federal-supreme-court-on-the-interpretation-of-inheritance-law
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE
#ጠበቃና #የሕግአማካሪ
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
👉Telegram👈
https://t.me/AleHig
👉Telegram_Group👈
https://t.me/AleHig_Group
👉Instagram👈
https://www.instagram.com/alehigofficial
👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/alehig/
✅New official website ✅
https://www.alehig.com
Abyssinialaw
በውርስ ሕግ አተረጓጎም ዙሪያ በተሰጡ አንዳንድ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጎሞች ላይ የቀረበ ትችት
ይህ ጽሑፍ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከውርስ ሕጉ አጠቃላይ አወቃቀር እና አደረጃጀት ወጥተው በአንደኛው የውርስ ሕግ ክፍል የተደነገገን ድንጋጌ አግባብነት ለሌለው ሌላ የውርስ ሕግ ክፍል ተግባራዊ በማድረግ አንዳንዴም በጉዳዩ ላይ ተፈጻሚነት ያላቸዉን የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች በመተዉ ...
👍12