አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
FXD012024-FOREIGN-EXCHANGE-1-1.pdf
22.8 MB
NATIONAL BANK OF ETHIOPIA FOREIGN EXCHANGE DIRECTIVE NO. FXD/01/2024

በዚህ መመሪያ መሰረት የውጭ ምንዛሪ ማግኘት የሚችሉት እነማን ናቸው ?

➡️ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የተፈቀደላቸው የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ከኢትዮጵያ ውጭ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊውያን ወይም በአገሪቱ ውስጥ የሚኖር የውጭ ዜጎች ናቸው።

➡️ ምንዛሪ ለማግኘት የሚፈልጉ ግለሰቦች ለበዓል ፣ ለትምህርት ፣ ለህክምና ጉዞዎች እና ሌሎች የግል ጉዳዮች እንደሚጓዙ የሚያሳይ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ የመግቢያ ቪዛ እና የአየር ትኬት የማቅረብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

➡️ ተጓዦች ከምንዛሪ ቢሮዎች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም የዚህ አቻ የሆነ የሌላ አገር ገንዘብ በጥሬ ወይም በክፍያ መፈጸሚያ ካርድ (debit card) አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።

➡️ የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ያላቸው ተጓዦች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ድረስ ማግኘት ተፈቅዶላቸዋል።

በብሔራዊ ባንክ ካልተፈቀደ በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነዋሪ በአንድ ጉዞ ላይ ከ10,000 የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ በካሽ መያዝ አይችልም።

➡️ ለንግድ የሚጓዙ ግለሰቦችም የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ይችላሉ።

➡️ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ፓስፖርት እና የአየር ትኬት ለሚያቀርቡ ለንግድ ድርጅት ተወካዮች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ እንዲችሉ ተፈቅዷል። እነዚሁ ቢሮዎች ፦
- ለንግድ ድርጅቶች፣
- ለበጎ አድራጎት ተቋማት
- ለሃይማኖት ማኅበራት፣
- ለንግድ ትርኢቶች፣
- ለቱሪዝም
- ለባህል እና ለስፖርቶች አዘጋጆች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ ይችላሉ።

➡️ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ለመንግሥት ተጓዦች ለምግብ፣ ለማረፊያ እና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ከ10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ የማይበልጥ የውጭ ምንዛሬ ሊሸጡ ይችላሉ።

➡️ ነዋሪ ላልሆኑ የውጭ አገር ዜጎች እና ቱሪስቶች ብርን ወደ ውጭ ምንዛሬ ሊለውጡ የሚችሉበት አሠራርም አለ። ፓስፖርት፣ ትክክለኛ ቪዛ እና የአየር ትኬት የሚያቀርቡ ሰዎች ያለማስረጃ እስከ 500 የአሜሪካን ዶላር መለወጥ ይችላሉ። ከ500 ዶላር በላይ መለወጥ የሚፈልጉ ከሆነ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ ቪዛ፣ የአየር ትኬት እና ተመጣጣኝ የሆነው የውጭ ምንዛሪ በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ገንዘብ መቀየሩን የሚያሳይ የተረጋገጠ የባንክ ማስረጃ ማቅርብ ይጠበቅባቸዋል።

ተጨማሪ ከላይ ተያያዘውን ፋይል ከፍተው ያንብቡ !

#NBE #BBC #Ethiopia

@tikvahethiopia
👍7
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀደም ሲል በ38 የገቢ ንግድ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ መነሳቱን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

ወደ ውጭ የሚደረግ የካፒታል ሂሳብ ፍስት እንደ በፊቱ የተገደበ እንደሆነ የውጭ ምንዛሪ ገበያው ለገቢ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ነጻ መሆኑንም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም " ቅድሚያ የማይሰጣቸው " ተብለው የተለዩ 38 ዓይነት ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ እግድ ጥሎ የነበረው የህገወጥ የምንዛሬ ገበያውን ይበልጥ ለማውረድ በማሰብ እንደነበር መገለጹ የሚዘነጋ አይደለም።

በወቅቱ 2014 ዓ/ም ላይ የአንድ የአሜሪካ ዶላር በባንክ ምንዛሬ 50 ብር ነበር ፤ አሁን ከ76 ብር ተሻግሯል።

አሁን እገዳው ተነስቶላቸዋል ከተባሉት 38ቱ የገቢ ንግድ ሸቀጦች ውስጥ ፦
➡️ የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች እና ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች (የነዳጅ)
➡️ የተገጣጠሙ የሞተር ሳይክሎች
➡️ አርቴፊሻል ጌጣጌጦች
➡️ የታሸጉ ምግቦች
➡️ የተለያዩ የጸጉር ጌጣጌጦች
➡️ ከሴራሚክ እና ፖርስሊን የተዘጋጁ የቤት እቃዎች
➡️ የውበት ወይም የመኳካያ ዝግጅቶች
➡️ ሽቶዎች
➡️ የቤት እና የቢሮ እቃዎች ይገኙበታል።

(ወደ ሀገር እንዳይገቡ እግድ ተጥሎባቸው የነበሩ የገቢ ንግድ ሸቀጦችን ዝርዝር ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
👍123👎1
👇👉 358 እና 418 👈👇⁉️
በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 418 መሠረት አቤቱታ አቅራቢ በዋናው ፍርድ ላይ ምንም ዓይነት ክርክር የሌለውና አፈጻጸም እንዲቀጥል ትዕዛዝ በተሰጠበት ንብረት ላይ መብት አለኝ የሚል ወገን መሆን አለበት፡፡
በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.358 መሠረት መብቱ የተነካው ወገን ፍርዱን ለሰጠው ፍ/ቤት መቃወሚያ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
መቃወሚያውን ማቅረብ የሚችሉትም ቀደም ሲል በተደረገው ክርክር ተካፋይ ያልነበሩት ወገኖች ናቸው፡፡

በጠበቃና የሕግ አማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍10
ECA Fellowship Advert - 2025_Eng (1).pdf
118.5 KB
🌍 Calling all young African professionals!
The United Nations Economic Commission for Africa (ECA) is inviting applications for the ECA Fellowship Program. Don't miss this incredible opportunity to make a difference in various thematic areas. Apply now!
👍51
FSCCD-Vol1-25-AregayG.pdf
10.7 MB
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ
ቅጽ 01-25
የካቲት 2015ዓ/ም
አዘጋጁ
አረጋይ ገ/እግዚአብሄር (LLB, LLM)
የሕግ አማካሪና ጠበቃ
👍11👏1
ሁሉን አቀፍ የአካል ጉዳተኞች አዋጅ እንዲጸድቅ የሚጠይቅ ሪፖርት
ለተ.መ.ድ ሰብአዊ መብት ምክርቤት ቀረበ!

ይህ ሪፖርት በኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ አይነስውራን ማህበር በጋራ ተዘጋጅቶ ለተ.መ.ድ ሰብአዊ መብቶች ምክርቤት የቀረበ ሲሆን፤ የማህበራቱ የጋራ ሪፖርት በየግዜው እየጨመረ  የመጣውን በአካል ጉዳተኞች ላይ የሚፈጸመውን የመብት ጥሰት በተጨባጭ ማስረጃዎች አስደግፎ በመተንተን፣ በአጥፊዎች ላይ  አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ  ተጠያቂነት እንዲሰፍን ይጠይቃል።  የጋራ ሪፖርቱ  የኢትዮጵያ መንግስት፣ በእኩልነት መብት እና ከአድልዎ በመጠበቅ መብት፤ በትምህርት፣ በጤና እና በሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች መብቶች፤ በሥራ እና በቅጥር መብት፤ እንዲሁም  ተደራሽነትን በተመለከተ የህግ ማሻሻያዎች እንዲያደርግ ይጠይቃል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት  የተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች ስምምነት ተጨማሪ ፕሮቶኮልን እንዲቀበል፤ የአፍሪካ የአካል ጉዳተኞችን ፕሮቶኮል እንዲቀበል እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የአካል ጉዳተኞች አዋጅን የአካል ጉዳተኞችን ማህበራት ጉልህ ተሳትፎ ባረጋገጠ ሁኔታ እንዲወጣ ምክረሀሳብ ያቀርባል።
በጋራ ሪፖርቱ ውስጥ የተመላከቱ ቁልፍ ምክረሀሳቦች በአራተኛው ሑሉን አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ (UPR) መድረክ በተ.መ.ድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት እንደምክረሀሳብ ሖነው በምክር ቤቱ ሀገራት እንዲነሱ ለማስቻል ኢንባሲያቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ሀገራት ሪፖርቱን ተደራሽ የማድረግ ስራ እና በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ እና ግንዛቤ እንዲያገኙ ጠንካራ  ተግባራጥ በትኩረት በመከናወን ላይ ይገኛሉ።
ከ Ethiopian center for disability and development (ECDD)
በጠበቃና የሕግ አማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍9
እውነት እና እውነትን ብቻ መመስከር
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

ፍትሕ እንዳትዛባና ሕግ እንዲከበር የሚፈልግ ዜጋ በወንጀልም ሆነ በፍትሐ-ብሔር የክስ ሂደት ላይ የሚያውቀውን ነገር በእውነት መመስከር አለበት።


በነዚህ ሂደቶች ውስጥ ፍርድ ቤቶች፣ ፖሊስ፣ የሕግ ባለሞያዎች ሥራዬ ብለው የሚወጧቸው ሚናዎች አሉ፡፡ ሌሎቻችን ደግሞ እንደ አንድ የሕብረተስቡ አባል እውነት እንዲወጣ ስለጉዳዩ ምናውቀውን ለሕግ አካል የመግለፅ የህሊና ብሎም እንደየሁኔታው የሕግ ግዴታ አለብን፡፡

በማንኛውም የሙግት ሂደት ላይ እውነቱ የሚነጥረው ስለ አከራካሪው ጉዳይ በቀጥታም ሆነ በሌላ መልኩ የሚያውቁ ሰዎች በሚሰጡት ማስረጃ ነው፡፡

ከነዚህ የማስረጃ ዓይነቶች ውስጥ አንዱ የሕብረተሰቡ አባላት ስለጉዳዩ ያዩትን፣ የሰሙትን ወይም በተለያየ መንገድ ያወቁትን ነገር በተመለከተ የሚሰጡት የነባሪነት፣ የእማኝነት ወይም የምስክርነት ቃል ነው፡፡

ማንኛችንም ነባሪ በነበርንበት የፍትሐ-ብሔር ጉዳይ ላይ ለፍትሕ ስንል ነገሩን በእማኝነት ማረጋገጥ ብሎም ወንጀል ከተፈፀመ ለሚመለከተው አካል የማሳወቅ ሕጋዊ ግዴታችንን መወጣቱና የሕግ አካል ሲጠይቀን የምናውቀውን በትክክል መግለፅ ማህበረሰቡ ውስጥ ወንጀል እንዳይስፋፋ፤የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥና ጥፋተኞች ለሕግ እንዲቀርቡ የምናደርገው ማህበራዊና ሕሊናዊ ግዴታችንም ጭምር ነው፡፡

በተለይ አንዳንድ ወንጀሎችን ዓይቶ እንዳላየ ማለፍ በራሱ ብቻውን በሕግ ያስጠይቃል፡፡ ሆኖም ግን ማንኛውም ሰው በማስረጃነት ቀርቦበት ሊያስወነጅለው በሚችል ጉዳይ ላይ ግን በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 19 (5) መሰረት የወንጀል ጥቆማ እንዲያቀርብ ወይም ምስክርነት እንዲሰጥ አይገደድም፡፡....... ይቀጥላል👇👇
👍6
................👇👇👇👇👇
👉በወንጀልም ሆነ በፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች ላይ ለምስክርነት ስንጠራም እነኚህን ጉዳዮች ልብ ማለት እና ሕግ የጣለብንን ግዴታ መወጣት ይጠበቅብናል።

1.መጥሪያን መቀበል

የሚላክልን መጥሪያ ለምን ጉዳይ፣ መቼ እና የት እንደተጠራን ይገልፅልናል። ስለ ጉዳዩ እንኳን ባናውቅ የተላከልንን መጥሪያ አልቀበልም ማለት አይገባም፡፡

ፍርድ ቤቱ መጥሪያ አልቀበልም ማለታችንን ካረጋገጠ ታስረን በግድ እንድንቀርብ ትዕዛዝ ሊያስትላልፍብን ይችላል። ስለዚህ ግልፅ ያልሆነልን ወይም መጥሪያው አይመለከተኝም የምንል ከሆነ መጥሪያውን ተቀብለን በቀጠሮው ቀንና ሰዓት ቀርበን ማስረዳት ወይም ማጣራቱ ተገቢ ነው።

2.ቀጠሮ ማክበር

ማንኛውም መጥሪያ ከደረሰን በቀጠሮው ቀንና ሰዓት በፍርድ ቤቱ መገኘት አለብን። በፍርድ ቤቱ ስንጠራም በአካል መቅረብ እና መቅረባችንን ማሳወቅ አለብን። ፍርድ ቤቱ ሳያሰናብተንም ችሎቱን ለቅቀን መሄድ አንችልም፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡- 👇👇👇👇👇👇👇
https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=7390

በጠበቃና የሕግ አማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍121
👍7
የአዲስ አበባ የኑሮ ውድነት እና የዶላር $ ምንዛሬ በእኛ ተጠቃሚዎች ላይ የፈጠረው ምስል። #አለሕግ https://t.me/lawsocieties
👍12
ሩዋንዳ ከ4 ሺህ በላይ ቤተክርስቲያናትና መስጂዶች ዘጋች

የድምጽ ብክለት ማስከተልና የደህንነት ደንቦችን መጣስ ለመዘጋታቸው ምክንያት ሆኖ ቀርቧል።

https://bit.ly/3AanM7d
👎3👍2
በአዲስ አበባ ከተማ በ2016 በጀት ዓመት 38 ሺህ 239 ጋብቻ እና 8 ሺህ 949 ፊቺ መመዝገቡ ተገልጿል።

በዚሁ በጀት ዓመት 765 ሺህ 272 የነዋሪነት መታወቂያ የተሰጠ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 715 ሺህ 138ቱ የዲጂታል መታወቂያ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ከልደት ጋር ተያይዞም ከዚህ ቀደም በ40 የጤና ተቋማት ላይ ብቻ ይሰጥ የነበረው ምዝገባ አሁን ላይ በ73 ጤና ተቋማት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ተብሏል፡፡ (AMN) #tikvahethmagazine
#AddisAbaba
👍12😁31👏1🤔1